Friday, December 12, 2014

እኔ ማን ነኝ?


እኔ….. ነኝ ብሎ በሥልጣን ቃል የተናገረ፡
በብሉይ ኪዳን፡ እግዚአብሔር ብቻ፡ ነው።….ሰባቱን ብናይ፡-
-      እኔ ለአንተ ጋሻህ ነኝ። ዘፍ ፲፭፣፩
-      እኔ ኤልሻዳይ ነኝ።. ዘፍ ፲፯፣፩
-      የአባቶችህ አምላክ እግዚአብሔር እኔ ነኝ። ዘፍ ፵፮፣፫
-      ያለና የሚኖር እኔ ነኝ። ዘጸ ፫፣፲፬
-      እኔ እግዚአብሔር ነኝ። ዘጸ ፮፣፫
-      ከግብጽ ምድር ከባርነት ቤት ያወጣሁህ እግዚአብሔር አምላክህ አኔ ነኝ። ዘጸ ፳፣፪
-      እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ቀናተኛ አምላክ ነኝ። ዘጸ ፳፣፪
በአዲስ ኪዳን፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ፡ ነው።….ሰባቱን ብናይ፡-ለ
-      የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ። ዮሐ ፮፣፴፭
-      እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ። ዮሐ ፰፣፲፪
-      እኔ የበጎች በር ነኝ። ዮሐ ፲፣፯
-      መልካም እረኛ እኔ ነኝ። ዮሐ ፲፣፲፩
-      ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ። ዮሐ ፲፩፣፳፭
-      እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ። ዮሐ ፲፬፣፮
-      እውነተኛ የወይን ግንድ እኔ ነኝ። ዮሐ ፲፭፣፩
እኔ…..እንዲህ… ነኝ ብሎ የተናገረና መናገር የሚችል አምላክ ብቻ ነው። ምክንያቱም፡-
፩. የማይለወጥ /የማይወሰን ስለሆነ፡
እንዲህ / እዚህ ነበርኩ። እንዲያ / እዚያ እሆናለሁ… አይልም። ቦታ ጊዜ ሁኔታ አይገድበውም።
እግዚአብሔር አይለወጥም፡ አይወሰንም።
ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንትና ዛሬም እስከለዘላለምም ያው ነው።… ዕብ ፲፫፣፰

፪. ሁሉ በእጁ / በእርሱ ስለሆነ፡
እግዚአብሔር ሁሉን ፈጥሮአል፣ ሁሉን ይመግባል።
ኢየሱስ ክርስቶስ ሁሉ ከእርሱና በእርሱ ለእርሱም ነውና፤ ለእርሱ ለዘላለም ክብር ይሁን፤ አሜን። ሮሜ ፲፩፣፴፮።
፫. ከእርሱ በላይ ማረጋገጫ ስለሌለ፡
አንድ ነገር -- ነው / አይደለም-- የሚል ልዩነት ቢፈጠር በሦስተኛ / በበላይ አካል እንዲረጋገጥ ይደረጋል።
እግዚአብሔር ሌላ አስረጅ፣ ምስክር አያስፈልገውም። ከእርሱ በላይ የሚያረጋግጥ ስለሌለ።
፬. ነኝ ያለው የሆነውን ስለሆነ
ሁልጊዜ የነበረውን፣ የሆነውን፣ ወደፊትም የሚሆነውን ነኝ አለ።
ያልሆነውን፣ የማይሆነውን ነኝ አላለም፤ አይልምም።


ከዚህ ምን እንማራለን፡-  
፩. እንድናምነው፡-
ነኝ ብሎ የተናገረ እራሱ ነው። ሌላ ወገን /ሰው/ አይደለም። እርሱ በቀጥታ ተናገረን።
ስለዚህ ምስክር / ማረጋገጫ ሳያስፈልገን ነኝ ያለውን እናምነዋለን።
፪. እንድንታመንበት፡-
ነኝ። የሚለው ከእርሱ ዘንድ ያበቃል፤ ይፈጸማል። ሌላ የተሻለ ወገን ዘንድ አንሄድም።
አለኝ፤ ቢል እርሱ ሳይሆን ከእርሱ ጋር ያለ ነው።… የተሰጠው ነው።/ የሚወሰድበት ይሆናል።
ያን ያህል አያስተማምንም።
፫. ታላቅነቱንና ታማኝነቱን ያሳያል።
ነኝ ያለው ማንነቱ.. በሁሉም ቦታ፣ በሁሉም ጊዜ ይሠራል። አይሻርም፤ አያልፍም።
የመጨረሻው ታማኝ እና ታላቅ እርሱ ብቻ ነው ማለት ነው።

