Friday, March 6, 2015

የኢየሱስ በዲያብሎስ መፈተን

« ከዚያ ወዲያ ኢየሱስ ከዲያብሎስ ይፈተን ዘንድ መንፈስ ወደ ምድረ በዳ ወሰደው፥
አርባ ቀንና አርባ ሌሊትም ከጦመ በኋላ ተራበ። ፈታኝም ቀርቦ…..» ማቴ ፬፣ ፩ - ፲፩
Ø ኢየሱስ ክርስቶስ በዮሐንስ መጥምቅ ከተጠመቀ በኋላ ምድራዊ አገልግሎቱን ከመጀመሩ በፊት በዲያብሎስ ተፈተነ፣- ከጾም ጋር ነበረ። - ለአገልግሎቱ የዝግጅት / የጽሞና ጊዜ ወሰደ።
Ø ክርስቶስ ወደ ምድረ በዳ በመንፈስ ቅዱስ ምሪት የተወሰደበት ዓላማ - ከዲያብሎስ ይፈተን ዘንድ - ነው።
-      ለምን ተፈተነ? - እግዚአብሔር ልጄ ስላለው ልጅነቱን ለማረጋገጥ፣ የዲያብሎስ አለመሆኑን - ወርቅ በእሳት እንደሚፈተን፡ - ማስመስከር ነበረበት።
-      ፈተናውን በድል ተወጥቶ ለእኛ እንድንማርበት፣ - ፍለጋውን እንድንከተል። ዲያብሎስን በፈተና ድል እንድናደርግ።
«የተጠራችሁለት ለዚህ ነውና፤ ክርስቶስ ደግሞ ፍለጋውን እንድትከተሉ ምሳሌ ትቶላችሁ ስለ እናንተ መከራን ተቀብሎአልና።»     ፩ ጴጥ ፪፣ ፳፩
Ø - ከዚያ ወዲያ-  ከምን? - ከምዕራፍ ፫፣ መጨረሻ- ተጠምቆ ከውሃ ሲወጣ - አብ በሰማይ ሆኖ ከመሰከረለት በኋላ- «… በእርሱ ደስ የሚለኝ የምውደው ልጄ ይህ ነው አለ።»
o   እግዚአብሔር ልጄ ብሎ መስክሮለት - የእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ ዲያብሎስ እንዴት ቀረበው? - ድል እንዲያደርገው።
o   ጌታ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ስለተጓዘ - በቃሉ ኃይል ድል አድርጎታል።
o   እኛ በጸጋ የእግዚአብሔር ልጆች ነን። ይህ ማለት ሰይጣን አይቀርበንም ማለት አይደለም። በተለያየ መንገድ ሊጥለን ይቀርባል። ትልቁ ነገር ግን በመንፈስ ቅዱስ ምሪት እስከተጓዝን ድረስ - ምድረ በዳም እንግባ/ ምግብም አይኑር/ ዲያብሎስም ይምጣ - ቃሉን እስከታጠቅን ድረስ - ድል እናደርገዋለን። - የተረጋገጠ ጉዳይ ነው።
፩. ፈተናዎቹ - ፫ ናቸው -  /ስስት፣ ትዕቢት፣ ፍቅረ-ንዋይ - ይሉታል አባቶች/ - እንያቸው፡-
ü ፩. ድንጋዩን እንጀራ አድርግ - ቁ. ፪ - ፬ - ስስት- ፤ - በእግዚአብሔር መግቦት ላይ የቀረበ ፈተና
o   ጌታ ፵ ቀን ፵ ሌሊት ጾሞ ተርቦ ነበር። ዲያብሎስ እንደራበው አይቶ ነው የተናገረው፡- የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንክ እነዚህ ድንጋዮች እንጀራ እንዲሆኑ በል- ሁለት ማሳመኛ
§  ፩. እርቦሃል - የሚበላ ነገር ያስፈልግሃል። በዚህ ምድረ በዳ ድንጋይ ብቻ ነው።
§  ፪. የእግዚአብሔር ልጅ ነህ - ድንጋዩን ወደ እንጀራ መለወጥ ትችላለህ።
እንደራበው እንዴት አወቀ? -- ያያል፣ ጌታ ምግብ አልበላም - በጾም ላይ ነውና።
የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን እንዴት አወቀ? -ሰምቷል-- አብ በሰማይ ተናግሯልና።
         ስለዚህ ዲያብሎስ ስለእኛ የሚያውቀው ከድርጊታችንና ከቃላችን ብቻ ነው ማለት ነው። የልባችን አያውቅም፤ የልብን የሚያውቅ ባለቤቱ እና እግዚአብሔር ብቻ ነው።…


የዲያብሎስ አሳቡ ሲታይ ጠቃሚና ትክክል ነገር ነው። ታዲያ ጌታ ለምን እምቢ አለው?
