Saturday, September 16, 2017

እግዚአብሔርን ማወቅ - ክፍል ፲፩


(የእግዚአብሔር መልክ - ቀጣይ)
የእግዚአብሔር መልክ መታየት - ለውስን ፍጡር - ፊት ለፊት

በብሉይ ኪዳን - ለሙሴ

እኔ አፍ ለአፍ በግልጥ እናገረዋለሁ፥ በምሳሌ አይደለም የእግዚአብሔርንም መልክ ያያል በባሪያዬ በሙሴ ላይ ትናገሩ ዘንድ ስለ ምን አልፈራችሁም? አለ።     ዘኁ ፲፪፡ ፰

ሙሴ ክብርህን አሳየኝ ባለው ጊዜ፡-

እግዚአብሔርም አለ፦ እነሆ ስፍራ በእኔ ዘንድ አለ፥ በዓለቱም ላይ ትቆማለህ

ክብሬም ባለፈ ጊዜ በሰንጣቃው ዓለት አኖርሃለሁ፥ እስካልፍ ድረስ እጄን በላይህ እጋርዳለሁ

እጄንም ፈቀቅ አደርጋለሁ፥ ጀርባዬንም ታያለህ ፊቴ ግን አይታይም።    ዘጸ ፴፫፣ ፲፰ - ፳፫፡

-      በኋላ ከሲና ተራራ ሲወርድ ፊቱ አንጸባረቀ፡- ጨርቅ ሸፈነው።

አሮንና የእስራኤልም ልጆች ሁሉ ሙሴን ባዩ ጊዜ፥ እነሆ የፊቱ ቁርበት አንጸባረቀ ወደ እርሱም ይቀርቡ ዘንድ ፈሩ።  ዘጸ ፴፬፣ ፳፱ - ፴፭

-      በትክክል ከእግዚአብሔር ጋር በመንፈስ ከተገናኘን የእግዚአብሔር መልክ ይሳልብናል። እርሱን እናንጸባርቃለን። ለእኛ ላይታወቀን ይችላል። የሚያዩን ግን ያውቃሉ።

በአዲስ ኪዳን፡- ፫ ቱ ሐዋርያት- በደብረ ታቦር

በፊታቸውም ተለወጠ፥ ፊቱም እንደ ፀሐይ በራ፥ ልብሱም እንደ ብርሃን ነጭ ሆነ።

እነሆም፥ ሙሴና ኤልያስ ከእርሱ ጋር ሲነጋገሩ ታዩአቸው። ጴጥሮስም መልሶ ኢየሱስን። ጌታ ሆይ፥ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው፤ ብትወድስ፥ በዚህ ሦስት ዳስ አንዱን ለአንተ አንዱንም ለሙሴ አንዱንም ለኤልያስ እንሥራ አለ።….  ማቴ ፲፯፣ ፩ - ፰

-      በእግዚአብሔር መልክ - በእርሱ ፊት መኖርን የመሰለ መልካም ነገር የለም።

ለአሕዛብ ሐዋርያ ሳውል - ጳውሎስ

ሲሄድም ወደ ደማስቆ በቀረበ ጊዜ ድንገት በእርሱ ዙሪያ ከሰማይ ብርሃን አንጸባረቀ፤

በምድርም ላይ ወድቆ ሳለ። ሳውል ሳውል፥ ስለ ምን ታሳድደኛለህ? የሚለውን ድምፅ ሰማ።… የሐዋ ፱፣ ፩ - ፰

-      ጌታን ፊት ለፊት በብርሃን መልክ አየው። በቀን በቀትር ስለሆነ ያየው ጌታ ከፀሐይ ብርሃን ይበልጥ አብርቷል ማለት ነው። /የሐዋ ፳፪፣፮/


፬. የእግዚአብሔር መልክ - በክርስቶስ ተመለሰልን።

እኛም ሁላችን በመጋረጃ በማይከደን ፊት የጌታን ክብር እንደ መስተዋት እያብለጨለጭን መንፈስ ከሚሆን ጌታ እንደሚደረግ ያን መልክ እንመስል ዘንድ ከክብር ወደ ክብር እንለወጣለን።  ፪ ቆሮ ፫፣ ፲፰።

