Wednesday, October 24, 2018

መጽሐፍ ቅዱሳዊ የመዳን አስተምህሮ


 ·        ሁሉም ሰው ኃጢአተኛ ነው።
o   ሁሉም በክርስቶስ ከማመኑ በፊት ኃጢአተኛ ነው
ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል፤ ሮሜ ፫፣ ፳፫
- ከዚህ ኃጢአት /እና ሞት/ መዳን አለብን፤ መድኃኒቱም ኢየሱስ ነው፤
እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ።  ማቴ ፩፣ ፳፩

o   በክርስቶስ ካመንን በኋላም እንኳ ኃጢአት ይኖርብናል - ባልዳነ ሥጋ ባልዳነች ዓለም ስለምንኖር
ኃጢአት የለብንም ብንል ራሳችንን እናስታለን፥ እውነትም በእኛ ውስጥ የለም።
ዮሐ ፩፣
- ከዚህ ኃጢአት መንጻት አለብን፤ /ከዳንን በኋላ በየጊዜው ስለምንቆሽሽ/
የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል።  ዮሐ ፩፣

·        ሁሉም የሚድነው በክርስቶስ በማመን ብቻ ነው።
በልጁ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤  ዮሐ ፫፣ ፴፮
·        ሌላ መድኃኒት የለም
መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና።  የሐዋ ፬፣ ፲፪
·        አምነን መዳናችንን የምረጋግጠው አሁን ነው።
እንግዲህ በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት አሁን ኵነኔ የለባቸውም። ሮሜ ፰፣
·        ካላመንንም ፍርዱ አሁን ነው።
በእርሱ በሚያምን አይፈረድበትም፤ በማያምን ግን በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ስላላመነ አሁን ተፈርዶበታል።። ሮሜ ፰፣


