/የእግዚአብሔር ስም - ቀጣይ/
እኛም ዛሬ በወል ስም -በክርስቶስ - ክርስቲያን የተባልነው- ከስማችን ጀምሮ ሕይወታችን እንዲለወጥ የክርስቶስን ፈለግ በመከተል እርሱን ወደ መምሰል እንድናድግ ነው።
ዲ/ን ኢንጅነር አብርሃም አብደላ
ነሐሴ ፲/ ፳፻፱ ዓ/ም - ጎንደር
Ø የእግዚአብሔር ወዳጆች እግዚአብሔር ካደረገላቸው ነገር ጋር በማያያዝ ለልጆቻቸው ስም ያወጡ ነበር።
ምናሴ - ማስረሻ፡- አባቱ ዮሴፍ መከራየን የአባቴን ቤት አስረሳኝ ሲል። ዘፍ ፵፩፣፶፩
ሳሙኤል - እግዚአብሔር ሰማ - መካኒቱ ሐና ጸሎቷን ስለሰማ ልጅ ስለሰጣት፡      ፩ ሳሙ ፩፣ ፳
o   ዛሬ የእኛ ስም አወጣጥ ምን ይመስላል? - የእግዚአብሔር ወገን መሆናችንን የሚያሳይ ነው?.. ስሞቻችንን ብንፈትሻቸው፡
-      ቦግ አለ፣ ዱብ አለ።  - ኩራባቸው፣ ሰጥአርጋቸው፣ 
Ø ቦታዎችንም ከእግዚአብሔር ጋር በማያያዝ ይሰይሙ ነበር።
o   አጋር ከሣራ ተሰዳ ስትወጣ እግዚአብሔር አገኛት - በመልአኩ፡
እርስዋም ይናገራት የነበረውን የእግዚአብሔርን ስም ኤልሮኢ ብላ ጠራች የሚያየኝን በውኑ እዚህ ደግሞ
አየሁትን? ብላለችና። ስለዚህም የዚያ ጕድጓድ ስም ብኤርለሃይሮኢ ተብሎ ተጠራ፡  ዘፍ ፲፮፣ ፲፫ - ፲፬
Ø እግዚአብሔር የወዳጆቹን ስም ይለውጣል። 
- አብራም /ታላቅ አባት/
- አብርሃም /የብዙዎች አባት/… 
- ያዕቆብ /አሰናካይ -ተረከዝ
የሚይዝ (ሲወለዱ የኤሳውን እግር ይዞ ስለነበር ወላጆቹ ያወጡለት 
እግዚአብሔር ግን - እስራኤል
- አለው፡- እግዚአብሔር ያሸንፋል ማለት ነው።
ወዳጆቹ ወደፊት የሚሆኑትን በማየት ሕይወታቸውን ለመለወጥ ስማቸውን ከመለወጥ ይጀምራል።እኛም ዛሬ በወል ስም -በክርስቶስ - ክርስቲያን የተባልነው- ከስማችን ጀምሮ ሕይወታችን እንዲለወጥ የክርስቶስን ፈለግ በመከተል እርሱን ወደ መምሰል እንድናድግ ነው።
የእግዚአብሔር ስም ለእኛ ምን ያስተምረናል?
Ø ይመልስልናል፡-  በስማችን ስንጠራ - አቤት- ብለን መልስ እንሰጣለን።
በስም መጥራት የግንኙነቶች መጀመሪያ /ትውውቅ/ ፣ የሥራ መጀመሪያ ነው። ከጠራን በኋላ ወደ ጉዳያችን እንገባለን።
o   እግዚአብሔር ስም ያለው መሆኑ እንድንጠራው ያስችለናል። እርሱም 
እንደሚመልስልን ማረጋገጫ ነው። 
o   ጆሮ እያለው በስሙ ተጠርቶ የማይመልስ የለም። - ጆሮን የፈጠረ አምላክ ይሰማል
Ø ግንኙነትን ያመለክታል አጠራራችን ግንኙነታችንን ያመለክታል። ከስሞቹ የትኛውን እንደምንጠቀም የሚያሳየው ቅርበታችንን ነው፤
o   ለምሳሌ እኔ ስጠራ፡-
§  አቶ አብርሃም / ጋሼ አብርሃም ብሎ የሚጠራኝ - የሥራ ግንኙነትን ያሳያል፤ በክብር በሩቁ የምጠራበት ነው ፡፡ 
§  አብርሽ - የወዳጅ መጥሪያ ነው- ቅርበትን ያሳያል፤
§  ባባ - የአባትና የልጅ..የበለጠ ቅርበትን ያሳያል።
o   እግዚአብሔርን ስንጠራው የትኛውን እንጠቀማለን። እግዚአብሔር  የሚለው በተፈጥሮ ሁሉም እርሱን የሚጠራበት - የአክብሮት -የጌትነቱ-የፈጣሪነቱ
ነው። ለእኛ ግን ከዚያም በላይ ነው። በሩቁ የምናከብረው ብቻ አይደለም። ቅርብ ነው- አባታችን ስለሆነ፤ 
ጌታ ስትጸልዩ፡- አባታችን ሆይ - በሉ  አለ