አዳም ከበደለ በኋላ በራሱ መልክ ልጅን ሲወልድ ይሄ በኃጢአት ማንነት የወደቀ የሰው ዘር በመጽሐፍ ቅዱስ - አሮጌ ሰው ተብሏል። አስወግዱት ተብለናል።

ዕውቀት

እርስ በርሳችሁ ውሸት አትነጋገሩ፥ አሮጌውን ሰው ከሥራው ጋር ገፋችሁታልና፥

የፈጠረውንም ምሳሌ እንዲመስል እውቀትን ለማግኘት የሚታደሰውን አዲሱን ሰው ለብሳችሁታል።   ቆላ ፫፣ ፱ - ፲

ጽድቅ ቅድስና

 ፊተኛ ኑሮአችሁን እያሰባችሁ እንደሚያታልል ምኞት የሚጠፋውን አሮጌውን ሰው አስወግዱ፥

በአእምሮአችሁም መንፈስ ታደሱ፥ለእውነትም በሚሆኑ ጽድቅና ቅድስና እንደ እግዚአብሔር ምሳሌ የተፈጠረውን አዲሱን ሰው ልበሱ።.  ኤፌ ፬፣ ፳ - ፳፬

የተፈጥሮ መልካችን የሚመለሰው - እግዚአብሔርን መምሰል የምንችለው - በክርስቶስ - ነው።

ልጁ በብዙ ወንድሞች መካከል በኵር ይሆን ዘንድ፥ አስቀድሞ ያወቃቸው የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ደግሞ ወስኖአልና፤   ሮሜ ፰፣ ፳፱

-      እግዚአብሔር ዓለም ሳይፈጠር አስቀድሞ የወሰነው - በመልኩ የፈጠረው/የሚፈጥረው/ ሰው ያን መልክ በኃጢአት እንደሚያጣው ስላወቀ- በልጁ መልኩ /የሰው/ እንዲመለስለት ማቀዱ ነው።

በተፈጥሮ /በመፈጠር/ ያገኘነውን እና በኃጢአት ያጣነውን መልክ የሚመለስልን በጥረታችን ሳይሆን በመወለድ ነው። - በመንፈስ ዳግም በመወለድ።

-      ልጅ አባቱን ይመስላል፣ ይህም በሌላ ነገር፡ በሥራ…ሳይሆን በመወለድ ነው።

-      እኛም በክርስቶስ ስናምን ከመንፈስ ቅዱስ ዳግም እንወለዳልን። እግዚአብሔርንም እንመስላለን። - እግዚአብሔርን መምሰል ከእኛ ከልጅ ይጠበቃል።

-      እግዚአብሔርን መምሰል - በሕይወታችን በኑሯችን ይንጸባረቃል።

o   ዕውቀት፡- እግዚአብሔርን ማወቅ፡- ዮሐ ፲፯፣ ፬ እግዚአብሔር በልጁ የሰጠን የዘላለም ሕይወት እርሱን ማወቅ ነው።- መገናኘት

o   ጽድቅ፡- ኃጢአታችን በክርስቶስ የመስቀል ዋጋ ስለተከፈለ እኛ ነጻ ነን።

አሁንም ለምንሠራው ኃጢአት ንስሐ ስንገባ -በደሙ ስርየት እናገኛለን።

o   ቅድስና፡- ከኃጢአት የተለየ ሕይወት መለማመድ። ከክፉ ሥራ ለመራቅ በመልካም ሥራ መጠመድ፡፡ መንፈስ ቅዱስ በውስጣችን ፍሬዎቹን ያፈራል።
--------------ይቀጥላል----------------------------------------
ዲ/ን ኢንጅነር አብርሃም አብደላ
መስከረም ፮፣ ፳፻፲ ዓ/ም- አዲስ አበባ

No comments:

Post a Comment

አስተያየትዎን ይስጡ / Give Comment