Wednesday, December 28, 2011

Quotes vs Bible Quotes -2

See God in every person, place, and thing, and all will be well in your world. 
                                      --Louise Hay
እግዚአብሔርን ፈልጉት ትጸናላችሁም ሁልጊዜ ፊቱን ፈልጉ። መዝ ፻፬፡፬

I'm a slow walker, but I never walk back.    --Abraham Lincoln (1809-1865)

ኢየሱስ ግን፦ ማንም ዕርፍ በእጁ ይዞ ወደ ኋላ የሚመለከት ለእግዚአብሔር መንግሥት የተገባ አይደለም አለው። ሉቃ ፱፡፷፪

A candle loses nothing by lighting another candle.....Erin Majors
  
መብራትንም አብርተው ከዕንቅብ በታች አይደለም እንጂ በመቅረዙ ላይ ያኖሩታል በቤት ላሉት ሁሉም ያበራል።
መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ።
 ማቴ ፭፡፲፭-፲፮። 
Man is given the power of anger,
not to use it against others and be angry with them but to
use it against himself if he does wrong.............pope shenuda
                            
እኔ ግን እላችኋለሁ፥ በወንድሙ ላይ የሚቆጣ ሁሉ ፍርድ ይገባዋል፤ ማቴ ፭፡፳፪


Friday, December 23, 2011

የትርጉሞች ንጽጽር

እንደ መጽሐፍ ቅዱስ በሁሉም ቋንቋዎች፡ በዘመናት ሁሉ እና በብዛት የተተረጎመ መጽሐፍ የለም። ትርጉሞች ሁለት ዓይነት ናቸው። ነጠላና አንድምታ። ነጠላ የምንለው ከቋንቋ ወደ ቋንቋ የሚተረጎም ሲሆን አንደምታ ደግሞ ከማብራሪያ ጋር በዝርዝር የሚተረጎም ነው። በዚህ ክፍል የመጽሐፍ ቅዱስን ሃሳቦች ለማግኘት እንድንችል የተለያዩ ትርጉሞችን እያነጻጸርን እናያለን። 
  ለዛሬ ለመጀመሪያ ለማነጻጸር ያህል በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በጣም ተወዳጅ የሆነውን ጥቅስ ዮሐ ፫፡፲፮  በተለያዩ ትርጉሞች እንመልከት።  በመካከላቸው ያለውን የቅርጽ ልዩነት ያስተውሉ።


« እንዲሁ እግዚአብሔር ዓለሙን ወዶታልና፡ አንድ ልጁን ቤዛ እስኪሰጥ ድረስ፡ በእርሱ ያመነ ሁሉ የዘለዓለም ሕይወት ትሆንለት ዘንድ እንጂ እንዳይጠፋ።»  አማርኛ  ፲፱፻፴፰ ዓ/ም የቀ/ኃይለ ሥላሴ የግል ቅጂ

«በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና፡» አማርኛ፡ ፲፱፻፶፬ ና ፲፱፻፹   ዓ/ም ትርጉም፡

«በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስከመስጠት ድረስ ዓለምን እንዲሁ ወዶአልና።» አማርኛ ፲፱፻፺፫ ዓ/ም አዲሱ መደበኛ ትርጉም፡


 «በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘለዓለም ሕይወትን እንዲያገኝ እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን ቤዛ አድርጎ እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲህ ወዶታልና።»                  አማርኛ  ፳፻ ዓ/ም ትርጉም፡-

Wednesday, December 21, 2011

ጥያቄ ፫

ግዚአብሔር ፍጥረታትን በ፮ ቀን እንደጨረሰ በዘፍጥረት ፩ ተጠቅሶአል። አንድ ቀን የምንለው ፀሐይ ፡ወጥታ፡ ገብታ መልሳ እስክትወጣ ያለውን ፳፬ ሰዓት ነው። ፀሐይ ግን የተፈጠረች በአራተኛው ቀን ረቡዕ ነው። ቁ ፲፬። 
    ታዲያ ከዚያ በፊት የነበሩት ፫ ቀናት (ከእሑድ- ማክሰኞ ያሉት) በምን ተቆጠሩ?

