Friday, November 28, 2014

የፈቃዱ ምሥጢር - ክፍል ፩


በክርስቶስ ለማድረግ እንደ ወደደ እንደ አሳቡ፥ የፈቃዱን ምሥጢር አስታውቆናልና፤
በዘመን ፍጻሜ ይደረግ ዘንድ ያለው አሳቡም በሰማይና በምድር ያለውን ሁሉ በክርስቶስ ለመጠቅለል ነው።
ኤፌ ፩፣ ፱ - ፲  / ሙሉ ሃሳቡ ከቁ ፩ - ፲፬፤/
ፈቃዱ፡- ፍላጎቱ፣ አሳቡ፣ እቅዱ፣ ዓላማው፣ ውሳኔው ማለት ነው።
ምሥጢር፡- የማይነገር ስለሆነ ሳይሆን ተሰውሮ የኖረ በኋላ የተገለጠ ለማለት ነው።
ይህም የእግዚአብሔር የዘላለም ሃሳብ የሆነ መለኮታዊ ዕቅድ ነው።
-      ከቁ. ፫ - ፲፬፡- በግሪኩ አንድ ረጅም አረፍተ ነገር ነው፡፡ እኛም በአንድ አረፍተ ነገር ብናጠቃለው፡-
Ø  «እግዚአብሔር በክርስቶስ ለሆኑት ልጆቹ ስላደረገው መንፈሳዊ በረከት ክብር ምስጋና ይገባዋል።»  የሚል ይሆናል።
፩. ራሱን ማስተዋወቅ፡-  - የድሮ ደብዳቤዎች ሲጀምሩ ጸሐፊው ራሱን በመጥቀስ ነው።  
 ጳውሎስ ሐዋርያ የሆነው በእግዚአብሔር ፈቃድ ነው።
ከ፲፪ቱ ሐዋርያት ጋር አልተጠራም፤ በኋላ በክርስቶስ መገለጥ በልዩ አጠራር ተጠራ።
የመልዕክቱ አድራሻ፡- በኤፌሶን ላሉት፣ በክርስቶስ ላሉት - አሁንም ለእኛ፡፡ - ተዘዋዋሪ ደብዳቤ ነው ይሉታል።
፪. ሠላምታ፣-  ጸጋና ሠላም - የጳውሎስ የተለመደ ሰላምታ።
ጸጋ፡- እግዚአብሔር መዳናችንን የሰጠበት የራሱ ነጻ ስጦታ። ቸርነቱ አይለየን፤ ጤና ይስጥልን እንደማለት ነው፡
ሠላም፡- ከዳንን በኋላ በክርስቶስ የሚኖረን እረፍት -- ሠላም ለናንተ ይሁን።
፫. በረከት፡- በረከት፣ የባረከን፣ ይባረክ።  ይህ በረከት፡-
Ø  በክርስቶስ የተደረገ ነው፤ ምክንያቱም መርገም በሰይጣን መጥቶ ነበርና ፡በአዳምና በልጆቹ ዘፍ ፫ና ፬
Ø  ሰማያዊ ነው። - ምድራዊ አይደለም፡- ቀዳሚው ነገር ነው።
Ø  መንፈሳዊ ነው። - ሥጋዊ / ቁሳዊ አይደለም።
Ø  ዘላለማዊ ነው፡፡ - ጊዜያዊ አይደለም።
²  የሚቀድም፣ የማይቀር፣ ዘላለማዊ በረከት ነው - የተፈጠርንበት ዋና ዓላማ።