አባ አባት ብለን የምንጮኽበትን የልጅነት መንፈስ ተቀበላችሁ
እንጂ እንደገና ለፍርሃት የባርነትን መንፈስ አልተቀበላችሁምና።  
ሮሜ ፰፣ ፲፭።
አባ፣ አባት፡- የልጅነት - የቅርበት ስለሆነ- በዚህ እንድንጠራው ይፈልጋል።
Ø በከንቱ አይጠራም፡ -  ስም
መጠሪያ ቢሆንም በትንሹ በትልቁ መጥራት የለብንም። ከ፲ቱ ትዕዛዛት አንዱ ሆኖ መሰጠቱ ይገርማል። ለስሙ ምን ያህል እንደሚጠነቀቅ/
እኛም እንድንጠነቀቅ በቋሚነት በ፲ቱ ትእዛዛት ተካተተ። 
የእግዚአብሔርን የአምላክህን ስም በከንቱ አትጥራ እግዚአብሔር ስሙን በከንቱ የሚጠራውን ከበደል አያነጻውምና።   ዘጸ ፳፣ ፯ፀ ስሙን በከንቱ መጥራት -ማለት
o   ያለቦታው መጥራት - እግዚአብሔርን ለጥፋት ተባባሪ ማድረግ
o   ስሙን ማሰደብ፡- የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን በማይሆን ቦታ/ በኃጢአት/ ብንገኝ የሚሰደበው እግዚአብሔር ነው። 
Ø መጠጊያ - የጸና ግንብ ተብሏል። - 
o   የእግዚአብሔር ስም የጸና ግምብ ነው ጻድቅ ወደ እርሱ ሮጦ ከፍ ከፍ ይላል።  ምሳ ፲፰፣ ፲
o   ጻድቅ ሮጦ - የሚጠጋበት ፣ ከዚያም የሚከብርበት ነው።
o   ስሙ መጠጊያ ነው፤-ከፀሐይ፡ ከዝናብ.. እንደምንጠጋው። እረፍት በእርሱ ነው፡፡
Ø መድኃኒት -
o   እንዲህም ይሆናል የእግዚአብሔር ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል
እግዚአብሔርም እንደ ተናገረ፥ በጽዮን ተራራና በኢየሩሳሌም መድኃኒት ይገኛል።   ኢዩ ፪፣ ፴፪
o   የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናልና።   ሮሜ ፲፣ ፲፫
o   ስሙን መጥራት ማለት - ግንኙነትን የሚያሳይ ነው። ስላወቀን/ስላወቅነው ነው። 
በአጠቃላይ የእግዚአብሔር ስም፡-
o   ስለ እግዚአብሔር ማንነት እንድናውቅ ያደርገናል። 
o   እንደስሙ እንደሚሠራ ያረጋግጥልናል። ሰዎች እንደስማቸው ላይሆኑ ይችላሉ። ትዕግስት - ተብለው ትዕግስት የሌላቸው ሊሆኑ
ይችላሉ። እግዚአብሔር ግን እንደስሙ ይሠራል።/ ያደርጋል።
o   እንድንታመንበት ይረዳናል።
Ø የስሙ ኃይል ተግባራዊ መገለጫ
- ኢየሱስ
o   ጌታ ሲወለድ መጠሪያው፡-
§  ኢየሱስ - አዳኝ - በኃጢአት ስለጠፋን ያዳነን መድኃኒት /ማቴ ፩፣ ፳፩/
§  አማኑኤል - እግዚአብሔር ከእኛ ጋር - በኃጢአት ከእርሱ ርቀን ስለነበር እርሱ እኛን ፈልጎ መጣ፣ - ከእኛ ጋር ሆነ።
 /ማቴ ፩፣ ፳፫/
o   ለእኛም ስሙ የወል መጠሪያችን ሆኗል፤ - ክርስቶስ - ክርስቲያን በእንግሊዝኛው  Christ – Christian – /adjective/ -  የክርስቶስ። 
§  ክርስቲያን የሚለው የወል ስማችን የክርስቶስ መሆናችንን ያመለክታል፡፡ በእኛ ላይ ባለቤት ነውና፣ በመፍጠርና በማዳን።
ስለዚህ ባለቤት ካለን በእርሱ እና ለእርሱ ልንኖር ይገባል። 
o   ከስም ሁሉ በላይ የሆነ - ሁሉ የሚንበረከክለት ስም
ከስምም ሁሉ በላይ ያለውን ስም ሰጠው፤ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ፥… ነው።  ፊልጵ ፪፣ ፱ - ፲
§   በሰዎች ምስጋና
እና ልመና፣ ለአጋንንት ውጊያ የሚጠራ፣