     ለዚህ ጥያቄ ተሳታፊዎች ከዚህ ጽሑፍ ሥር comments የሚለውን በመጫን post comment በሚለው መልሳችሁን መላክ ትችላላችሁ።  መልሱ ከጥቂት ቀናት በኋላ ይሰጣል።

Friday, December 16, 2011

ምሥጢረ-ሥላሴ (ክፍል ፩)


ለመጽሐፍ ቅዱስ ጥናታችን የሚያስፈልጉን ጉዳዮች በቅድሚያ በእግዚአብሔርና በክርስቶስ ማመን (ምሥጢረ-ሥላሴና ምሥጢረ-ሥጋዌ)፡ ቀጥሎም መጸለይና ለቃሉ መታዘዝ፡ በመጨረሻም ስለራሱ ስለመጽሐፍ ቅዱስ ልዩ ልዩ መረጃዎችን ማወቅ እንደሚገባን ባለፈው ጽሑፋችን አይተናል። በዚህ የትምሀርት ክፍል እነዚህን ጉዳዮች በየተራ እንመለከታለን።
፩. ምሥጢረ-ሥላሴ
ሥላሴ የግዕዝ ቃል ሲሆን ሦስትነት ማለት ነው። ሠለሰ-ሦስት አደረገ፡ ይሤለስ፡ ሥሉስ፡ ሥላሴ እያለ ግሱ ይወጣል።
ምሥጢረ-ሥላሴ የእግዚአብሔርን አንድነትና ሦስትነት የምንማርበት ክፍል ነው። እግዚአብሔር በኛ ዕውቀት ልንደርስበት የማንችል የማይመረመር ግሩም ድነቅ አምላክ ነው። ትምህርቱን ምሥጢር ያሰኘው የማይነገር ስለሆነ ሳይሆን የማይመረመር ስለሆነ ነው። ነገረ-እግዚአብሔር የማይመረመር ነው ሲባል በጭራሽ የማናገኘው እርሱም የማያገኘን- የማንገናኝ ነን ማለት አይደለም። ስለእግዚአብሔር ሙሉ በሙሉ መረዳት የማንችለው በሁለት ምክንያት ነው።
  በአእምሮ ውስንነትና  በቋንቋ ውስንት ።
- የእኛ አእምሮ (የዕውቀት ደረጃ) እግዚአብሔርን ሊደርስበት ከቶ አይችልም። እንኳን ፈጣሪን- ፍጡራንንና ፍጥረትን መርምረን አልጨረስንም።
- በቋንቋም ብንሄድ ስለእግዚአብሔር ለመግለጽ የሚችል ቃላት የሉንም። እንኳን ስለእግዚአብሔር ለራሳችን ስሜት እንኳ ቃላት የሚያጥረን ጊዜ ብዙ ነው። ቃላት ያጥረኛል የምንልባቸው ብዙ ስሜቶችና ጉዳዮች አሉን።
ስለዚህ እግዚአብሔር እርሱ ስለራሱ የገለጠልንን ያህል፡ እኛም መረዳት የቻልነውን ያህል እንማራለን።
እግዚአብሔር በሦስት ነገሮች -በስም ፡ በአካል፡ በግብር ሦስት የሆነ፡- ። በቀሩት ነገሮች ሁሉ -በመለኮት በአገዛዝ፡ በሕልውና፡ በፈቃድ፡ በመፍጠር፡ በማዳን፡ .   አንድ የሆነ አምላክ ነው። ይህ ሲባል አንድ ሆኖ ቆይቶ ሦስት የሆነ ወይም ሦስት ሆኖ ቆይቶ አንድ የሆነ አይደለም። እግዚአብሔር በአንድ ጊዜ አንድም ሦስትም ነው። አንድነቱ ሦስትነቱን አይጠቀልለውም። ሦስትነቱ አንድነቱን አይከፋፍለውም። አንድና ሦስት ሳይሆን አንድም፡ ሦስትም ነው።

Wednesday, December 14, 2011

Interesting and Unusual facts about the Bible-1

History
THE BIIBLE;- 


- was written by about 40 men over a period of about 1600 years dating from 1500 BC to about 100 years after Christ. These men wrote this Scripture as they were given inspiration by God. (2 Timothy 3:16)


The first translation of the English Bible was initiated by John Wycliffe and completed by John Purvey in 1388.