1ኛ - ፬-፭. - የፈቃዱ መነሻ፡- እቅዱ-- የአብ ሥራ
የእግዚአብሔር ምርጫና ውሳኔ፡ - ቅድመ-ውሳኔ በሚል ያከራክራል። የሚድኑትን አስቀድሞ ወስኗል???
-      እግዚአብሔር የወሰነው መንገዱን እንጂ ሰዎችን አይደለም። - God choose the plan not the man.
-      መቼ? -- ዓለም ሳይፈጠር - ማንነታችን ሳይታወቅ፣ ሥራችን ሳይታይ - መረጠን።
-      ለምን? -- በፊቱ ቅዱሳን፡- ለእርሱ የተለዩ፤ ነውር የሌለን- ያለኃጢአት /በጽድቅ/ ፣ በፍቅር እንድንሆን
-      እንዴት?-- በክርስቶስ ፤  - በክርስቶስ ምን? --  ከታች አለ- በደሙ በተደረገ ቤዛነት፡- ቁ. ፯
Ø  ከመፈጠራችን በፊት መዳናችን ታቅዷል። የድኅነታችን መነሻ የእግዚአብሔር እቅድ ነው።
Ø  ልጆቹ ገና ሳይወለዱ፥ በጎ ወይም ክፉ ምንም ሳያደርጉ፥ ከጠሪው እንጂ ከሥራ ሳይሆን በምርጫ የሚሆን የእግዚአብሔር አሳብ ይጸና ዘንድ፥---  ሮሜ ፱፥ ፲ - ፲፪
Ø  የሰርግ ግብዣ ጥሪ ስናደርግ የሚመጡትን ሰዎች ስም እንወስናለን። የጥሪ ወረቀት እንበትናለን።
²  የምንወስነው የሚመጡትን ነው፤ የማይመጡትን አይደለም።
²  እግዚአብሔር ሁሉን ነው የጠራ-- ከታች ቁ. ፲ -- ሁሉን በክርስቶስ ለመጠቅለል
²  የተጠሩት ሁሉ ግን ጥሪውን አክብረው ላይመጡ ይችላሉ። እንዳይመጡ ግን አልወሰነም።
Ø  በሁሉን አዋቂነቱ ማን ለጥሪው መልስ እንደሚሰጥ/ እንደሚድን/ ያውቃል
- ይህ ማለት የሚድኑትን ለይቶ ወስኗል ማለት አይደለም።
- ምክንያቱም በሌላ በኩል የሰዎች ምርጫ /መብት/ ያለገደብ የተከበረ ነው፤ ማንም አይገደድም።
Ø  ቁ. ፬ - በክርስቶስ፣ ቁ. ፭ - በክርስቶስ ሥራ -- ስለዚህ በእኛ በጎነት ስለተገኘ/ ልዩ ስለሆንን አይደለም
Ø  ይህ ከሥላሴ -- የአብ - ድርሻ ነው፤ -- እቅድ- ውሳኔ። ስለዚህ፡-
Ø  ቁ ፮  - የጸጋው ክብር ይመሰገን ዘንድ --- ለአብ ክብር ምስጋና ይገባዋል።
2ኛ የፈቃዱ ምሥጢር አፈጻጸም -- የወልድ ሥራ
ቁ. ፯ - በደሙ- ቤዛነትና ሥርየት
-      እንደጸጋው ባለጠግነት መጠን፡- በብዙ ቸርነቱ፡- -- በኛ ሥራ አይደለም።
-      በደሙ-- በክርስቶስ የመስቀል ሞት -- ደሙን በማፍሰስ - በዚህ ሁለት ነገር አገኘን
Ø  ፩. ቤዛነት - በኛ ምትክ እርሱ ሲሞት እኛ ሕይወትን አገኘን።
Ø  ፪. ስርየት - የኃጢአት ይቅርታ የበደላችንን ሙሉ ዋጋ እርሱ ከፈለ።
ቁ. ፰ - ፱ ማስተዋልና ዕውቀት
Ø  በደሙ የኃጢአት ሥርየት እና ሕይወት ካገኘን ከጽድቅ በኋላ - ዕውቀት ይመለስልናል።
Ø  ይህን የፈቃዱን ምሥጢር የምንረዳው / የምናስተውለው በክርስቶስ ድህነትን ካገኘን በኋላ ነው።
ቁ. ፲ - ዋናው የፈቃዱ ምሥጢር  - አሳቡ
Ø  ሁሉን በክርስቶስ ለመጠቅለል ነው። መጠቅለል ምንድን ነው?
²  በልጁ ሞት /በደሙ ዋጋ ሁሉም የመንግሥቱ ወራሾች እንዲሆኑ ማድረግ ነው።
