Wednesday, August 16, 2017

እግዚአብሔርን ማወቅ - ክፍል ፱

/የእግዚአብሔር ስም - ቀጣይ/

Ø የእግዚአብሔር ወዳጆች እግዚአብሔር ካደረገላቸው ነገር ጋር በማያያዝ ለልጆቻቸው ስም ያወጡ ነበር።

ምናሴ - ማስረሻ፡- አባቱ ዮሴፍ መከራየን የአባቴን ቤት አስረሳኝ ሲል። ዘፍ ፵፩፣፶፩

ሳሙኤል - እግዚአብሔር ሰማ - መካኒቱ ሐና ጸሎቷን ስለሰማ ልጅ ስለሰጣት፡      ፩ ሳሙ ፩፣ ፳

o   ዛሬ የእኛ ስም አወጣጥ ምን ይመስላል? - የእግዚአብሔር ወገን መሆናችንን የሚያሳይ ነው?.. ስሞቻችንን ብንፈትሻቸው፡

-      ቦግ አለ፣ ዱብ አለ።  - ኩራባቸው፣ ሰጥአርጋቸው፣

Ø ቦታዎችንም ከእግዚአብሔር ጋር በማያያዝ ይሰይሙ ነበር።

o   አጋር ከሣራ ተሰዳ ስትወጣ እግዚአብሔር አገኛት - በመልአኩ፡
እርስዋም ይናገራት የነበረውን የእግዚአብሔርን ስም ኤልሮኢ ብላ ጠራች የሚያየኝን በውኑ እዚህ ደግሞ አየሁትን? ብላለችና። ስለዚህም የዚያ ጕድጓድ ስም ብኤርለሃይሮኢ ተብሎ ተጠራ፡  ዘፍ ፲፮፣ ፲፫ - ፲፬

Ø እግዚአብሔር የወዳጆቹን ስም ይለውጣል።

- አብራም /ታላቅ አባት/ - አብርሃም /የብዙዎች አባት/…

- ያዕቆብ /አሰናካይ -ተረከዝ የሚይዝ (ሲወለዱ የኤሳውን እግር ይዞ ስለነበር ወላጆቹ ያወጡለት

እግዚአብሔር ግን - እስራኤል - አለው፡- እግዚአብሔር ያሸንፋል ማለት ነው።
ወዳጆቹ ወደፊት የሚሆኑትን በማየት ሕይወታቸውን ለመለወጥ ስማቸውን ከመለወጥ ይጀምራል።
እኛም ዛሬ በወል ስም -በክርስቶስ - ክርስቲያን የተባልነው- ከስማችን ጀምሮ ሕይወታችን እንዲለወጥ የክርስቶስን ፈለግ በመከተል እርሱን ወደ መምሰል እንድናድግ ነው።

የእግዚአብሔር ስም ለእኛ ምን ያስተምረናል?
Ø ይመልስልናል፡-  በስማችን ስንጠራ - አቤት- ብለን መልስ እንሰጣለን። በስም መጥራት የግንኙነቶች መጀመሪያ /ትውውቅ/ ፣ የሥራ መጀመሪያ ነው። ከጠራን በኋላ ወደ ጉዳያችን እንገባለን።

o   እግዚአብሔር ስም ያለው መሆኑ እንድንጠራው ያስችለናል። እርሱም  እንደሚመልስልን ማረጋገጫ ነው።

o   ጆሮ እያለው በስሙ ተጠርቶ የማይመልስ የለም። - ጆሮን የፈጠረ አምላክ ይሰማል

Ø ግንኙነትን ያመለክታል አጠራራችን ግንኙነታችንን ያመለክታል። ስሞቹ የትኛውን እንደምንጠቀም የሚያሳየው ቅርበታችንን ነው፤

o   ለምሳሌ እኔ ስጠራ፡-

§  አቶ አብርሃም / ጋሼ አብርሃም ብሎ የሚጠራኝ - የሥራ ግንኙነትን ያሳያል፤ በክብር በሩቁ የምጠራበት ነው ፡፡

§  አብርሽ - የወዳጅ መጥሪያ ነው- ቅርበትን ያሳያል፤

§  ባባ - የአባትና የልጅ..የበለጠ ቅርበትን ያሳያል።

o   እግዚአብሔርን ስንጠራው የትኛውን እንጠቀማለን። እግዚአብሔር  የሚለው በተፈጥሮ ሁሉም እርሱን የሚጠራበት - የአክብሮት -የጌትነቱ-የፈጣሪነቱ ነው። ለእኛ ግን ከዚያም በላይ ነው። በሩቁ የምናከብረው ብቻ አይደለም። ቅርብ ነው- አባታችን ስለሆነ፤

