Friday, December 23, 2011

የትርጉሞች ንጽጽር

እንደ መጽሐፍ ቅዱስ በሁሉም ቋንቋዎች፡ በዘመናት ሁሉ እና በብዛት የተተረጎመ መጽሐፍ የለም። ትርጉሞች ሁለት ዓይነት ናቸው። ነጠላና አንድምታ። ነጠላ የምንለው ከቋንቋ ወደ ቋንቋ የሚተረጎም ሲሆን አንደምታ ደግሞ ከማብራሪያ ጋር በዝርዝር የሚተረጎም ነው። በዚህ ክፍል የመጽሐፍ ቅዱስን ሃሳቦች ለማግኘት እንድንችል የተለያዩ ትርጉሞችን እያነጻጸርን እናያለን። 
  ለዛሬ ለመጀመሪያ ለማነጻጸር ያህል በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በጣም ተወዳጅ የሆነውን ጥቅስ ዮሐ ፫፡፲፮  በተለያዩ ትርጉሞች እንመልከት።  በመካከላቸው ያለውን የቅርጽ ልዩነት ያስተውሉ።


« እንዲሁ እግዚአብሔር ዓለሙን ወዶታልና፡ አንድ ልጁን ቤዛ እስኪሰጥ ድረስ፡ በእርሱ ያመነ ሁሉ የዘለዓለም ሕይወት ትሆንለት ዘንድ እንጂ እንዳይጠፋ።»  አማርኛ  ፲፱፻፴፰ ዓ/ም የቀ/ኃይለ ሥላሴ የግል ቅጂ

«በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና፡» አማርኛ፡ ፲፱፻፶፬ ና ፲፱፻፹   ዓ/ም ትርጉም፡

«በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስከመስጠት ድረስ ዓለምን እንዲሁ ወዶአልና።» አማርኛ ፲፱፻፺፫ ዓ/ም አዲሱ መደበኛ ትርጉም፡


 «በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘለዓለም ሕይወትን እንዲያገኝ እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን ቤዛ አድርጎ እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲህ ወዶታልና።»                  አማርኛ  ፳፻ ዓ/ም ትርጉም፡-


“For God so loved the world that He gave His only-begotten Son, so that whoever believes in Him should not perish, but have everlasting life.”      እንግሊዝኛ (Placed by the Gideosns)

“For God so loved the world that He gave His only Son, so that everyone who believes in Him may not perish but may have eternal life.”  እንግሊዝኛ (United Bible Society 1962 G.C.)

For God so loved the world, that he gave his only begotten Son, that whosoever believeth in him should not perish, but have everlasting life.
እንግሊዝኛ (King James Version.)


Car Dieu a tant aimé le monde qu'il a donné son Fils unique, afin que quiconque croit en lui ne périsse point, mais qu'il ait la vie éternelle.               French 


«እስመ ከመዝ አፍቀሮ እግዚአብሔር ለዓለም እስከ ወልዶ ዋሕደ መጠወ፡ ወወሀበ ቤዛ ከመ ኩሉ ዘየአምን ቦቱ ኢይትሐጐል አላ ይረክብ ሕይወተ ዘለዓለም»                            ግዕዝ


«ኣምላኽ በቲ ሓደ ወዱ ዝኣመነ ዀሎ ናይ ዘለኣለም ህይወት ምእንቲ ኺረክብ እምበር ከይጠፍእሲ ንወዱ በጃ ኽሳዕ ዚህብ ክሳዕ ክንድዚ ንዓለም ኣፍቀራ።»                                      ትግርኛ

Akka namni isatti amanu marti jireenya barabaraa qabaatuuf malee akka hin banneef, Waaqayyo hanga ilma isaa tokkicha kennutti akka malee addunyaa jaalateeraatii       Oromiffa


ተሳታፊዎች በሌላም ቋንቋ መቀጠል ይችላሉ። ዋናው ነጥብ አንድን ጥቅስ በተለያዩ ትርጉሞች ስናየው ሃሳቡን ይበልጥ ግልጽ እንደሚያደርገው፡ (አንዳንዱም እንደሚያዛባው) እንድናስተውል ነው። እንግዲህ በዚህ የትርጉም ክፍል ለመጽሐፍ ቅዱስ ጥናታችን የተለያዩ ትርጉሞችን በማየት ሃሳቦችን ይበልጥ ለመረዳት እንችላለን ።
ጌታ ቢፈቅድ ብንኖርም በቀጣይ የተለያዩ ጥቅሶችን፡ ጥሬ ቃሎችን በተለያዩ ትርጉሞች እያየን ጥናታችን እንቀጥላለን።
ይቆየን።

No comments:

Post a Comment

አስተያየትዎን ይስጡ / Give Comment