  It has since been translated in part or in whole into over 1200 languages and dialects.


  It was divided into chapters by Stephen Langton in 1228. The Old Testament was divided into verses by R. Nathan in 1488 and the New Testament by Robert Stephanus in 1551.


The entire Bible divided into chapters and verses first appeared in the Geneva Bible of 1560.


Today  is the largest seller of all books published.


Saturday, December 10, 2011

መጽሐፍ ቅዱስን ለመረዳት


መጽሐፍ ቅዱስ ፈቃደኛ በሆነ ልብ ለሚያዳምጡት ሰዎች የእግዚአብሔር ድምጽ የሚሰማበት መጽሐፍ ነው። የእግዚአብሔር ድምጽ ደግሞ በኃጢአት የወደቀውን ለማንሣት፡ የጎሰቆለውንና ያደፈውን ለማደስና ለማንጻት፡ የደከመውን ለማበርታት ሙሉ ኃይል አለው።መጽሐፍ ቅዱስ መጻፉም ለዚሁ ዓላማ ነው።
በመጽሐፍ ቅዱስ ለመጠቀምና እግዚአብሔር ከሰው ልጅ የሚፈልገውን ሁሉ ለመፈጸም ደግሞ የመጽሐፍ ቅዱስን ዓላማ፡ የአካሔድ ባህልና አጠቃላይ ታሪክ መረዳት፡ ማጥናትና ማገናዘብ ይገባል። ቅዱሳን አበው በሕይወታቸው እግዚአብሔርን ለማገልገልና ለማስደሰት የቻሉት እግዚአብሔር በመጽሐፍ የተናገራቸውን በማስተዋላቸውና በሥራ በመግለጣቸው ነው።
ባለንበት ዘመንም ምእመናን እግዚአብሔርን እንደ አምላክነቱ ለማወቅና ለማመን፡ ቅዱሳን አበውን ለመከተልና እነርሱን ለመምሰል እንዲሁም እነርሱ ያገኙትን አምላካዊ ስጦታ ለማግኘት አበው የያዙትን፡ የተመሩበትንና የተጠቀሙበትን መጽሐፍ ቅዱስ ልናውቀው፡ ልንረዳውና ልንጠቀምበት ይገባል።
መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር አሳብና ፈቃድ የተገለጠበት መጽሐፍ ነው። የእግዚአብሔርን አሳብ ደግሞ በሥጋዊ በደማዊ አእምሮ መረዳት አይቻልም። በመሆኑም ጥልቅና ምጡቅ የሆነው የእግዚአብሔር አሳብ የተገለጠበትን መጽሐፍ ቅዱስ አንብቦ ለመረዳት ከአንባቢያን አፍኣዊና ውስጣዊ ዝግጅት ማድረግ ይጠበቃል። 

Wednesday, December 7, 2011

ክርስቶስ በመጽሐፍ ቅዱስ-ሁሉ በሁሉ። ክፍል ፩



- በዚያም የግሪክ ሰው አይሁዳዊም የተገረዘም ያልተገረዘም አረማዊም እስኩቴስም ባሪያም ጨዋ ሰውም መሆን አልተቻለም። ነገር ግን ክርስቶስ ሁሉ ነው፡ በሁሉም ነው። ቆላ ፫፡፲፩
Christ in the Bible all in all p-1, READ IN PDF