ጌታ ስትጸልዩ፡- አባታችን ሆይ - በሉ  አለ

አባ አባት ብለን የምንጮኽበትን የልጅነት መንፈስ ተቀበላችሁ እንጂ እንደገና ለፍርሃት የባርነትን መንፈስ አልተቀበላችሁምና።   ሮሜ ፰፣ ፲፭።

አባ፣ አባት፡- የልጅነት - የቅርበት ስለሆነ- በዚህ እንድንጠራው ይፈልጋል።

Ø በከንቱ አይጠራም፡ -  ስም መጠሪያ ቢሆንም በትንሹ በትልቁ መጥራት የለብንም። ከ፲ቱ ትዕዛዛት አንዱ ሆኖ መሰጠቱ ይገርማል። ለስሙ ምን ያህል እንደሚጠነቀቅ/ እኛም እንድንጠነቀቅ በቋሚነት በ፲ቱ ትእዛዛት ተካተተ።

የእግዚአብሔርን የአምላክህን ስም በከንቱ አትጥራ እግዚአብሔር ስሙን በከንቱ የሚጠራውን ከበደል አያነጻውምና።   ዘጸ ፳፣ ፯ፀ ስሙን በከንቱ መጥራት -ማለት

o   ያለቦታው መጥራት - እግዚአብሔርን ለጥፋት ተባባሪ ማድረግ

o   ስሙን ማሰደብ፡- የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን በማይሆን ቦታ/ በኃጢአት/ ብንገኝ የሚሰደበው እግዚአብሔር ነው። 


Ø መጠጊያ - የጸና ግንብ ተብሏል። -

o   የእግዚአብሔር ስም የጸና ግምብ ነው ጻድቅ ወደ እርሱ ሮጦ ከፍ ከፍ ይላል።  ምሳ ፲፰፣ ፲

o   ጻድቅ ሮጦ - የሚጠጋበት ፣ ከዚያም የሚከብርበት ነው።

o   ስሙ መጠጊያ ነው፤-ከፀሐይ፡ ከዝናብ.. እንደምንጠጋው። እረፍት በእርሱ ነው፡፡

Ø መድኃኒት -

o   እንዲህም ይሆናል የእግዚአብሔር ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል እግዚአብሔርም እንደ ተናገረ፥ በጽዮን ተራራና በኢየሩሳሌም መድኃኒት ይገኛል።   ኢዩ ፪፣ ፴፪

o   የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናልና።   ሮሜ ፲፣ ፲፫

o   ስሙን መጥራት ማለት - ግንኙነትን የሚያሳይ ነው። ስላወቀን/ስላወቅነው ነው።
በአጠቃላይ የእግዚአብሔር ስም፡-

o   ስለ እግዚአብሔር ማንነት እንድናውቅ ያደርገናል።

o   እንደስሙ እንደሚሠራ ያረጋግጥልናል። ሰዎች እንደስማቸው ላይሆኑ ይችላሉ። ትዕግስት - ተብለው ትዕግስት የሌላቸው ሊሆኑ ይችላሉ። እግዚአብሔር ግን እንደስሙ ይሠራል።/ ያደርጋል።

o   እንድንታመንበት ይረዳናል።

Ø የስሙ ኃይል ተግባራዊ መገለጫ - ኢየሱስ

o   ጌታ ሲወለድ መጠሪያው፡-

§  ኢየሱስ - አዳኝ - በኃጢአት ስለጠፋን ያዳነን መድኃኒት /ማቴ ፩፣ ፳፩/

§  አማኑኤል - እግዚአብሔር ከእኛ ጋር - በኃጢአት ከእርሱ ርቀን ስለነበር እርሱ እኛን ፈልጎ መጣ፣ - ከእኛ ጋር ሆነ።  /ማቴ ፩፣ ፳፫/

o   ለእኛም ስሙ የወል መጠሪያችን ሆኗል፤ - ክርስቶስ - ክርስቲያን በእንግሊዝኛው  Christ – Christian – /adjective/ -  የክርስቶስ።

§  ክርስቲያን የሚለው የወል ስማችን የክርስቶስ መሆናችንን ያመለክታል፡፡ በእኛ ላይ ባለቤት ነውና፣ በመፍጠርና በማዳን። ስለዚህ ባለቤት ካለን በእርሱ እና ለእርሱ ልንኖር ይገባል።

o   ከስም ሁሉ በላይ የሆነ - ሁሉ የሚንበረከክለት ስም

ከስምም ሁሉ በላይ ያለውን ስም ሰጠው፤ይህም በሰማይ በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ፥… ነው።  ፊልጵ ፪፣ ፱ - ፲

