እኔ….. ነኝ ብሎ በሥልጣን ቃል የተናገረ፡
በብሉይ ኪዳን፡ እግዚአብሔር ብቻ፡ ነው።….ሰባቱን ብናይ፡-
- እኔ ለአንተ ጋሻህ ነኝ። ዘፍ ፲፭፣፩
- እኔ ኤልሻዳይ ነኝ።. ዘፍ ፲፯፣፩
- የአባቶችህ አምላክ እግዚአብሔር
እኔ ነኝ። ዘፍ ፵፮፣፫
- ያለና የሚኖር እኔ ነኝ። ዘጸ ፫፣፲፬
- እኔ እግዚአብሔር ነኝ። ዘጸ ፮፣፫
- ከግብጽ ምድር ከባርነት ቤት ያወጣሁህ
እግዚአብሔር አምላክህ አኔ ነኝ። ዘጸ ፳፣፪
- እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ቀናተኛ
አምላክ ነኝ። ዘጸ ፳፣፪
በአዲስ ኪዳን፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ፡ ነው።….ሰባቱን ብናይ፡-ለ
- የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ። ዮሐ
፮፣፴፭
- እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ። ዮሐ
፰፣፲፪
- እኔ የበጎች በር ነኝ። ዮሐ ፲፣፯
- መልካም እረኛ እኔ ነኝ። ዮሐ ፲፣፲፩
- ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ። ዮሐ
፲፩፣፳፭
- እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም
ነኝ። ዮሐ ፲፬፣፮
- እውነተኛ የወይን ግንድ እኔ ነኝ።
ዮሐ ፲፭፣፩
እኔ…..እንዲህ… ነኝ ብሎ የተናገረና መናገር የሚችል አምላክ ብቻ ነው።
ምክንያቱም፡-
፩. የማይለወጥ
/የማይወሰን ስለሆነ፡
እንዲህ / እዚህ ነበርኩ። እንዲያ / እዚያ እሆናለሁ… አይልም። ቦታ
ጊዜ ሁኔታ አይገድበውም።
እግዚአብሔር አይለወጥም፡ አይወሰንም።
ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንትና ዛሬም
እስከለዘላለምም ያው ነው።… ዕብ ፲፫፣፰
፪.
ሁሉ በእጁ / በእርሱ ስለሆነ፡
እግዚአብሔር ሁሉን ፈጥሮአል፣ ሁሉን ይመግባል።
ኢየሱስ ክርስቶስ ሁሉ ከእርሱና በእርሱ ለእርሱም ነውና፤ ለእርሱ ለዘላለም ክብር ይሁን፤ አሜን። ሮሜ ፲፩፣፴፮።
፫. ከእርሱ
በላይ ማረጋገጫ ስለሌለ፡
አንድ ነገር -- ነው / አይደለም-- የሚል ልዩነት ቢፈጠር በሦስተኛ
/ በበላይ አካል እንዲረጋገጥ ይደረጋል።
እግዚአብሔር ሌላ አስረጅ፣ ምስክር አያስፈልገውም። ከእርሱ በላይ የሚያረጋግጥ
ስለሌለ።
፬. ነኝ
ያለው የሆነውን ስለሆነ
ሁልጊዜ የነበረውን፣ የሆነውን፣ ወደፊትም የሚሆነውን ነኝ አለ።
ያልሆነውን፣ የማይሆነውን ነኝ አላለም፤ አይልምም።