Sunday, September 3, 2017

እግዚአብሔርን ማወቅ - ክፍል ፲


፬. የእግዚአብሔር መልክ


እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው።  ዘፍ ፩፣ ፳፯

መልክ፡- ሲባል የማይታየውን የሰውን ረቂቅ ማንነት /መንፈስ/ ለማመልከት ነው።

፩. የእግዚአብሔር መልክ በሰው፡ በ፫ መልክ ይታያል፤

፩. በነፍሱ፡  እግዚአብሔር ሰውን በመልኩና በአምሳሉ ሲፈጥረው ማንኛችንን ነው የሚመስለው? የሰው መልክ የተለያየ ነው። ጥቁሮች፣ ነጮች፣ ቀዮች፣….

ü በሰው ላይ ያረፈው መልክ በሥጋ ሳይሆን በነፍስ። ሥጋ ከአፈር ነው። ነፍስ ከእግዚአብሔር እስትንፋስ ናት። የእርሱን ነገሮች በተመጠነ ሁኔታ ወደ እኛ አሳርፏል።

o   ሰው ሥጋ ብቻ ሳይሆን ረቂቅ ማንነት አለው። መንፈሱ- በነፍሱ ያገኛት ናት።

o   የነፍስ ባሕርያት፡፫ - አሳቢነት፣ ተናጋሪነት፣ ዘላለማዊነት፡- ይህም አብ፣ ወልድ፣ መንፈስቅዱስ፣ አንጻር የሚታዩ ናቸው፤  እግዚአብሔር ሦስትነት አለው፤ ሥላሴ። ሥላሴ በአብ ልብነት ያስባሉ፤ በወልድ ቃልነት ይናገራሉ፤ በመንፈስ ቅዱስ ሕይወት ይኖራሉ፤

o    ስለዚህ ነፍስ፡- ከእንስሳት የምንለይበት፣ እግዚአብሔርን የምንመስልበት ነው።

፪. በኑሮ/በአኗኗሩ፡  ሰው ዘላለማዊ ሆኖ ሲኖር - ፫ መገለጫዎች አሉት።

ü ፩. ዕውቀት፡- ከራሱ ጋር ያለውን ግንኙነት ያሳያል፣ በዚህ ውስጥ፡- የመምረጥ የመወሰን፣ የማድረግ/መሥራት/ ነጻነት አለን፤…ባወቅነው/በገባን ጉዳይ ላይ ምላሽ እንሰጣለን ይህም ስሜት ይባላል፤ በመጨረሻ ባወቅነው ነገር ተንተርሰን በጉዳዩ ላይ ፈቃዳችን እንገልጻለን። ይህም ውሳኔ ይባላል።

ü ፪. ቅድስና፡- ከሌላው ጋር ያለውን ግንኙነት ያሳያል።- በዚህ ውስጥ፣ ያለኃጢአት / ያለበደል/ በሰላም መኖር፣ ኅብረት፣ሌላውን የመፈለግ /የመርዳት/ ነገሮች ይገለጻሉ።

ü ፫. ጽድቅ፡- ከእግዚአብሔር ጋር ያለውን ግንኙነት ያሳያል፡- በዚህ ውስጥ ያለኃጢአት ከአምላክ ጋር የመኖር፣ አምክን የመፈለግ፣ የመታመን /ተስፋ የማድረግ ሁኔታዎች አሉ።


፫.  በሥልጣን፡-  መግዛት ፣ ማስተዳደር - በሁለት ጉዳዮች፡

ü ራሱን እንዲገዛ

ü ዓለምን / ተፈጥሮን እንዲገዛ

የእግዚአብሔር መልክ ሲባል መንፈሳዊ /ረቂቅ / የሆነ ጉዳይ ነው፡ እግዚአብሔርን መምሰል ነው።

ሰው በነፍሱ በተሰጠው ነጻነት በእግዚአብሔት ላይ በማመጹ - መልካም ብቻ የሚያውቅ እና የሚኖር የነበረው ክፉንም አወቀ። - በውስጡ የነበረውን የእግዚአብሔር መልክ አጣ።

