Wednesday, December 3, 2014

የፈቃዱ ምሥጢር - ክፍል ፪

......ባለፈው ክፍል ኤፌ ፩፣ ፩ - ፲፬
.... በክርስቶስ ለማድረግ እንደ ወደደ እንደ አሳቡ፥ የፈቃዱን ምሥጢር አስታውቆናልና፤
በዘመን ፍጻሜ ይደረግ ዘንድ ያለው አሳቡም በሰማይና በምድር ያለውን ሁሉ በክርስቶስ ለመጠቅለል ነው።...
የሚለውን አሳብ ማየታችን ይታወሳል። ከዚህ ክፍል ምን እንማራለን? 
፩. ምሥጢረ-ሥላሴ፡-
Ø  መዳናችን የሥላሴ ሥራ ነው ። ሥላሴ - አብ ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ።
²  አብ - ዓለም ሳይፈጠር - አቀደ -- የአሳብ መነሻ - ልብ።
²  ወልድ - ዓለም ከተፈጠረ በኋላ - ሰው ሆኖ የአብን ዕቅድ ፈጸመ፣ ሞቶ አዳነን።
²  መንፈስ ቅዱስ - ዓለም ካለፈ በኋላ ለምንወርሳት መንግሥተ ሰማያት አሁን ማረጋገጫ /ማኅተም ሆነ።
፪. ምሥጢረ ሥጋዌ    
Ø  ቁ. ፫፡- የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት
²  አምላክ -ሲል- ክርስቶስ ፍጹም ሰው መሆኑን
²  አባት - ሲል- ክርስቶስ ፍጹም አምላክ መሆኑን - የአብ የባሕርይ ልጅ መሆኑን ያሳያል።
፫. ሁሉ በክርስቶስ እንደሆነና እንደሚሆን -  ሁሉ በእርሲ ሆነ ዮሐ ፩፣ ፫።
-      ከቁ .፩ - ፲፬ -- ኢየሱስ ክርስቶስ  ፲፬ ጊዜ ተጠቅሷል። -- በየቁጥሩ ማለት ይቻላል። ቃሎቹን ብናያቸው፡-
Ø  የኢየሱስ ክርስቶስ  ፩  ፫ 
Ø  በክርስቶስ ኢየሱስ  ፩ 
Ø  ከኢየሱስ ክርስቶስ  ፪  --- ምንጭን ያሳያል - የጸጋና የሰላም ምንጫችን እርሱ ነው።
Ø  በኢየሱስ ክርስቶስ  ፭
Ø  በውድ ልጁ  ፮  ፯
Ø  በክርስቶስ ፫  ፬  ፱  ፲  ፲፩  ፲፪  ፲፫
-      የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ - ባለቤትነቱን ያሳያል። እንደ ሐዋርያ ሆኖ የሚሠራ ማንኛውም አገልጋይ የኢየሱስ ክርስቶስ ነው። - የእገሌ ወይም የቤተ ክርስቲያን አይደለም።
Ø  ራሱን ያስተዋወቀበት ስም ነው።-  ክርስቶስ መታወቂያው ሆነ ፤ መታወቂያችን ሊሆን ይገባል።
-      ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም - ምንጭን ያሳያል። የተደረገልን የመዳን ጸጋ/ቸርነት እና ያገኘነው ሰላም ምንጩ ክርስቶስ ነው።


