የዚህ ሕግ መጽሐፍ ከአፍህ አይለይ፥ ነገር ግን የተጻፈበትን ሁሉ ትጠብቅና ታደርግ ዘንድ በቀንም በሌሊትም አስበው የዚያን ጊዜም መንገድህ ይቀናልሃል ይከናወንልሃልም። ኢያ ፩፣ ፰
ነገር ግን በእግዚአብሔር ሕግ
ደስ ይለዋል፥ ሕጉንም በቀንና በሌሊት ያስባል። …. የሚሠራውም ሁሉ ይከናወንለታል። መዝ ፩፣ ፩ - ፫
-
እግዚአብሔር ከሙሴ በኋላ ላስነሳው መሪ- ለኢያሱ- ከ፪
ሚሊየን በላይ ሕዝብ ለሚመራው፣ ከነዓንን ለማውረስ ላዘጋጀው ሰው ያስታጠቀው መሣሪያ - ቃሉን እንዲያስብ ነው።
o
የሚመራው ቀላል ሕዝብ አይደለም። በጉዞ የታከተው…
o
ከነዓን ምድሪቱ በአሕዛብ እጅ ስለሆነች ጦርነት አለበት።
፩. ሕጉ ምንድን ነው? –
የእግዚአብሔር ሕግ ፍጹም ነው ነፍስን ይመልሳል። መዝ ፲፰/፲፱፣
፯
ሕጉ፡- ፍጹም - እንከን የለሽ
ነው። ሕጉ ለሰዎች የተሰጠ ነው። እግዚአብሔር ከሰዎች የሚፈልገውን የቅድስና መስፈርት ያሳያል። ወይም ለእግዚአብሔር ቅድስና ሰዎች
መስጠት ያለባቸውን ምላሽ ያስቀምጣል።
ከእግዚአብሔር ጋር የሚኖረው
/መኖር የሚፈልገው ሰው እንደ እግዚአብሔር ኃጢአት የሌለበት እንከን የለሽ መሆን አለበት።
ይህን ደግሞ ማድረግ ለሰው
አልተቻለውም። በሕጉ መጽደቅ / በእግዚአብሔር ፊት የመቆም ብቃት ማግኘት/ አልተቻለም።
ይህም የሕግን ሥራ በመሥራት ሥጋ የለበሰ ሁሉ በእርሱ ፊት ስለማይጸድቅ ነው። ሮሜ ፫፣ ፳።
ሕጉን መሥራት/መፈጸም ባንችልም
- ማሰብ ግን አለብን።
-
ሕጉን የምንፈጽመው
በትዕዛዝ ግዳጅ - ሳይሆን በፍቅር መንፈስ ነው።
-
ፍቅር - የእኛ
ጥረት ውጤት ሳይሆን እግዚአብሔር በእኛ ውስጥ የሚገልጸው የመንፈስ ቅዱስ ፍሬ ነው። -- ገላ ፭፣፳፪ - ፍቅር ከ፱ኙ የመጀመሪያው የመንፈስ ቅዱስ ፍሬ ነው።
-
ሕጉን የምንፈጽመው
በክርስቶስ ስንሆን እና በመንፈስ ቅዱስ የፍቅር ሰዎች ስንሆን ነው።
የሚያምኑ ሁሉ ይጸድቁ ዘንድ ክርስቶስ የሕግ ፍጻሜ ነውና። ሮሜ ፲፣ ፬
ፍቅር ለባልንጀራው ክፉ አያደርግም፤ ስለዚህ ፍቅር የሕግ ፍጻሜ ነው። ሮሜ ፲፫፣ ፲