እኛስ? … እኔ… ብለን ስለራሳችን ምን መናገር እንችላለን?
በተፈጥሮአችን ብቻ ሰው ነኝ ማለት እንችላለን። ሰው ያደረገን እርሱ ስለሆነ።
በባሕርያችን ግን አንዲህ ነኝ ማለት አንችለም። ምክንያቱም፡-
፩. ተለዋዋጭ/ውስን ስለሆንን፡
በሁኔታ እንለዋወጣለን። እንደ ስሜታችንና ውጫዊ ነገሮች ጠባያችን ይቀያየራል።
በቦታ/በዘመን ውስን ነን። ስለዚህ  እዚህ ነበርኩ፣ ..ዛሬ/አሁን እዚህ ነኝ።…. ነገ እዚያ እሆናለሁ።…. እንላለን።
ተለዋዋጭነታችን ተፈጥሮአዊ ስለሆነ.. ለሁልጊዜ / ለዘላለም እንዲህ ነኝ ማለት አንችልም።
ሰው ፍጹም አይደለም። አንከን የለሽ፣ የማይሳሳት አይደለም። ….. በሰው አንፍረድ። እኛ ነንና።
፪. አለኝ ማለት አንችላለን።
የተሰጠን ነገር ነውና። ለምሳሌ.. ሃብት፣ ልጅ፣ እውቀት፣ወዘተ….
አለኝ የምንለው ሁልጊዜ አብሮን ሊኖር ስለማይችል አያረካንም።
አለኝ የምንለው ሁልጊዜ ሊያሳርፈን/ ሊያረካን የሚችለው በክርስቶስ ያገኘነው… የዘላለም ሕይወት… ብቻ ነው።
፫. ስለራሳችን ምን እንናገር?
በመጽሐፍ ቅዱስ የቀደሙት ስለራሳቸው ምን ተናገሩ?
-      አብርሃም….. የእግዚአብሔር ወዳጅ……«እኔ አፈርና አመድ ስሆን…»   ዘፍ ፲፰፣፳፯
-      ሙሴ…የእስራኤል ታላቅ መሪ/ በምድር ላይ ካሉት ሰዎች ይልቅ እጅግ ትሑት ሰው ነበረ። የተባለለት….ዘኁ ፲፪፣፫።.. «እስራኤልን ከግብጽ የማወጣ እኔ ማን ነኝ?»…. ዘጸ ፫፣፲፩።
-      ዳዊት… እግዚአብሔር እንደ ልቤ የሆነ የእሴይን ልጅ አገኘሁ… ብሎ የመሰከረለት…የሐዋ ፲፫፣፳፪።….«እኔ ግን ትል ነኝ።».. መዝ ፳፩፣፮።
-      ጳውሎስ… የአሕዛብ ሐዋርያ፣ የተመረጠ እቃ የተባለው…«ከሁሉም በላይ እንደ ጭንጋፍ ለምሆን ለእኔ ደግሞ ታየኝ፤» «ከሐዋርያት ሁሉ የማንስ ነኝና።»….አለ። ፩ቆሮ ፲፭፣፰-፱።
እነዚህ ታላላቅ አባቶች ስለራሳቸው እኔ ብለው እንዲህ ከተናገሩ እኛስ ምን እንበል?
፩. ስለራሳችን በትዕቢት ታላቅ ነገርን የምናወራ ከሆነ እንዋረዳለን።
እግዚአብሔር ሥራው ቦታ ማለዋወጥ ነው።
ትዕቢተኞችን በልባቸው አሳብ በትኖአል፣ ትሑታንንም ከፍ አድርጓል። ሉቃ ፩፣፶፩።
፪. ደካማነታችንን ስናምንለት በድካማችን ኃይሉን ይገልጻል።.. በኛ ላይ ይሠራል።
ለጳውሎስ፡- «ኃይሌ በድካም ይፈጸማልና አለኝ፤ እንግዲህ የክርስቶስ ኃይል ያድርብኝ ዘንድ በብዙ ደስታ በድካሜ ልመካ እወዳለሁ።»  ፪ቆሮ ፲፪፣ ፱።
እግዚአብሔር ጥበበኞችን እንዲያሳፍር የዓለምን ሞኝ ነገር መረጠ፤ ብርቱንም ነገር እንዲያሳፍር እግዚአብሔር የዓለምን ደካማ ነገር መረጠ፤» ፩ቆሮ ፩፣፳፯።
በእውነት ካስተዋልነው ተፈጥሮችን ደካማ ነው። በዓይን የማይታዩ ባክቴሪያዎች የሚያጠቁን ነን።
፫. ባዶነታችን ስናምንለት እርሱ ይሞላናል፣ ይለውጠናል። በቃሉ፣ በመንፈሱ
ወደ ሚጣፍጥ ወይን ጠጅ የተለወጡት የሰው ባዶ ጋኖች በእርሱ ትዕዛዝ /በቃሉ/ ውኃ ከተሞሉ በኋላ ነው። ዮሐ ፪።
አለኝ ብለን በራሳችን ብንመካ… ያለን እስክምንጨርስ /እስኪያልቅ/ ዝም ይለናል። ይጠብቀናል።
፬. ኃጢአታችንን፣ ኃጢአተኝነታችንን ስናምንለት እርሱ ያጸድቀናል።
በራሱ ጻድቅ የሆነ አንድም ስለሌለ።..«ጻድቅ የለም አንድስንኳ፤» ሮሜ ፫፣፲፩
የሚያጸድቅ እግዚአብሔር ብቻ ስለሆነ።  ሮሜ ፰፣፴፫።
-      ስለራሳችን የምንናገረውና የምናወራው ከዜሮ በታች የሆነ አጉል ትሕትና እንዳይሆን እንጠንቀቅ።
፭. ስለሌሎች?
ስለማንም ምንም ልንል አንችልም። ምክንያቱም
-      ሰው ተለዋዋጭ ነውና.. ወደ ክፉም ወደ በጎም።
-      እግዚአብሔርም ይለውጣልና። ወደ በጎ፡
እኔ ማን ነኝ? የሚለውን የራሳችንን ማንነት እንወቅ፣ እንመን።
ማንነታችንን ካላወቅን ሰዎች ናችሁ ብለው የሚያስቡትን ይነግሩናል።
ማንነታችንን ለማወቅ የማን መሆናችንን ማወቅ።

እኔ የእግዚአብሔር ነኝ። በክርስቶስ የዘላለም ሕይወት ያገኘሁ ልጁ ነኝ።

No comments:

Post a Comment

አስተያየትዎን ይስጡ / Give Comment