o   ልመና ወደ እግዚአብሔር የሚቀርብበት 
እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ አብ በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ ይሰጣችኋል። እስከ አሁን በስሜ ምንም አልለመናችሁም፤ ደስታችሁ ፍጹም እንዲሆን ለምኑ ትቀበሉማላችሁ።   ዮሐ ፲፮፣  ፳፫ - ፳፬።
o   ምስጋና ወደ እግዚአብሔር የሚደርስበት
ሁልጊዜ ስለ ሁሉ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አምላካችንንና አባታችንን ስለ ሁሉ አመስግኑ።   ኤፌ ፭፣ ፳
o   ሁሉ የሚደረግበት
እግዚአብሔር አብን በእርሱ እያመሰገናችሁ፥ በቃል ቢሆን ወይም በሥራ የምታደርጉትን ሁሉ በጌታ በኢየሱስ ስም አድርጉት።  ቆላ ፫፣ ፲፯
o   ስለስሙ መነቀፍ ደስታ ነው።
እነርሱም ስለ ስሙ ይናቁ ዘንድ የተገባቸው ሆነው
ስለ ተቈጠሩ ከሸንጎው ፊት ደስ እያላቸው ወጡ፤   የሐዋ ፭፣ ፵፩
§  በስሙ መናቅን ካገኘነው - የተገባቸው ሆነው ስለተቆጠሩ
- ዕድል ነው።
§  ስሙን ስለጠራን፣ ስላስተማርን፣ ስለመሰከርን፣ ስላከበርን ማለት ነው። 
§  ስሙ ለጠላት ቁጣን ፣ ለእኛ ለልጆቹ ግን ደስታን ያመጣል።
o   በስሙ አለማመን ፍርድን ያስከትላል። 
በእርሱ በሚያምን አይፈረድበትም፤ በማያምን ግን በአንዱ በእግዚአብሔር
ልጅ ስም ስላላመነ አሁን ተፈርዶበታል።   ፩ ዮሐ ፫፣ ፲፰
§  በስሙ አለማመን ማለት ስሙ የሚገልጠውን ማንነቱን፣ ሥራውን፣ ባሕርይውን፣ ኃይሉን…አለማመን ማለት ነውና
o   ስሙ ከፍተኛ ኃይል ስላለው አጋንንትን የምንዋጋበት ብቸኛው መንገድ ነው።
§  ያመኑትንም እነዚህ ምልክቶች ይከተሉአቸዋል፤ በስሜ አጋንንትን
ያወጣሉ፤ በአዲስ ቋንቋ ይናገራሉ፤ እባቦችን ይይዛሉ፥
….. ወዘተ…. ከስሙ ጋር የተያያዙ ብዙ ነገሮች ናቸው።
o   ስምህ ይቀደስ፣ ስለስሙ መመስከር፣ …..
ኢየሱስ - ስሙን አንፍራው። እንደሌሎች በትንሽ በትልቁ ሳይሆን በክብር
እንጥራው።
የጌታ መሆናችን ዋናው መገለጫው ይህ ነውና-
ጌታ ለእርሱ የሆኑትን
ያውቃል፥ ደግሞም፦ የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ከዓመፅ ይራቅ የሚለው ማኅተም ያለበት የተደላደለ የእግዚአብሔር መሠረት
ቆሞአል።  ፪ ጢሞ ፪፣ ፲፱።
-     
እግዚአብሔር የዓለማት አስገኚ ጌታ ባለቤት ነው። - በተፈጥሮ
-     
በልጁ በማመን በማዳን ደግሞ እያንዳንዱ በፈቃዱ እኔ የጌታ
ነኝ ይላል። 
-     
የጌታ የምሆነው የጌታ ነኝ ብየ በአፍ ስለተናገርኩ አይደለም።
በስም ክርስቲያን ነኝ ስላልኩም አይደለም፤ ስለእርሱ ስላወራሁ፣ ስለመሰከርኩ… አይደለም።
 -- ጌታ ለእርሱ
የሆኑትን (እርሱ) ያውቃል
-     
የጌታ መሆናችን ማረጋገጫው - ማኅተም ያለበት የተደላለደ
መሠረት - ስሙን የሚጠራ ከአመጽ ይራቅ  የሚለው  በተግባር
የምንኖረው የቅድስና ሕይወት ነው።
……………ይቀጥላል……………ዲ/ን ኢንጅነር አብርሃም አብደላ
ነሐሴ ፲/ ፳፻፱ ዓ/ም - ጎንደር
 
No comments:
Post a Comment
አስተያየትዎን ይስጡ / Give Comment