o    የእግዚአብሔር ልጅ እንደመሆኑ ማስቀደም ያለበት መንፈሳዊውን ምግብ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ማዕድ መመገብ መሆን አለበት።
ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም
o   በእንጀራ ብቻ - ሲል በዚች ምድር ለማለት ነው። ለሥጋ እንጀራ ብቻ ሳይሆን ለነፍስ የቃሉ ማዕድ ያስፈልጋል፤ አለዚያ - አይኖርም - ኑሮ መኖር አይባልም።
o   እንጀራ ለመብላትም መጀመሪያ ሕይወት /ሕልውና/ ሲኖረን ነው። ሕይወትም እግዚአብሔር ነው። ርቦኛል ብለህ እንጀራ ለመፈለግም መጀመሪያ ሕይወትን ማን ሰጠህ?
o   ከእግዚአብሔር አፍ የሚወጣው ቃል - የኑሮ ኃይል፣ ሠላም፣ ደስታ - ከምግብ ጋር ያልተያያዘ ነው።.. እንጀራ እየበላንም ኑሮ መኖር ላይባል ይችላል፤ በእነዚህ እጦት።
o   ወደፊት ለዘላለም ከእግዚአብሔር ጋር የምንኖረው በቃሉ መሠረት እንጂ በእንጀራ አይደለም፤ ስለዚህ ሁልጊዜ ስለሆድ፣ ስለመብል ስለመጠጥ ብቻ በማሰብ መጠመድ የለብንም፤ የሚቀድመውን እና የሚዘልቀውን ሕልውናችንን /ዘላለማዊውን፣ ሰማያዊውን/ ማሰብ አለብን።
ተብሎ ተጽፏአል፤ - ምግብ ለተራበ ከሚለው ምድራዊ መመሪያ በላይ የተጻፈው ቃሉ ሊገዛን፣ ሊመራን ይገባል።

-      ፪. መላእክቱን ስለአንተ ያዝልሃል… ራስህን ወደታች ወርውር - ቁ. ፭- ፮  - ትዕቢት- ፤
በእግዚአብሔር ጥበቃ ላይ የቀረበ - ፈተና
o   ዲያብሎስ መጀመሪያ የተናገረው ትክክል ነው፤ በመዝ ፺/፺፩፣ ፲፩ - ፲፪ ፣ አለ።
      በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ መላእክቱን ስለ አንተ ያዝዛቸዋልና እግርህም በድንጋይ እንዳትሰናከል በእጆቻቸው ያነሡሃል።
o   በሁለተኛው የተናገረው ግን ስህተት ነው፤ - ራስህን ወርውር-
ጌታ - አምላክህን አትፈታተነው- ማለትም- ራስህን አለመጉዳት፣ ወይም ማዳን እየቻልክ እንዴት ያድነኝ እንደሆነ ብለህ ትፈታተነዋለህ? ዓይን፣ አእምሮ፣ ልብ/ማስተዋል/ ለምን ሰጠህ ታዲያ?
ራሳቸውን መጠበቅ የማይችሉትን - ሕጻናትን- እግዚአብሔር ይጠብቃል- ከትልልቅ የአውሮፕላን/የእሳት አደጋዎች- ሕጻናት ሲተርፉ እንሰማለን።
-      ፫. ወድቀህ ብትሰግድልኝ ይህን ሁሉ እሰጥሃለሁ- ቁ. ፰ - ፱ -  - ፍቅረ-ንዋይ- ፤
በእግዚአብሔር አምልኮ ላይ የቀረበ ፈተና
-      ደግሞ ዲያብሎስ እጅግ ረጅም ወደ ሆነ ተራራ ወሰደው፥ የዓለምንም መንግሥታት ሁሉ ክብራቸውንም አሳይቶ።?
