የእግዚአብሔር ስም
ሙሴም እግዚአብሔርን፦ እነሆ፥ እኔ ወደ እስራኤል ልጆች በመጣሁ ጊዜ። የአባቶቻችሁ አምላክ ወደ እናንተ ላከኝ ባልሁም
ጊዜ። ስሙስ ማን ነው? ባሉኝ ጊዜ፥ ምን እላቸዋለሁ? አለው።
እግዚአብሔርም ሙሴን፦ «ያለና የሚኖር» እኔ ነኝ አለው እንዲህ ለእስራኤል ልጆች። «ያለና የሚኖር» ወደ
እናንተ ላከኝ ትላለህ አለው። … ዘጸ ፫፣ ፲፫ - ፲፬
እግዚአብሔርም በደመናው ውስጥ ወረደ፥ በዚያም ከእርሱ ጋር ቆመ፥ የእግዚአብሔርንም ስም አወጀ።
እግዚአብሔርም በፊቱ አልፎ። እግዚአብሔር፥ እግዚአብሔር መሐሪ፥ ሞገስ ያለው፥ ታጋሽም፥ ባለ ብዙ ቸርነትና እውነት፥
እስከ ሺህ ትውልድም ቸርነትን የሚጠብቅ፥ አበሳንና መተላለፍን ኃጢአትንም ይቅር የሚል፥ በደለኛውንም ከቶ የማያነጻ፥
የአባቶችንም ኃጢአት በልጆች እስከ ሦስትና እስከ አራት ትውልድም በልጅ ልጆች የሚያመጣ አምላክ ነው ሲል አወጀ። .. ዘጸ ፴፬፣ ፭-፯
ስም፡- ምንድን ነው?
- መጠሪያ
ነው።በምክንያት የሚወጣ። ለልጃችን ስም ለማውጣት ብዙ እናስባለን።
የተለየ ቆንጆ ስም እንዲሆን እንፈልጋለን።
- ራስን መግለጫ /ማስተዋወቂያ/ ነው። ሰዎች ሲተዋወቁ መጀመሪያ የሚለዋወጡት
ስም ነው። እገሌ እባላለሁ።…
·
አዳም በመጀመሪያ ለእንስሳት - በኋላም ለሚስቱ ስም አወጣ።
- ባለቤትነትን ያሳያል።
በመጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ስም በራሱ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲተዋወቅ ፡-
ለሙሴ- ማን ነው? ሲሉኝ…ማን ልበላቸው ባለው ጊዜ እንዲህ ብሎታል፡-
Ø ያለና የሚኖር በእንግሊዝኛው - I AM
that I AM’- ይላል። በቀጥታ እንዳለ ብንተረጉመው፡- « እኔ እኔው ነኝ፡- ማለት ነው።
o ለእግዚአብሔር ማንም ስም አላወጣለትም፤ ራሱን ራሱ ገለጸ፣ ስሙን ተናገረ።
o የሚገልጸው ነገር ስለሌለ - እኔ እኔው ነኝ - አለ።
o በራሱ ሕልው መሆኑን - በራሴ ያለሁና በራሴ የምኖር - አለ።
Ø በአማርኛ እግዚአብሔር ብለን የሰጠነው ስም የግዕዝ ቃል ነው። አባቶች በሁለት መልክ ይተረጉሙታል፡
፩ኛ. እግዚአ - ጌታ፣ ብሔር - ሃገር/ ዓለም/ - እግዚአ ብሔር፡-
የዓለም ጌታ የሚል ነው። የዓለማት ሁሉ አስገኝ ባለቤት መሆኑን ያሳያል።
ይህ ማንነቱን በሙሉ አይገልጸውም። ያንሳል። እርሱ ከጌታም በላይ ነውና።
፪ኛ. እግዚእ- ወልድ፣ አብ - አብ፣ ሔር - መንፈስ ቅዱስ - ሥላሴነቱን ያሳያል።
ይህ ስሙም ሦስትነቱን መግለጹ እንጂ መላ ማንነቱን ሊገልጽ አይችልም።