Ø  በዘመን ፍጻሜ፡ - በሰማይና በምድር  -- መላእክትና ሰዎች ይጠቀለላሉ -- አንድ ላይ ይሆናሉ።
²  በብሉይ ኪዳን ፍጻሜ -- ክርስቶስ መጣ ተወለደ - መላእክትና ሰው ዘመሩ
²  በአዲስ ኪዳን ፍጻሜ- - ክርስቶስ ዳግም ሲመጣ- ጥሪውን የተቀበሉ እና ያመኑበት ወደ መንግሥተ ሰማያት ይሄዳሉ፡- ከመላእክት ጋር ለዘላለም በምስጋና ይኖራሉ።
Ø  በሰማይና በምድር -- ዓለማቱን ሁሉ ከወሰድን
²  በወልድ ቃልነት ዓለማቱ ተፈጠሩ።
l  በእግዚአብሔር ቃል ሰማዮች ጸኑ፥ ሠራዊታቸውም ሁሉ በአፉ እስትንፋስ  መዝ ፴፫፣፮
l  ዓለሞች በእግዚአብሔር ቃል እንደ ተዘጋጁ፥  ዕብ ፲፩፣፫
²  በወልድ /በክርስቶስ/ ሞት ዓለም ዳነ።
²  በወልድ /በክርስቶስ/ ምጽአት ዓለሙ ያልፋል።
l  ዓለማቱን በመፍጠር - በማዳን - በማሳለፍ --- በወልድ /በክርስቶስ/ ተጠቅልለዋል።
 ቁ. ፲፩ - ርስት /መንግሥተ ሰማያትን/ መቀበል
Ø  እንደ እርሱ አሳብ /መለኮታዊ ዕቅድ/ - መንግሥቱን ለማውረስ አሳቡን ያመጣው እርሱ ነው።
Ø  አስቀድመን የተወሰንን - ዓለም ሳይፈጠር ጥሪውን የተላከልን - በኋላ ጥሪውን የተቀበልን
Ø  በክርስቶስ ርስትን ተቀበልን፡- ርስቱን የምንቀበለው ነው እንጂ በጥረታችን የምናገኘው አይደለም። በክርስቶስ ሥራ - የመስቀል ሥራ።
²  እንኳን የዘላለም ሕይወትን - ሥጋዊ ሕይወታችን እንኳን በጥረታችን አላገኘነውም። መፈጠራችን እና መወለዳችን የእርሱ ሥራ ነው።
-      ቁ. ፲፪ - ለክብሩ ምሥጋና - ፪ኛው።
Ø  መዳንን ያገኘንበት - ርስቱን እንድንወርስ ተስፋ ያደረግንበት እግዚአብሔር ወልድ - ኢየሱስ ክርስቶስ ክብር ምስጋና ይድረሰው።
3ኛ. የእቅዱ አፈጻጸም ማረጋገጫ - መንፈስ ቅዱስ
ቁ. ፲፫ - የመዳን ማኅተም
Ø  የእውነት ቃል - የመዳን ወንጌል - -- ቃል/ወንጌል - ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
Ø  ሰምታችሁ - አምናችሁ -- ከዳናችሁ -- ማህተም - የተስፋው መንፈስ - መታተም።
Ø  ማኅተም - ማረጋገጫ ነው።
ቁ. ፲፬ - የርስታችን መያዣ
Ø  እርሱም -- መንፈስ ቅዱስ
Ø  መያዣ - ቀብድ ነው። አንድ ሰው ለሚገዛው እቃ ቀብድ ካስያዘ እንደሚወስደው ማረጋገጫ ነው።
Ø  መንግሥተ ሰማያትን / ርስታችንን/ እንደምንወርስ ማረጋገጫው የመንፈስ ቅዱስ ማኅተም ነው።
Ø  በአብ የታቀደውን፣ በወልድ የተከናወነውን ሥራ ቀጣይና ዘላቂ የሚያደርገው መንፈስ ቅዱስ ነው።
-      ለእግዚአብሔር ያለውን እስኪዋጅ ድረስ -- ሁሉም እስኪድኑ /በክርስቶስ እስኪጠቀለሉ ሥራውን የሚሠራ አሁን መንፈስ ቅዱስ ነው።
-      ለክብሩ ምስጋና - ፫ኛ
Ø  በአብ ዕቅድ መሠረት በወልድ የተፈጸመውን ፈቃዱን በማረጋገጥ ሥራውን ለሚሠራ ለመንፈስ ቅዱስም ክብር ምስጋና ይገባዋል።

ከዚህ ክፍል የምንማራቸው፡-
-- ይቀጥላል---

No comments:

Post a Comment

አስተያየትዎን ይስጡ / Give Comment