 .. እንዴት/ወዴት ሄዱ?... የትኛው ተራራ ነው በዓለም ላይ ያሉትን መንግሥታት ሁሉ ክብራቸውንም የሚያሳይ - በአንድ ጊዜ?..
 ሁለተኛው ፈተና ላይ፡- ከዚህ በኋላ ዲያብሎስ ወደ ቅድስት ከተማ ወሰደውና እርሱን በመቅደስ ጫፍ ላይ አቁሞ። --  በትክክል በእግራቸው ሄደው ወጥተዋል። ራስህን ወርውር ብሎታልና።
-      ይሄኛው ተራራ ግን እንዴት የሚል ጥያቄ ያስነሳል? ይህ መጽሐፍ ቅዱስን /ቃሉን/ ጥያቄ ውስጥ አይከተውም። አተረጓጎሙን በሌላ ተመሳሳይ ገለጻ ማየት እንጂ።
በእግዚአብሔር ራእይ ወደ እስራኤል ምድር አመጣኝ እጅግም በረዘመ ተራራ ላይ አኖረኝ፥ በዚያም ላይ በደቡብ ወገን እንደ ከተማ ሆኖ የተሠራ ነገር ነበረ።  ሕዝ ፵፣ ፪
በመንፈስም ወደ ታላቅና ወደ ረጅም ተራራ ወሰደኝ፥ የእግዚአብሔርም ክብር ያለባትን ቅድስቲቱን ከተማ ኢየሩሳሌምን ከሰማይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ስትወርድ አሳየኝ፤ ራእ ፳፩፣ ፲
ስለዚህ ሊሆን የሚችለው - በራእይ/በመንፈስ- ነው።
-      ከዚያ - ወድቀህ ብትሰግድልኝ ይህን ሁሉ እሰጥሃለሁ። 
ይሄ ሁለቱም ንግግሩ ሙሉ በሙሉ ስህተት ነው።
     ፩ኛ መስገድ የሚገባ ለእግዚአብሔር አምላክ ብቻ ነው። - ከ፲ቱ ትዕዛዛት ፩ኛ።
     ፪ኛ እርሱ መስጠት አይችልም፤ ውሸቱን ነው። ሁሉ የጌታ ነው። እርሱ ምንም የለውምና።
ጌታ ከዚህ ላይ አልታገሰውም፣ በእግዚአብሔር አምልኮ በቀዳማዊ ትዕዛዝ ስለመጣ - ሂድ አለው።
በሦስቱም የዲያብሎስ ሁለት ሁለት ንግግሮች የምናስተውለው
- በመጀመሪያው ሁለቱም ትክክል ነበር። ርቦታል፣ ድንጋዩን እንጀራ ማድረግ ይችለል
- በሁለተኛው አንዱ ትክክል አንዱ ስህተት ነበር፤ መላእክቱን ያዝልሃል /የተጻፈ/ - ራስህን ወርውር??
