- በዚያም የግሪክ ሰው አይሁዳዊም የተገረዘም ያልተገረዘም አረማዊም እስኩቴስም ባሪያም ጨዋ ሰውም መሆን አልተቻለም። ነገር ግን ክርስቶስ ሁሉ ነው፡ በሁሉም ነው። ቆላ ፫፡፲፩
- ኢየሱስም ቀረበና እንዲህ ብሎ ተናገራቸው። ሥልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ተሰጠኝ። ማቴ ፳፰፡፲፰።
ለተቀበሉት ሁሉ ሥልጣንን የሚሰጥ፡-
ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤ ዮሐ ፩፡፲፪።
የዘላለም ሕይወት የሚገኝበት፡-
- በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና። ዮሐ ፫፡፲፮።
- እንግዲህ በአንድ በደል ምክንያት ፍርድ ለኩነኔ ወደ ሰው ሁሉ እንደመጣ እንዲሁም በአንድ ጽድቅ ምክንያት ስጦታው ሕይወትን ለማጽደቅ ወደ ሰው ሁሉ መጣ። ሮሜ ፭፡፲፰-፳፭።
- ሁሉ በአዳም እንደሚሞቱ እንዲሁ ሁሉ በክርስቶስ ደግሞ ሕያዋን ይሆናሉና። ፩ቆሮ ፲፭፡፳፪።
ሰማይ ምድር የተጠቀለለበት፡-
- በዘመን ፍጻሜ ይደረግ ዘንድ ያለው አሳቡም በሰማይና በምድር ያለውን ሁሉ በክርስቶስ ለመጠቅለል ነው። ኤፌ ፩፡፲
ሁሉ በስሙ የሚንበረከክለት፡-
- ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ መላስም ሁሉ ለእግዚአብሔር አብ ክብር ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደሆነ ይመሰክር ዘንድ ነው። ፊልጵ ፪፡፲-፲፩።
መላስም ሁሉ የሚመሰክርለት፡-
- ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ መላስም ሁሉ ለእግዚአብሔር አብ ክብር ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደሆነ ይመሰክር ዘንድ ነው። ፊልጵ ፪፡፲-፲፩።
ከሁሉ ይልቅ የሚሻለው ኑሮ፡-
- በእነዚህም በሁለቱ እጨነቃለሁ። ልሄድ ከክርስቶስ ጋር ልኖር እናፍቃለሁ። ከሁሉ ይልቅ እጅግ የሚሻል ነውና። ፊልጵ ፩፡፳፫።
No comments:
Post a Comment
አስተያየትዎን ይስጡ / Give Comment