-      በክርስቶስ ፲፩ ጊዜ የተጠቀሰው --  በክርስቶስ ውስጥ/ ሥር / በኩል መሆንን ያመለክታል።  in Christ
-      ክርስቶስ የተጠቀሰባቸውን አሳቦች ስናይ፡-
Ø  ራሱን በማስተዋወቅ - ፩ ጊዜ - ቁ. ፩
Ø  በመልእክቱ አድራሻ - ፩ ጊዜ - ቁ. ፩
Ø  በሠላምታ - ፩ ጊዜ - ቁ. ፪
Ø  በበረከት - ፪ ጊዜ - ቁ. ፫
Ø  በዕቅድ / በአብ ሥራ/ - ፫ ጊዜ - ቁ. ፫ - ፮
Ø  በደኅንነት /በወልድ ሥራ/ - ፫ ጊዜ - ቁ. ፯ - ፲
Ø  ርስትን በመውረስ /በመንፈስ ቅዱስ ሥራ/ - ፫ ጊዜ - ቁ. ፲፩ - ፲፫
-      ክርስቶስ ሁሉ በሁሉ ነው። ሁለንተናችን/ሁለመናችን ነው። መታወቂያችን፣ አድራሻችን፣ የሠላምታችን መግለጫ፣ የበረከታችን ምንጭ፣ የመዳናችን መሠረት እና ፍጻሜ….።
፫. የእግዚአብሔርን የፈቃዱን ምሥጢር - ማስተዋል አለብን፤ መግለጥና ማስተማር አለብን
-      የዚህ ክፍል ዋናው የፈቃዱ ምሥጢር የተባለው ቁ. ፱ - ፲
Ø  የፈቃዱን ምሥጢር አስታውቆናልና፤ በዘመን ፍጻሜ ይደረግ ዘንድ ያለው አሳቡም በሰማይና በምድር ያለውን ሁሉ በክርስቶስ ለመጠቅለል ነው።  - ለማዳን።
Ø  እግዚአብሔር ማንም እንዲጠፋ አይፈልግም፤ - ወደ ገሃነም እንዲገባ የወሰነበት ሰው የለም።
²  በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና። - ዮሐ ፫፣ ፲፮
Ø  ሰዎች ሁሉ እንዲድኑ ነው ፍላጎቱ፡-
²  ሰዎች ሁሉ ሊድኑና እውነቱን ወደ ማወቅ ሊደርሱ በሚወድ በእግዚአብሔር በመድኃኒታችን ፊት መልካምና ደስ የሚያሰኝ ይህ ነው።  ፩ ጢሞ ፪፣ ፫ - ፬
²  ሰዎችን ሁሉ የሚያድን የእግዚአብሔር ጸጋ ተገልጦአልና፤  ቲቶ ፪፣ ፲፩
²  ለአንዳንዶች የሚዘገይ እንደሚመስላቸው ጌታ ስለ ተስፋ ቃሉ አይዘገይም፥ ነገር ግን ሁሉ ወደ ንስሐ እንዲደርሱ እንጂ ማንም እንዳይጠፋ ወዶ ስለ እናንተ ይታገሣል። ፪ ጴጥ ፫፣ ፱
Ø  እግዚአብሔር ፍቅር ነው። - ፍርድ ነው አልተባለም። አይፈርድም ማለት አይደለም።
ዋናው ዕቅዱ፣ ፍላጎቱ፣ ፈቃዱ ሁሉም ሰው እንዲድን ነው። ----  በግድ ግን አይደለም።
²  እያንዳንዱ ሰው ይህን ፈቃዱን የመቀበል መብቱ ሙሉ በሙሉ ያለገደብ የተጠበቀ ነው። ነጻ ፈቃድ ተሰጥቷታል። ለምን ነጻ ፈቃድ ሰጠን ካልን- ዕቃ ያድርገን እያልን ነው።
²  ሰዎች የሚሰሯቸው ሮቦቶች ያለፈቃዳቸው የሚንቀሳቀሱ - በሰሯቸው ሰዎች ቁጥጥር ሥር ያሉ እና የሚመሩ ናቸው።
l  እግዚአብሔር የፈጠረው ሰው ግን ሙሉ መብትና ነጻነት ያለው - በዚህም ወዶ እና ፈቅዶ እንዲከተለው ፍላጎት ያለው ነው።
l  ይህን ነጻነት ሰው እንደፈለገ መጠቀም ቢችልም እግዚአብሔር እንዲሁ አልተወውም። የሰጠውን መብት ተጠቅሞ አብሮት ለዘላለም እንዲኖር እንደሚፈልግ መክሮታል፤ ዛሬም።
l  ካለዚያ ምርጫና መብት እንዳይኖረን አድርጎ ይፍጠረን ካልን እንደ ሮቦት / እንደ እቃ/ አደረገን ማለት ነው።
²  ሰው ይህን ነጻነቱን ተጠቅሞ የመዳን ጥሪውን ባለመቀበሉ ይፈረድበታል እንጂ ዓለም ሳይፈጠር እግዚአብሔር ለፍርድ ያዘጋጀው ሰው የለም። ደግሞስ ለምን እንደዚያ ያደርጋል?
²  እግዚአብሔር ዓለም ሳይፈጠር ያቀደው - ኋላም የፈጸመው በክርስቶስ ሁሉም የመንግሥቱ ወራሾች እንዲሆኑ ነው።

ይህን የእግዚአብሔር ዘላለማዊ እቅድና አሳብ ማስተዋል ማስፈጸም ይገባናል።

No comments:

Post a Comment

አስተያየትዎን ይስጡ / Give Comment