ሥልጣን ሁሉ የተሰጠው፡-
- ኢየሱስም ቀረበና እንዲህ ብሎ ተናገራቸው። ሥልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ተሰጠኝ። ማቴ ፳፰፡፲፰።


ለተቀበሉት ሁሉ ሥልጣንን የሚሰጥ፡-
ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤ ዮሐ ፩፡፲፪።


የዘላለም ሕይወት የሚገኝበት፡-
- በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።  ዮሐ ፫፡፲፮።




ሁሉን ለማጽደቅ የመጣ፡-
- እንግዲህ በአንድ በደል ምክንያት ፍርድ ለኩነኔ ወደ ሰው ሁሉ እንደመጣ እንዲሁም በአንድ ጽድቅ ምክንያት ስጦታው ሕይወትን ለማጽደቅ ወደ ሰው ሁሉ መጣ።  ሮሜ ፭፡፲፰-፳፭።

Saturday, December 3, 2011

-የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መመሪያዎች



መጽሐፍ ቅዱስ ከላይ ወደ ውስጥ በሚዘልቅ አካሄድ  በ፯ ደረጃዎች እንደሚከፋፈልና ሁሉም በየደረጃው ጥቅምና ዋጋ እንዳለው ባለፈው ጽሑፋችን አይተናል።
ወደዝርዝር የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናታችን ከማለፋችን በፊት ግን ስለመጽሐፉ ጠባያት አስቀድመን ልናውቃቸው የሚገቡ ፫ ዋና ዋና ጉዳዮች አሉ። እነዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ የጥናት መመሪያዎች ይባላሉ።  
እምነት፡ ምግባር፡ እና መረጃ ።
፩. እምነት
መጽሐፍ ቅዱስ የታሪክ፡ የፍልስፍና የሳይንስ… መጽሐፍ እንዳልሆነ ከዚህ ቀደም አይተናል። መጽሐፉ ዓለማዊ ሳይሆን መንፈሳዊ የእምነት መጽሐፍ እንደመሆኑ መጠን ልንረዳው የምንችለውም በመንፈሳዊ መንገድ ነው። መጽሐፍ ቅዱስን ለመረዳት እና በተግባር ለመተርጎም/ለመኖር የሚፈልግ ማንኛውም ሰው አስቀድሞ በሁለት ነገሮች ማመን አለበት።
በእግዚአብሔርና በኢየሱስ ክርስቶስ፡፡
·         የመጀመሪያው በእግዚአብሔር ማመን - ምሥጢረ-ሥላሴ  ይባላል።  ሁሉን ያስገኘ፡ ለራሱ መገኘት ምክንያት የሌለው፡ ዓለምን የፈጠረና የሚመግብ፡ በሦስት ነገሮች ሦስትነት ያለው፡ (በስም፡ በአካል፡ በግብር) በቀሩት ነገሮች ሁሉ (በመለኮት፡ በአገዛዝ፡ በሕልውና…) አንድ የሆነ ስሙ እግዚአብሔር የሆነ ዘላለማዊ አምላክ አለ ብሎ ማመን።
·         ሁለተኛው በኢየሱስ ክርስቶስ ማመን-  ምሥጢረ-ሥጋዌ/ነገረ-ድኅነት ይባላል።  ከሦስቱ አካል አንዱ ወልድ በኋለኛው ዘመን (በአዲስ ኪዳን) ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ያለወንድ ዘር በመወለድ፡ በአጭር ቁመት፡በጠባብ ደረት ተወስኖ ሰው ሆኖ የአዳምንና የሰውን ኃጢአት ዕዳ ለመክፈል በመስቀል ላይ ውሎ ሞቶ የተነሳ፡ ዳግመኛም ለፍርድ የሚመጣ ፍጹም ሰው፡ ፍጹም አምላክ  የሆነው የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝ መሆኑን መቀበል።  

