Wednesday, October 4, 2017

እግዚአብሔርን ማወቅ - ክፍል ፲፪


የእግዚአብሔር ሥራ


ለሚጠፋ መብል አትሥሩ ነገር ግን ለዘላለም ሕይወት ለሚኖር መብል የሰው ልጅ ለሚሰጣችሁ ሥሩ፤ እርሱን እግዚአብሔር አብ አትሞታልና። እንግዲህ። የእግዚአብሔርን ሥራ እንድንሠራ ምን እናድርግ? አሉት። ኢየሱስ መልሶ፦ ይህ የእግዚአብሔር ሥራ እርሱ በላከው እንድታምኑ ነው አላቸው።    ዮሐ 6፣ 27 – 29

-      ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሕዝቡ እንጀራና አሳ አበርክቶ ስለሰጣቸው - ለዚያ ሲሉ ነበር የተከተሉት። ለዚህ መልስ ሲሰጣቸው - ለሚጠፋ መብል አትሥሩ፡፡ የምትከተሉኝ ለምን ዓላማ ነው?

እንደ ክርስቲያን /የክርስቶስ ተከታዮች/ በዚች ምድር የመኖራችን ዓላማ ምንድን ነው? ብንል መልሱ የእግዚአብሔርን ሥራ እንድንሠራ ነው።

-      እርሱን እግዚአብሔር አብ አትሞታል፡- ወልድ የአብ ልጅ ነው። አብን መስሎ፣ አብን አክሎ የተገኘ፣ - ማኅተም፡- ሲደረግ ቅርጹ በወረቀቱ ላይ በትክክል ያርፋል። የአብን ማንነት በሥጋ /በሰው/ ታትሞ ያየነው በክርስቶስ ነው። - ወልድ ሰው ሲሆን አብ አትሞታል። የምወደው ልጄ ይህ ነው ብሎ ማረጋገጫ /ማኅተም/ አድርጎበታል።

-      ስለዚህ በክርስቶስ የሆነውን ማንኛውም መንፈሳዊ ሥራ እግዚአብሔር ከእኔ ነው ብሎ እውቅና /ማረጋገጫ / ይሰጠዋል- ማለት ነው።


የእግዚአብሔርን ሥራ እንድንሠራ ነው። -ይህ የእግዚአብሔር ሥራ ምንድን ነው?

የእግዚአብሔርን ሥራ እንድንሠራ ምን እናድርግ? - የሚለው ተገቢ ጥያቄ ነው።

-      በራሳችን እንደሚመስለን - እርሱን ደስ የሚያሰኙ ጥሩ ጥሩ ነገሮችን ማድረግ። ጾም፣ ጸሎት፣ መጽሐፍ ቅዱስ ማንበብ፣ ጥሩ ሰው መሆን፣….የእኛ ድርጊቶች።

ክርስቶስ ግን ለዚህ ጥያቄ የሰጠው መልስ፡- አጭር፣ ግልጽ፣ ቀላል ነው።

-      እርሱ በላከው እንድታምኑ። - በክርስቶስ ማመን። --- ምንም ጥረት አይጠይቅም። ድርጊት/እንቅስቃሴ /ውጣ ውረድ የለበትም። - በቃ፤ በልብ ማመን- መቀበል።

-      ማመን፡- ለመዳን ከዚያም ለማዳን።  የሚሠራው እርሱ ነው።……

የእግዚአብሔር ሥራ ከመጀመሪያው፡-  ዓለምን መፍጠር።

እግዚአብሔር ዓለምን የመፍጠር ስራውን ጨርሶ - አረፈ- ተብሏል።  ከዛ በኋላ ምን ይሠራል? ቦዘኔ ነው? ምን እያደረገ ነው ያለው በአሁኑ ሰአት?.

ከሠራው ሥራ ሁሉ አረፈ…ይላል፤ ያረፈው ከመፍጠር ነው፤ /ዘፍ ፪፣ ፪-፫/

ይህም ማለት አዲስ ነገርን ከማስገኘት። እንጂ ሥራ ፈታ ማለት አይደለም።

በመላው ፍጥረት ላይ ያለው ቀጣይ ሥራው ማስተዳደር፣ መጠበቅ፣ መመገብ ነው።

-      እግዚአብሔር ፍጥረታትን ለመመገብ ምን ይሠራል? - ወዲያ- ወዲህ ሽር ጉድ .. ይላል? በዚህ ዘመን የሚኖሩትን 6.7 ቢሊየን ሕዝብ እንደ አንድ ሰው ይመግባል፣ ስፍር ቁጥር የሌላቸውን እንስሳት፣ አራዊት፣ አእዋፋት… ይመግባል፣ ያስተዳድራል። እንዴት?