§   በሰዎች ምስጋና እና ልመና፣ ለአጋንንት ውጊያ የሚጠራ፣

o   ልመና ወደ እግዚአብሔር የሚቀርብበት

እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ አብ በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ ይሰጣችኋል። እስከ አሁን በስሜ ምንም አልለመናችሁም፤ ደስታችሁ ፍጹም እንዲሆን ለምኑ ትቀበሉማላችሁ።   ዮሐ ፲፮፣  ፳፫ - ፳፬።

o   ምስጋና ወደ እግዚአብሔር የሚደርስበት

ሁልጊዜ ስለ ሁሉ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አምላካችንንና አባታችንን ስለ ሁሉ አመስግኑ።   ኤፌ ፭፣ ፳

o   ሁሉ የሚደረግበት

እግዚአብሔር አብን በእርሱ እያመሰገናችሁ፥ በቃል ቢሆን ወይም በሥራ የምታደርጉትን ሁሉ በጌታ በኢየሱስ ስም አድርጉት።  ቆላ ፫፣ ፲፯

o   ስለስሙ መነቀፍ ደስታ ነው።

እነርሱም ስለ ስሙ ይናቁ ዘንድ የተገባቸው ሆነው ስለ ተቈጠሩ ከሸንጎው ፊት ደስ እያላቸው ወጡ፤   የሐዋ ፭፣ ፵፩

§  በስሙ መናቅን ካገኘነው - የተገባቸው ሆነው ስለተቆጠሩ - ዕድል ነው።

§  ስሙን ስለጠራን፣ ስላስተማርን፣ ስለመሰከርን፣ ስላከበርን ማለት ነው።

§  ስሙ ለጠላት ቁጣን ፣ ለእኛ ለልጆቹ ግን ደስታን ያመጣል።

o   በስሙ አለማመን ፍርድን ያስከትላል።

በእርሱ በሚያምን አይፈረድበትም፤ በማያምን ግን በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ስላላመነ አሁን ተፈርዶበታል።   ፩ ዮሐ ፫፣ ፲፰

§  በስሙ አለማመን ማለት ስሙ የሚገልጠውን ማንነቱን፣ ሥራውን፣ ባሕርይውን፣ ኃይሉን…አለማመን ማለት ነውና

o   ስሙ ከፍተኛ ኃይል ስላለው አጋንንትን የምንዋጋበት ብቸኛው መንገድ ነው።

§  ያመኑትንም እነዚህ ምልክቶች ይከተሉአቸዋል፤ በስሜ አጋንንትን ያወጣሉ፤ በአዲስ ቋንቋ ይናገራሉ፤ እባቦችን ይይዛሉ፥

….. ወዘተ…. ከስሙ ጋር የተያያዙ ብዙ ነገሮች ናቸው።

o   ስምህ ይቀደስ፣ ስለስሙ መመስከር፣ …..

ኢየሱስ - ስሙን አንፍራው። እንደሌሎች በትንሽ በትልቁ ሳይሆን በክብር እንጥራው።

የጌታ መሆናችን ዋናው መገለጫው ይህ ነውና-

ጌታ ለእርሱ የሆኑትን ያውቃል፥ ደግሞም፦ የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ከዓመፅ ይራቅ የሚለው ማኅተም ያለበት የተደላደለ የእግዚአብሔር መሠረት ቆሞአል።  ፪ ጢሞ ፪፣ ፲፱።

-      እግዚአብሔር የዓለማት አስገኚ ጌታ ባለቤት ነው። - በተፈጥሮ

-      በልጁ በማመን በማዳን ደግሞ እያንዳንዱ በፈቃዱ እኔ የጌታ ነኝ ይላል።

-      የጌታ የምሆነው የጌታ ነኝ ብየ በአፍ ስለተናገርኩ አይደለም። በስም ክርስቲያን ነኝ ስላልኩም አይደለም፤ ስለእርሱ ስላወራሁ፣ ስለመሰከርኩ… አይደለም።

 -- ጌታ ለእርሱ የሆኑትን (እርሱ) ያውቃል

-      የጌታ መሆናችን ማረጋገጫው - ማኅተም ያለበት የተደላለደ መሠረት - ስሙን የሚጠራ ከአመጽ ይራቅ  የሚለው  በተግባር የምንኖረው የቅድስና ሕይወት ነው።
……………ይቀጥላል……………
ዲ/ን ኢንጅነር አብርሃም አብደላ
ነሐሴ ፲/ ፳፻፱ ዓ/ም - ጎንደር

No comments:

Post a Comment

አስተያየትዎን ይስጡ / Give Comment