Wednesday, November 30, 2011

ታላቅ ምክር



ፍቅራችሁ ያለግብዝነት ይሁን።

ክፉውን ነገር ተጸየፉት

ከበጎ ነገር ጋር ተባበሩ፤

በወንድማማች መዋደድ

እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ፤


እርስ በርሳችሁ ተከባበሩ፤

ለሥራ ከመትጋት አትለግሙ፤

በመንፈስ የምትቃጠሉ ሁኑ፤

ለጌታ ተገዙ፤

በተስፋ ደስ ይበላችሁ፤

በመከራ ታገሡ፤

በጸሎት ጽኑ፤

ቅዱሳንን በሚያስፈልጋቸው እርዱ፤

እንግዶችን ለመቀበል ትጉ።

ሮሜ ፲፪፡፱-፲፫

የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር

አዲስ አበባ/ኢትዮጵያ

Friday, November 25, 2011

የጥያቄ ፪ መልስ


ጥያቄ -  ዕጸ-በለስ  ባትኖር አዳም አይሳሳትም ነበር?   እግዚአብሔር ለምን ዕጸ-በለስን ፈጠረ? ወይም ለምን እንዳይበላት ከለከለ? 

እግዚአብሔር በገነት የፈጠራቸው ዛፎች ከሰው ጋር ባላቸው ግንኙነት አንጻር በጥቅሉ ፬ ዓይነት እንደሆኑ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። እነዚህም በዘፍ ፪፡፱ የተጠቀሱት-
 ፩ ለማየት ደስ የሚያሰኘውን፥              ፪  ለመብላትም መልካም የሆነውን ዛፍ ሁሉ
 ፫ በገነትም መካከል የሕይወትን ዛፍ፥  ፬  መልካምንና ክፉን የሚያስታውቀውንም ዛፍ
የመጀመሪያዎቹ ሁለቱ ለማየትና ለመብላት የተፈጠሩት ብዙ ሲሆኑ የመጨረሻዎቹ ሁለቱ ግን አንድ አንድ ብቻ ናቸው። የሕይወት ዛፍ ዕጸ-ሕይወት ትባላለች። ዕጽ ማለት ተክል ሲሆን በብዙ ቁጥር ሲነገር ዕጽዋት ይሆናል። መልካሙንና ክፉን የሚያስታውቀው ዛፍ ዕጸ-በለስ ትባላለች። በለስ ቅጠሉ ሰፋፊ የሆነ ነጭ ደም ያለው ፍሬው የሚበላ አጭር ዛፍ እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ይናገራል። በለስ በመጽሐፍ ቅዱስ በብዙ ቦታ ተጠቅሶአል። ለአብነት ያህልም፡-
«እግዚአብሔርም፦ ኤርምያስ ሆይ፥ የምታየው ምንድር ነው? አለኝ። እኔም። በለስን አያለሁ እጅግ መልካም የሆነ መልካም በለስ፥ ከክፋቱም የተነሣ ይበላ ዘንድ የማይቻል እጅግ ክፉ የሆነ ክፉ በለስ ነው አልሁ።….» ኤር ፳፬፡ ፪-፫።
እግዚአብሔር አዳምን እንዳይበላ የከለከለው ዛፍ ይህ እጸ-በለስ በባሕርይው/በተፈጥሮው ከሌሎች እጽዋት የተለየ የሚያደርገው ምንም ነገር የለም። እንደማንኛውም ተክል ነው። ምናልባት የተለየ የሚያደርገው ትዕዛዝ የወደቀበት መሆኑ ብቻ ነው። ስለዚህ ጥያቄአችንን እግዚአብሔር ዕጸ-በለስን ለምን ፈጠረ? ከሚሆን ለምን ከለከለ? ቢባል ይሻላል።
ዛፊቱ መልካምንና ክፉን የሚያስታውቀው ዛፍ ተብላ ተጠቅሳለች። ይህ ማመዛዘንን የሚያመለክት የሰው ጠባይ ነው። ይህን የሰውን ጠባይ ከሚያመላክት አቅጣጫ እግዚአብሔር አዳም ዕጸ-በለስን እንዳይበላ የከለከለው በ፫ ምክንያት ነው፡-

