o ሁሉም
በክርስቶስ ከማመኑ በፊት ኃጢአተኛ ነው
ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል፤ ሮሜ ፫፣ ፳፫
- ከዚህ ኃጢአት /እና ሞት/ መዳን አለብን፤ መድኃኒቱም ኢየሱስ ነው፤
እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ። ማቴ ፩፣ ፳፩
o በክርስቶስ ካመንን በኋላም እንኳ ኃጢአት ይኖርብናል - ባልዳነ ሥጋ ባልዳነች ዓለም ስለምንኖር
ኃጢአት የለብንም ብንል ራሳችንን እናስታለን፥ እውነትም በእኛ ውስጥ የለም።
፩ ዮሐ ፩፣ ፰
-
ከዚህ
ኃጢአት
መንጻት
አለብን፤
/ከዳንን
በኋላ
በየጊዜው
ስለምንቆሽሽ/
የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል። ፩ ዮሐ ፩፣ ፯
·
ሁሉም የሚድነው በክርስቶስ በማመን ብቻ ነው።
በልጁ
የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ ዮሐ ፫፣ ፴፮
·
ሌላ መድኃኒት የለም
መዳንም
በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና። የሐዋ ፬፣ ፲፪
·
አምነን መዳናችንን የምረጋግጠው አሁን ነው።
እንግዲህ በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት አሁን ኵነኔ የለባቸውም። ሮሜ ፰፣ ፩
·
ካላመንንም ፍርዱ አሁን ነው።
በእርሱ በሚያምን አይፈረድበትም፤ በማያምን ግን በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ስላላመነ አሁን ተፈርዶበታል።። ሮሜ ፰፣ ፩