- በሦስተኛው ሁለቱም ስህተት ነበር።- ስገድልኝ፣ እሰጥሃለሁ።
ከስውር ወደ ግልጽ/ ከሚጠቅም የሚመስል ወደ ሚጎዳ/ ከእውነት ወደ ሀሰት ከትክክል ወደ ስህተት ንግግሩ መሄዱን ነው። ዛሬም እንደዚያው ነው። ቀስ በቀስ እያንሸራተተ ይወስዳል።
የምንማራቸው፡-
፩. ዲያብሎስ የእግዚአብሔርን ቃል ያውቃል።
-      የእግዚአብሔርን ቃል የሚጠቅስ ሁሉ ከእግዚአብሔር ላይሆን ይችላል፤ ከዲያብሎስ ሊሆን ይችላል። መጠንቀቅ አለብን።
-      ዲያብሎስ የእግዚአብሔርን ልጅ የእግዚአብሔርን ቃል በመጥቀስ ከፈተነው - እኛንም ልጆቹን እንዲሁ ይፈትነናል። ቃሉን በበለጠ ታጥቀን መከላከል አለብን።
-      የእግዚአብሔርን ቃል መቼ፣ ለምን ሁኔታ መጠቀም እንዳለብን ማወቅ አለብን።
፪. ዲያብሎስ የእግዚአብሔርን ልጅ ያውቃል።
-      ጌታን የእግዚአብሔርስ ልጅ ከሆንክ ይለው ነበር። ጌታ- የእግዚአብሔር ልጅ ለመሆኑ ማረጋገጨው የዲያብሎስ ንግግር በመስማቱ እና በፈጸሙ አይደለም።
-      እኛም የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን ያውቃል፤ በክርስቶስ አምነን ስናርፍ ያያል፤ ስለዚህ ይከታተለናል። ልንፈራው አይገባም፤ የተሸነፈ ጠላት ነው።
፫. ሦስት ፈተናዎች - በሦስት ቦታዎች - በሦስት አቅጣጫዎች
-      ሦስቱ ፈተናዎች፡-  ስስት፣ ትዕቢት፣ ፍቅረ-ንዋይ
ሰይጣን - አዳምን - በኋላም ዳግማዊ አዳም ክርስቶስን - ዛሬም ሰዎችን የሚፈትንበት በዓለም ያለው እነዚህ ሦስት ጉዳዮች ናቸው። - ዮሐንስ ስለእነዚህ ያስጠነቅቀናል።
ዓለምን ወይም በዓለም ያሉትን አትውደዱ፤ በዓለም ያለው ሁሉ እርሱም የሥጋ ምኞትና የዓይን አምሮት ስለ ገንዘብም መመካት ከዓለም ስለ ሆነ እንጂ ከአባት ስላልሆነ፥ ማንም ዓለምን ቢወድ የአባት ፍቅር በእርሱ ውስጥ የለም።  ፩ ዮሐ ፪፣ ፲፭ - ፲፮
፩. የሥጋ ምኞት - ሥጋ የሚፈልገው የመጀመሪያው ነገር - ምግብ ነው። ስለምግብ መጠጥ መጨነቅ።
፪. የዓይን አምሮት - ትዕቢት፣ ታይታ፤ አጉል ትምክህት…
፫. ስለገንዘብ መመካት - ገንዘብን መውደድ፣ ማሳደድ፣ ሁልጊዜ ማሰብ…..
ዲያብሎስ ሔዋንን ሲፈትን በእርሷ በኩል ሦስት ችግሮች ነበሩ፤  ዘፍ ፫፣ ፫ - ፭
       ስለመብል - - አትንኩትም---ቁ. ፫ - እግዚአብሔር ያልተናገረውን ተናገረች።
       ስለመኖር -- ሞትን አትሞቱም፡ - እግዚአብሔር ከተናገረው ተቃራኒ ሰማች፡-ዝም አለች፤  ቁ. ፬፡  ከ፪፣ ፲፯ ጋር።
       ስለጥበብ - --- እንደ አምላክ የመሆን--- እግዘአብሔር ያላለውን ነገር ሰማች። ቁ ፭
በሦስቱም የእግዚአብሔር ቃል እውቀት አልነበራትም። ራሷን ለፈተና አጋለጠች፣ ሰማች፣ ተሳሳተች፤
«….ሴቲቱም ዛፉ ለመብላት ያማረ እንደ ሆነ፥ ለዓይንም እንደሚያስጎመጅ፥ ለጥበብም መልካም እንደ ሆነ አየች…»  ዘፍ ፫፣ ፮
የአዳም/የሔዋን/ እና የክርስቶስ ፈተና ግን የሚነጻጸር እንጂ የሚወዳደር አይደለም። ምክንያቱም፡-