Wednesday, November 23, 2011

በክርስቶስ ኢየሱስ ሆኖ በፍቅር የሚሠራ እምነት



በታሪክም ሆነ በተሞክሮ እንደምናውቀው ሰው በክርስቶስ ላይ ባለው እምነቱ ይጸድቃል ይድናል እንጂ የሙሴን ሕግ በመፈጸሙ ወይም በራሱ ጥረትና ሥራ እንዳልሆነ ግልጽ ነው።
በክርስቶስ የተገኘው የመዳን እምነት ከኦሪት ሥራ እንጂ ከፍቅር ሥራ አልተለያየም። ስለዚህ ሐዋርያው፡-
«በክርስቶስ ኢየሱስ ሆኖ በፍቅር የሚሠራ እምነት እንጂ መገረዝ ቢሆን አለመገረዝ አይጠቅምም::» አለ። ገላ 5;6
በክርስቶስ ከሆንን የክርስትናን ሃይማኖት ምሥጢር ለማስተዋል እንችላለን። ካልሆንን ግን ዓላማውን ስተናል። ከመንገድም ወጥተናል።
የክርስቶስ ወደዚህ ዓለም መምጣት በጥቅሉ ሲገለጥ፡
-አንደኛ ለቤዛነት - ሁለተኛ ለአርአያነት
ስለሆነ ሁለቱም በእኛ ላይ ተፈጻሚነት ሊኖራቸው የሚችለው:-
-የመጀመሪያውን በእምነት ስንቀበለው - ሁለተኛውን ክርስቶስን መስለን እንደ ክርስቶስ በመኖር በፍቅር ሥራ በተግባር ስንተረጉመው ነው። ሁለቱንም በአንድነት በመያዝ ነው።
ኢየሱስ ክርስቶስ በሥራው  በሕይወቱ፡ በትምህርቱና በተአምራቱ፡ በሕማሙና በሞቱ፡ በትንሣኤውና በዕርገቱ በዓለም ላይ ከዚያ በፊትም ሆነ በኋላ ያልታየና ያልተሰማ ተአምራዊ ታሪክ ሠርቶ የክርስትናን ሃይማኖት መሠረተ።
ቤተ ክርስቲያን ማለት ክርስቶስ የሕያው የእግዚአብሔር የባሕርይ ልጁ እንደሆነ የሚያምኑትን ክርስቲያኖች ሁሉ ያጠቃልላል። የክርስትና እምነት ምንነት በክርስቶስ ማንነት ይተረጎማል።
« ብሉይ ኪዳን ቤተ አይሁድን በሞግዚትነት አሳድጎ ለወንጌል እንዳስረከበ አሕዛብንም ፍልስፍናቸው (ሕገ-ልቦና) ወደ ክርስቶስ እንዳደረሰ ይነገራል። (ብሉይ ኪዳን ወደ ክርስቶስ ያላደረሳቸው፡ ፍልስፍና ወደ ክህደት የመራቸውም እንዳሉ አይዘነጋም።)
እውነተኛው አምልኮተ እግዚአብሔር ሊታወቅ የሚችለው በራሱ በእግዚአብሔር በኩል ብቻ ነው።
ከጥንት ጀምሮ በመረጣቸው ወገኖች አማካይነት ለዓለም ሁሉ ያዘጋጀውን የማዳን ምሥጢር ቀስ በቀስ በጊዜው ገለጠላቸው። በመጀመሪያ በቤተ እስራኤል- ቀጥሎ በቤተ ክርስቲያን፡ በፊተኛው በትንቢትና በታሪክና በምሳሌ በኋለኛው በአማናዊነትና በፍጹምነት ተገልጧል።
ትምህርተ ሃይማኖትና ክርስቲያናዊ ሕይወት
በሊቀ-ጉባዔ አባ አበራ በቀለ
መጽሐፍ የተወሰደ ከገጽ 12 – 23
አሳታሚ ማኅበረ-ቅዱሳን 1996 /