Thursday, March 30, 2017

እግዚአብሔርን ማወቅ- ክፍል ፫


የእግዚአብሔር ባሕርያት

ስለእግዚአብሔር ለማወቅ ፍንጭ የሚሰጡን፣ የሚገልጡት ባሕርያቱ ናቸው።

ተፈጥሯዊ መገለጫዎቹ፡-  ከሌላው ፍጥረት ጋር በሚነጻጸር መልኩ ከመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ-ቃላት በተቀመጠው መሠረት በ፬ መልኩ ይገለጻል።

፩. አይታይም፡-  እግዚአብሔር ረቂቅ - መንፈስ ነው። ደቃቅ ሆኖ በአጉሊ መነጽር /በማይክሮስኮፕ/ ወይም ሩቅ ሆኖ በርቀት - መነጽር /በቴሌስኮፕ/ የሚታይ አይደለም።

-      « ብቻውን አምላክ ለሚሆን ለማይጠፋው ለማይታየውም ለዘመናት ንጉሥ ምስጋናና ክብር እስከ ዘላለም ድረስ ይሁን፤ አሜን።»  ፩ ጢሞ ፩፣ ፲፯

o   ስሜት ሕዋሳቶቻችን ልንደርስበት አንችልም።

o   ከምናውቃቸው በመጀመር የርቀት /የመርቀቅ/ ቅደም ተከተል ሲቀመጥ ፡ ከግዙፍ ወደ ረቂቅ፡-

§  መሬት - ውኃ- እሳት - ነፋስ - ነፍስ - መላእክት -የሥላሴ አካል።
ይህ ማለት ከመሬት ውኃ ይረቃል፣ ከውሃ እሳት፣ ከእሳት ነፋስ፣ ከነፋስ ነፍስ፣ ከነፍስ መላእክት፣ ከመላእክት ደግሞ ሥላሴ ይረቃሉ።
አባቶች አንደሚያስተምሩት የመላእክት እና የሥላሴ አካል ግን የአንዲት ጎመን ዘር እና የተራራ ያህል አይገናኝም፣ አይነጻጸርም።

o   እግዚአብሔር የማይታይ እንጂ የማያይ አይደለም።

o   በእምነት ግን በሕይወታችን እናየዋለን።