አዳም - እየበላ እየጠጣ - በአንዲት ዛፍ ነው። , - ጌታ ግን ምንም ሳይበላ ሳይጠጣ ጾሞ ነው።
አዳም - ከሚስቱ ጋር ነበሩ። . - ጌታ ግን ብቻውን ነበረ።
አዳም - በገነት - በልምላሜ ቦታ ነበረ። - ጌታ ግን በምድረ-በዳ /ምንም ተክል… በሌለበት።
የማን ይብሳል? - ማን መቋቋም ነበረበት?--
-      ሦስት ቦታዎች
፩. በምድረ በዳ - በጾም፣ ጸሎት - በጽሞና ስንሆን - ምንም ነገር በሌለበት - ፈተና አለ።
§  እግዚአብሔር አይመግብህም- ቶቶሃል-
፪. በመቅደስ - በእግዚአብሔር ቤት - በአገልግሎት - ፈተና አለ
§  እግዚአብሔር አይጠብቅህም፣ በቤቱ ሆነህ - ጥርጣሬ መዝራት
፫. በከተማ - በዓለም - ሰዎችን ግርግር በበዛበት - ፈተና አለ።
§  በዚህ እግዚአብሔር ስለማይታወቅ  ለእኔ ስገዱልኝ - ተገዙልኝ፤ በማለት
-      በሦስት አቅጣጫዎች፡-  ወደ ውስጥ፣ ወደላይ፣ ወደጎን
o   ፩. ከራሳችን ጋር፡- ስስት/ መብል መጠጥ/ ግላዊ ነው። በምድረ-በዳ ብቻውን ከራሱ ጋር በጾም ጸሎት /ጽሞና/ እያለ - ከራሳችን ጋር እንድንጣላ፤
ርቦኛል -ቸግሮኛል - የእግዚአብሔር ልጅ መሆኔ ለዚህ ካልጠቀመኝ ምን ዋጋ አለው?... እንድንል
§  ጌታ ግን መቅደም ያለበትን እንድናስቀድም ይፈልጋል። ሌላው ይከተላል።
o   ፪. ከእግዚአብሔር ጋር፡-  /ወደላይ/ እግዚአብሔር ይጠብቅሃል፣ ስለዚህ እንደፈለክ መኖር ትችላለህ፤… /ራስህን ወርውር-/
§  እግዚአብሔር ግን ራሳችንን የምንጠብቅበት አእምሮ ሰጥቶናል። እጅ፣ እግር፣ ዓይን ሰጥቶናል። እያየን መራመድ አለብን።
§  እግዚአብሔር ሁልጊዜ ይጠብቀናል፤ ግን ራሳችንን መጠበቅ ከምንችለው አቅም በላይ ሲሆን ነው። - የማናየው፣ ያልደረስንበት….
§  «ከጠላቴ ራሴን እጠብቃለሁ፤ ከወዳጄ አንተ ጠብቀኝ» ይላሉ ፈረንጆች። ጠላት የሚታይ- ፊት ለፊት ያለ ነው። ወዳጅ ግን አጠገብ ሆኖ የሚጎዳ ነው። ---በኛ አገርም - «ከወዳጅ ክዳት የጠላት ጥቃት ይሻላል» ይባላል።
o   ፫. ከዓለም ጋር፣-  /ወደ ጎን/ - በዙርያችን የምናየው፣ የምንሰማው የዓለም ግርግር፣ ገንዘብ፣ ዝና፣ ክብር፣ ኢንተርኔት… እነዚህን እንድንከተል/ እንድናስቀድም በማድረግ፤ በእነዚህ በመጥመድ ስለመንፈሳዊው እንዳናስብ አእምሮአችንን፣ ጊያችንን በመያዝ….
o   ይህ አሁን የሚታይ የዲያብሎስ የዘመኑ ፈተና ነው።
o   አስፈላጊ ቢሆንም ቀዳሚ ነገር አይደለም። የሚቀድመው የእግዚአብሔር መንግሥት ሲሆን እነዚህ የሚከተሉ/ የሚጨመሩ ናቸው።
፬. በእግዚአብሔር ቃል ዕውቀት፣ በመንፈስ ቅዱስ ምሪት እስከተጓዝን ድረስ የዲያብሎስን ፈተና ድል እናደርገዋለን።
-      በራሳችን ማስተዋል፣ በራሳችን ምሪት /የሕይወት ፍልስፍና/ ከተጓዝን እንወድቃለን።
፭. ጌታ የዲያብሎስን ፈተና ድል ያደረገው እንዴት ነው?
በመሸሽ ፣ በማምለጥ አይደለም፡- ወሰደው - አቆመው፣ …. አሳየው ፤
ግን ጌታ ዲያብሎስ መሆኑን ያውቅ ነበር? /እንደ ሰውነቱ?/ ከሆነ እያወቀ ለምን ሄደለት?