·        ማመን ማለት ስለክርስቶስ መረጃ እና እውቀት መያዝ ሳይሆን የክርስቶን አዳኝነት ከውስጥ መቀበል ነው። ይህም እምነት ከልብ የሆነ እና የተፈተነ  ሊሆን ይገባል፡፡
- በሃይማኖት ብትኖሩ ራሳችሁን መርምሩ፤ ራሳችሁን ፈትኑ ቆሮ ፲፫፣
/በሃይማኖት - ማለት በእምነት እንጂ በተቋም አይደለም፤  ያን ጊዜ ተቋም አልነበረም።/
- ነገር ግን በእሳት ምንም ቢፈተን ከሚጠፋው ወርቅ ይልቅ አብልጦ የሚከብር የተፈተነ እምነታችሁ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ፥ ለምስጋናና ለክብር ለውዳሴም ይገኝ ዘንድ አሁን ለጥቂት ጊዜ ቢያስፈልግ በልዩ ልዩ ፈተና አዝናችኋል።  ጴጥ ፩፣ -
·        በክርስቶስ አምነን ከዳንን በኋላ መልካም ሥራ እንሠራለን።
እኛ ፍጥረቱ ነንና፤ እንመላለስበት ዘንድ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጀውን መልካሙን ሥራ ለማድረግ በክርስቶስ ኢየሱስ ተፈጠርን።  ኤፌ ፪፣
/ተፈጠርን፡ ሲል- አዲስ ማንነትን ያሳያል፣ እንጂ አዲስ የሚፈጠር ነገር የለም።/
መልካም ሥራ የሕይወት መገለጫ ፍሬ ነው፡፡የሕይወት ሕግ እንደሚያሳየው ሕይወት ሳይኖር ፍሬ አይመጣም፡ - ያልጸደቀ አያፈራም፡ /ዛፍም ቢሆን/ ጽድቅ ደግሞ በክርስቶስ ነው፡፡
          በኢየሱስ ክርስቶስም በሆነው ቤዛነት በኩል እንዲያው በጸጋው ይጸድቃሉ።    ገላ ፫፤ ፳፬
 በኛ ሕይወት የሚገለጠው መንፈሳዊ ፍሬ የመንፈሳዊ ሕይወት /የመንፈስ ቅዱስ ውጤት ነው፡፡ /ገላ ፣፳፪
·        በሥራችን መጠን ክብር፣ ሽልማት፣ አክሊል፣ ዋጋ፣ ደመወዝ.. እናገኛለን።
እነሆ፥ በቶሎ እመጣለሁ፥ ለእያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን እከፍል ዘንድ ዋጋዬ ከእኔ ጋር አለ። ራእ ፳፪፣ ፲፪
·        የምንድነው በእምነት እንጂ በሥራ አይደለም።
ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤ ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም።  ኤፌ ፪፣ -
/እዚህ ሥራ የተባለው ከኛ የሆነውን ሁሉ ያካትታል፣ መልካም ሥራ፣ ጾም፣ ጸሎት፣ ስግደት..
የምንድነው በኛ ሥራ ሳይሆን ክርስቶስ በመስቀል ላይ በሠራው ታላቅ የማዳን ሥራ በማመን ነው፡፡
መዳን በኛ ሥራ ነው ካልን  ቢያንስ ሁለት ጥያቄዎችን መመለስ አለብን፡፡
1.     በሥራችን የምንድን ከሆነ የክርስቶስ ሞት ጥቅሙ ምንድን ነው?
የእግዚአብሔርን ጸጋ አልጥልም፤ ጽድቅስ በሕግ በኩል ከሆነ እንኪያስ ክርስቶስ በከንቱ ሞተ።
ኤፌ ፪፤ ፳፩
2.     ስንት መልካም ሥራ ስንሠራ ነው ለመዳን የምንበቃው?
እንደ ምሕረቱ መጠን ለአዲስ ልደት በሚሆነው መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ በመታደስ አዳነን እንጂ፥ እኛ ስላደረግነው በጽድቅ ስለ ነበረው ሥራ አይደለም፤   ቲቶ ፫፤
በክርስቶስ አምነን ከዳንን በኋላም ኃጢአት እንሠራለን፡ ነገር ግን ወደነው፣ ሆን ብለን፣ በተደጋጋሚ ሳይሆን - ሥጋችን ስላልዳነ በእርሱ ግፊት ሲሆን ይህም ድል ልናደርገው የሚገባ የሥጋ ትግል ነው፡፡ የጾምና ጸሎት ሚና እዚህ ላይ ወሳኝ ነው፡፡
በእኔ ማለት በሥጋዬ በጎ ነገር እንዳይኖር አውቃለሁና፤ ፈቃድ አለኝና፥ መልካሙን ግን ማድረግ የለኝም። የማልወደውን ክፉን ነገር አደርጋለሁና  ሮሜ ፯፣ ፲፰
·        በክርስቶስ አምነን ከዳንን በኋላም ኃጢአት ስንሠራ የምንነጻው በንስሃ- በክርስቶስ ደም ነው። ይህም ንስሐ መግባት በየጊዜው ልናደርገው የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡
በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው። ዮሐ ፩፣
የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል ዮሐ ፩፣
ለኃጢአት የተከፈለ ውድ የሕይወት ዋጋ የክርስቶስ ስለሆነ ሌላ የሚያነጻ ነገር የለም፡ ሊኖርም አይችልም፡፡
/ልብ እንበል፡-  ሊያነጻን፣ ያነጻናል - ስለመንጻት /ስንቆሽሽ/ እንጂ ስለመዳን አይደለም።/
ቢገባንም ባይገባንም የእግዚአብሔር ቃል እውነት ነው፤ ይሠራል።
ካመንንበት እና ከተቀበልነው በኛም ሕይወት ይሠራል፤ ይለውጠናል፡፡

እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ቃሌን የሚሰማ የላከኝንም የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፥ ከሞትም ወደ ሕይወት ተሻገረ እንጂ ወደ ፍርድ አይመጣም። ዮሐ ፭፣ ፳፬
---------------------------//----------------------

- / ኢንጅነር አብርሃም አብደላ
ዓርብ - መስከረም ፲፩፣ ፳፻፲፩ / - አዲስ አበባ

No comments:

Post a Comment

አስተያየትዎን ይስጡ / Give Comment