ስለዚህ የራሱን መልክ ያዘ፣ ክፉና ደግ ያለበት። ይህንም ለትውልድ አስተላለፈ፡፡ በእግዚአብሔር መልክ ተፈጥሮ ሲኖር የነበረው አዳም ከበደለ በኋላ ልጅን በመልኩ ወለደ።

አዳምም ሁለት መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፥ ልጅንም በምሳሌው እንደ መልኩ ወለደ… ዘፍ ፭፣ ፫።

ስለዚህ የአዳም በኃጢአት የወደቀ ማንነት /መልክ/ በሰው ዘር ሲተላለፍ ኖረ። ይህን በአዳም በኃጢአት ያጣናቸውን ኋላ በክርስቶስ ተመልሰውልናል። - እግዚአብሔርን መምሰል።

፪. ከውድቀት በኋላ የእንስሳት መልክ

የማይጠፋውንም የእግዚአብሔር ክብር በሚጠፋ ሰውና በወፎች አራት እግር ባላቸውም በሚንቀሳቀሱትም መልክ መስለው ለወጡ።   ሮሜ ፩፣ ፳፫

-      ሰው ከውድቀት በኋላ የእግዚአብሔርን መልክ /ክብር/ ሲያጣ የራሱን መልክ ያዘ - በሚጠፋ ሰው።

-      ከዚህ የሚብሰው ግን የእንስሳትን መልክ መያዛችን ነው።  አራት እግር ባላቸው በሚንቀሳቀሱትም..

o   እንስሳዊ ባሕርይ፡- ገደብ ማጣት፣ ልቅ መሆን፣ መብላት-መብላት፣ መተኛት፣ ብቻ….

፫. ከውድቀትም በኋላ ያልጠፉ የእግዚአብሔር መልክ

መገለጫዎች- ሦስቱ የነፍስ ባሕርያት፡- 

፩. አሳቢነት- በነፍሳችን ከሌሎች ሕይወት ካላቸው የምንለይበት - አሳቢነት- ነው።

፪. ተናጋሪነት፡- ቋንቋ፣ መግባባት፣ ከመሰሎቻችን ጋር በውይይት መገናኘት…

፫. ሕያውነት፡- ዘላለማዊ ነን።

ከነዚህ በተጨማሪ፡-

፬. አቅዶ - መሥራት፡- እግዚአብሔር ፈጣሪ ነው። ሁሉን አስገኝቷል። ሰውም በተሰጠው አሳቢ አእምሮ ካሉት ፍጥረታት - ብዙ ነገሮችን አስገኝቷል። - የምናየው ቁሳቁስ፣ ተክኖሎጂ፣ ኮምፒውተር…

፭. መንፈስ - ሰው የምንለው ሥጋ /ቁሳዊ/ ብቻ አይደለም። ከዚያ ያለፈ ማንነት አለን። መንፈሳዊነት። ይህም መንፈስ ከሆነው ከእግዚአብሔር የተካፈልነው ተፈጥሯዊ መልክ ነው።

፮. ማመዛዘን፡- ክፉና ደጉን መለየት- ሰው ቢማርም ባይማርም፣ እግዚአብሔርን ቢያውቅም ባያውቅም፣ በውስጡ የሕሊና ሚዛን /ዳኝነት/ ተቀምጦለታል፤ የዚህ መገለጫው ክፉ ስንሰራ የሕሊና ወቀሳ፣ መልካም ስንሠራ የሕሊና እርካታ አለ፤ ሕሊና የእግዚአብሔር ወኪል ነውና፤

እነዚህ ሰው በኃጢአት ከወደቀ ባኋላ ጨርሰው ያልጠፉ የእግዚአብሔር መልክ ናቸው፤ ….

……………ይቀጥላል……………

ዲ/ን ኢንጅነር አብርሃም አብደላ

ነሐሴ ፳፰፣ ፳፻፱ ዓ/ም - አዲስ አበባ

No comments:

Post a Comment

አስተያየትዎን ይስጡ / Give Comment