በግልጽ አልተጻፈም። --- ሳናስበው በመደበኛ ማኅበራዊ ሕይወታችን ዲያብሎስ ሊወስደን ይችላል። በሰዎች፣ በእንቅስቃሴዎች… ስለዚህ በሰዎች ንግግር በሁኔታዎች የምንሰማውን የምናጣራው በእግዚአብሔር ቃል እውቀት ነው። - ወደ ፈተና ላለመግባት።
ዋናው ግን ሰው የሚፈተነው፡-
ነገር ግን እያንዳንዱ በራሱ ምኞት ሲሳብና ሲታለል ይፈተናል።   ያዕ ፩፣ ፲፬
ዲያብሎስ የሌለበት ቦታ አይኖርም፤ የዚች ዓለም ገዢ እስከተባለ ድረስ - በሁሉም ቦታ ይኖራል፤ ቤተ መቅደስን/ ቤተ ክርስቲያን ጨምሮ።
 በሦስቱም ጌታ---  እንዲህ ተብሎ ተጽለፏል በማለት ነበር። - በእግዚአብሔር ቃል እውቀት።
-      በእግዚአብሔር ቃል ዕውቀት ከታጠቅን የዲያብሎስን ፈተና በቀላሉ ድል እናደርገዋለን።
« የዲያብሎስን ሽንገላ ትቃወሙ ዘንድ እንዲቻላችሁ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ ልበሱ።…..የእምነትን ጋሻ አንሡ፤ የመዳንንም ራስ ቁር የመንፈስንም ሰይፍ ያዙ። እርሱም የእግዚአብሔር ቃል ነው።»     ኤፌ ፮፣ ፲ - ፲፯
የእግዚአብሔር ቃል ቀላል አይደለም። እኛ በቀላሉ እናየዋለን። እግዚአብሔር ዲያብሎስን ድል ለማድረግ ቃሉ ብቻ በቂ ነው። ቃሉ ራሱ ከኃይል ጋር ይሠራልና።
ስለዚህ ቃሉ የዲያብሎስን ፈተና የምንከላከልበትና የምናጠቃበት ዋና ዕቃ ጦር /ጦር መሣሪያ/ ነው። ስለዚህ ቃሉን ማንበብ፣ ማጥናት፣ በቃል መያዝ… አለብን። - ጌታ መጽሐፍ አልገለጠም፣ በቃሉ ይመልስ ነበር።
-      ጋሻ ና ራስ ቁር - መከላከያ።  ሰይፍ - ማጥቂያ። - የውጊያ ስልት መከላከል ብቻ አይደለም ማጥቃትም ያስፈልጋል።- ጌታ ሲከላከለው ቆይቶ በመጨረሻ - ሂድ- ነው ያለው፣ አጠቃው። ድል አደረገው።
Ø የጌታ ጾም - የዐቢይ ጾም ዐቢይ ዓላማ ይህ ነው። የዲያብሎስን ፈተና በቃሉ እውቀት ድል ለማድረግ። ለምን ነው የምንጾመው? - ዓላማ ሊኖረን/ ዓላማውን ልናውቅ ይገባል።
በመጨረሻ - ሂድ አንተ ሰይጣን - ብሎ አባረረው፡- አምላክ ነውና።
እኛም በስሙ ኃይል - በኢየሱስ ክርስቶስ ስም- ልናባርረው እንችላለን፤ በራሳችን አይደለም።
ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ፥….ነው።   ፊልጵ ፪፣ ፲ - ፲፩
Ø ስለዚህ ፈተናን ልንፈራ አይገባም። ምክንያቱም፡-
« እርሱ ራሱ ተፈትኖ መከራን ስለ ተቀበለ የሚፈተኑትን ሊረዳቸው ይችላልና።» ዕብ ፪፣፲፰
-      አንድ መምህር እንዳለው ለጌታ ችግራችንን ስንነግረው የሚሰማ ብቻ ሳይሆን የሚሰማው ነው። ግን ከሁሉም በላይ፡-

-      ለጌታ የችግርህን ታላቅነት አትንገረው፣ ለችግርህ የጌታን ታላቅነት ንገረው። እንደተባለው ነው።

No comments:

Post a Comment

አስተያየትዎን ይስጡ / Give Comment