(የእግዚአብሔር መልክ - ቀጣይ)
የእግዚአብሔር መልክ መታየት - ለውስን ፍጡር - ፊት ለፊት
በብሉይ ኪዳን - ለሙሴ
እኔ አፍ ለአፍ በግልጥ እናገረዋለሁ፥ በምሳሌ አይደለም የእግዚአብሔርንም መልክ
ያያል በባሪያዬ በሙሴ ላይ ትናገሩ ዘንድ ስለ ምን አልፈራችሁም? አለ። ዘኁ ፲፪፡ ፰
ሙሴ ክብርህን አሳየኝ ባለው
ጊዜ፡-
እግዚአብሔርም አለ፦ እነሆ ስፍራ በእኔ ዘንድ አለ፥ በዓለቱም ላይ ትቆማለህ
ክብሬም ባለፈ ጊዜ በሰንጣቃው ዓለት አኖርሃለሁ፥ እስካልፍ ድረስ እጄን በላይህ እጋርዳለሁ
እጄንም ፈቀቅ አደርጋለሁ፥ ጀርባዬንም ታያለህ ፊቴ ግን አይታይም። ዘጸ ፴፫፣ ፲፰ - ፳፫፡
-
በኋላ ከሲና ተራራ
ሲወርድ ፊቱ አንጸባረቀ፡- ጨርቅ ሸፈነው።
አሮንና የእስራኤልም ልጆች ሁሉ ሙሴን ባዩ ጊዜ፥ እነሆ የፊቱ ቁርበት አንጸባረቀ
ወደ እርሱም ይቀርቡ ዘንድ ፈሩ። ዘጸ ፴፬፣ ፳፱ - ፴፭
-
በትክክል ከእግዚአብሔር
ጋር በመንፈስ ከተገናኘን የእግዚአብሔር መልክ ይሳልብናል። እርሱን እናንጸባርቃለን። ለእኛ ላይታወቀን ይችላል። የሚያዩን ግን ያውቃሉ።
በአዲስ ኪዳን፡- ፫ ቱ ሐዋርያት- በደብረ ታቦር
በፊታቸውም ተለወጠ፥ ፊቱም እንደ ፀሐይ በራ፥ ልብሱም እንደ ብርሃን ነጭ ሆነ።
እነሆም፥ ሙሴና ኤልያስ ከእርሱ ጋር ሲነጋገሩ ታዩአቸው። ጴጥሮስም መልሶ ኢየሱስን።
ጌታ ሆይ፥ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው፤ ብትወድስ፥ በዚህ ሦስት ዳስ አንዱን ለአንተ አንዱንም ለሙሴ አንዱንም ለኤልያስ
እንሥራ አለ።…. ማቴ ፲፯፣ ፩ - ፰
-
በእግዚአብሔር
መልክ - በእርሱ ፊት መኖርን የመሰለ መልካም ነገር የለም።
ለአሕዛብ ሐዋርያ ሳውል - ጳውሎስ
ሲሄድም ወደ ደማስቆ በቀረበ ጊዜ ድንገት በእርሱ ዙሪያ ከሰማይ ብርሃን አንጸባረቀ፤
በምድርም ላይ ወድቆ ሳለ። ሳውል ሳውል፥ ስለ ምን ታሳድደኛለህ? የሚለውን ድምፅ ሰማ።…
የሐዋ ፱፣ ፩ - ፰
-
ጌታን ፊት ለፊት
በብርሃን መልክ አየው። በቀን በቀትር ስለሆነ ያየው ጌታ ከፀሐይ ብርሃን ይበልጥ አብርቷል ማለት ነው። /የሐዋ ፳፪፣፮/