Wednesday, December 21, 2011

ጥያቄ ፫

ግዚአብሔር ፍጥረታትን በ፮ ቀን እንደጨረሰ በዘፍጥረት ፩ ተጠቅሶአል። አንድ ቀን የምንለው ፀሐይ ፡ወጥታ፡ ገብታ መልሳ እስክትወጣ ያለውን ፳፬ ሰዓት ነው። ፀሐይ ግን የተፈጠረች በአራተኛው ቀን ረቡዕ ነው። ቁ ፲፬። 
    ታዲያ ከዚያ በፊት የነበሩት ፫ ቀናት (ከእሑድ- ማክሰኞ ያሉት) በምን ተቆጠሩ?

     ለዚህ ጥያቄ ተሳታፊዎች ከዚህ ጽሑፍ ሥር comments የሚለውን በመጫን post comment በሚለው መልሳችሁን መላክ ትችላላችሁ።  መልሱ ከጥቂት ቀናት በኋላ ይሰጣል።

1 comment:

  1. ይህ ማለት እግዚአብሔር ሰማይና ምድርን በስድስት ቀን ሳይሆን በአንድ ቀን ውስጥ ፈጠረ ማለቱ ነውን? አይደለም። አስቀድመን እንደተመለከትነው « ዮም » የሚለው ቃል ጊዜን የሚያመለክት ቢሆንም ከቶም የተወሰነ ጊዜን ብቻ ለይቶ የሚያመለክት ቃል አይደለም። ስለዚህ የዕብራይስጡ ቋንቋ ትርጉሙ እኛ እንደምንተረጉመው ግልጽና የተወሰነ ጊዜን የሚያመለክት ቢሆን፥ በመጽሐፍ ቅዱስ ይህ ቃል በተጠቀሰበት ቦታ ሁሉ እንዳለ ትርጉሙን መውሰድ እንችል ነበር። በዘፍጥረት ምዕራፍ አንድ መዝጊያ በትክክል እንዲህ ብለን መተርጎም ያስችለን ነበር ይኸውም ፡- ማታም ሆነ ቀንም ሆነ ስድስተኛው ቀን ስለዚህ ሰማይና ምድር ተሰርቶ ተፈጸመ።» ማለት እንችል ነበር።

    ReplyDelete

አስተያየትዎን ይስጡ / Give Comment