-      ሥርዓት /ሲስተም/ በመዘርጋት ነው። አንዱ አንዱን እንዲመግብ - የዝናብ፣ የፀሐይ፣ የነፋስ… ሥርዓት። የእጽዋት፣ የእንስሳት አመጋገብ ሥርዓት..ወዘተ…

በሰዎች ላይ ያለው ዋናው ስራ ማዳን ነው። በዚህ ጉዳይ እስከዛሬ ይሠራል። ምክንያቱም

o   ሰዎች ከመበደል ስላላረፉ፣ እርሱም ከማዳን አላረፈም።

o   በአሁኑ ሰአት የእግዚአብሔር ዋና የማያቋርጥ ሥራ ምንድን ነው? - ማዳን ነው።

፩. እግዚአብሔር በምን? - በቃሉ ይሠራል።

-      መፍጠር፡- እግዚአብሔር ዓለምን በቃሉ ፈጠረ፣

እግዚአብሔር ይህን ግዙፍ/ረቂቅ ድንቅ ዓለም ለመፍጠር ቃሉ በቂ ነበርና

በእግዚአብሔር ቃል ሰማዮች ጸኑ፥ ሠራዊታቸውም ሁሉ በአፉ እስትንፋስ፤   መዝ ፴፫፣፮

-      ማዳን፡- በአካላዊ ቃሉ በወልድ - በኢየሱስ ክርስቶስ ዓለምን አዳነ።

-      የጠፋውን የሰውን ልጅ ቃሉ ሥጋን ለብሶ - ሰው ሆኖ - ተሰቅሎ አዳነን፤

    ቃልም ሥጋ ሆነ፤ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ አደረ፥    ዮሐ ፩፣ ፲፬

ቃል - ወልድ ሥጋን ከለበሰ በኋላ - የእግዚአብሔርን ሥራ ሲሠራ ኖረ፤

       ኢየሱስ ግን፦ አባቴ እስከ ዛሬ ይሠራል እኔም ደግሞ እሠራለሁ ብሎ መለሰላቸው።  ዮሐ ፭፣ ፲፯

n ይህን የተናገረው ፴፰ ዓመት በአልጋ ተኝቶ የነበረውን ሰው ከፈወሰ /ካዳነ በኋላ ነው።

አባቴ ይሠራል፣ እኔም እሠራለሁ - ያለው ማዳንን ነው። - ሥጋዊ ደኅንነት።

n ዋናው ትልቁ ሥራው - ስለእኛ በመስቀል ላይ ቤዛ ሆኖ መሞት ነው።

እኔ ላደርገው የሰጠኸኝን ሥራ ፈጽሜ በምድር አከበርሁህ፤   ዮሐ ፲፯፣ ፬

n ክርስቶስ በመስቀል ላይ ሰውን የማዳን ሥራውን አጠናቋል። ጨርሷል።

ሁሉ ተፈጸመ። - ሥራው ያለቀ ነው።

ሰዎች ይህን የተፈጸመ ሥራ እንዲቀበሉ /እንዲያምኑ/ መናገር ማወጅ ብቻ ነው የሚጠበቀው፤ ይህም በሐዋርያት ተጀምሮ - ዛሬም በአገልጋዮች /በእኛ/ ይቀጥላል።

n በእግዚአብሔር የማዳን ሥራ ውስጥ የሰው ድርሻ ምንድን ነው?/ ስንት % ነው?

ማመን ብቻ። በክርስቶስ የተሠራውን / የተፈጸመውን የመስቀል ሥራ መቀበል።

ስለዚህ የሰው ድርሻ ስንት % ነው? -- ምንም።  0 %. ::

መፈጠራችን / መወለዳችን ያለእኛ አንዳች አስተዋጽኦ ሙሉ በሙሉ እንደተከናወነ፡- መዳናችንም እንዲሁ ሙሉ በሙሉ በእርሱ የተፈጸመ ነው።

የማዳኑን ስራ መቀበል - በእርሱ የማዳን ሥራ ውስጥ ድርሻ ማስቀመጥ አይደለም። መቀበሉ፣ ማመኑ ለራሳችን መዳን ነው።

ማዳን የእግዚአብሔር ነው፥  መዝ ፫፣ ፰ ፤…..የሰውም ማዳን ከንቱ ነው። መዝ ፻፰፣ ፲፪

ስለዚህ፡-

ማዳን በማይችሉ በሰው ልጆችና በአለቆች አትታመኑ። መዝ ፻፵፮፣ ፫

ይልቅስ፡-

ሰው ዝም ብሎ የእግዚአብሔርን ማዳን ተስፋ ቢያደርግ መልካም ነው።  ሰቆ ፫፣ ፳፮

……………ይቀጥላል……………

ዲ/ን ኢንጅነር አብርሃም አብደላ

መስከረም ፳፫፣ ፳፻፲ ዓ/ም - ጎንደር

No comments:

Post a Comment

አስተያየትዎን ይስጡ / Give Comment