Tuesday, November 4, 2014

ስለጉድለት አልልም - ፩

ማክሰኞ - ጥቅምት ፳፭ / ፳፻፯ ዓ/ም
« … ይህን ስል ስለጉድለት አልልም፤ የምኖርበት ኑሮ ይበቃኛል፤ ማለትን ተምሬያለሁና። መዋረድንም አውቃለሁ መብዛትንም አውቃለሁ፤ በእያንዳንዱ ነገር በነገርም ሁሉ መጥገብንና መራብንም መብዛትንና መጉደልን ተምሬአለሁ።
ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ።»  ፊልጵ ፬፣ ፲-፲፫።
-      ኑሮየ ይበቃኛል - በእንግሊዝኛው content - ባለው የረካ - የገንዘብ ፍቅር የማያጠቃው፣
-      የፊልጵዩስ ቤተክርስቲያን /አማኞች/ ጳውሎስን ለመርዳት ፍላጎት አላቸው ዕድሉን ግን አላገኙም።
-      ጊዜ አጣችሁ - ያለው - ዕድል አጋጣሚውን አላገኛችሁም። - ለማለት ነው።
*. አገልጋዮችን፣ የተቸገሩ ክርስቲያን ወንድሞችን ስለመርዳት - 
 እነርሱ ፍለጎት አላቸው፣ ዕድል አላገኙም፤ ባሁኑ ጊዜ ግን ዕድሉ አለ፣ ፍላጎት ያለው ሰው የለም።
-      ጳውሎስ ስለደስታ፣ እርካታ - ይናገራል - ከምዕራፉ መጀመሪያ አንስቶ - በጌታ ደስ ይበላችሁ።
-      የእኔ እርካታ - ከማግኘትም፣ ከማጣትም አይደለም። እነዚህን ነገሮች ተምሬያለሁ- በተግባር አይቻቸዋለሁ።
-      ደስታ ከሃብት፣ ሃዘን-ከድኅነት አይደለም። እንዲያውም ብዙ ችግር/ሃዘን የሚገጥማቸው ከድሆች ይልቅ ሃብታሞች ናቸው።
-      የሚመጣውን ነገር ሁሉ - ማግኘትን ማጣትን፣ ሁሉን በክርስቶስ እችላለሁ፡ - እቀበላለሁ፣ አስተናግዳለሁ
-      ስለዚህ - ክርስቶስ ካለኝ ሁሉ አለኝ -ይበዛልኝማል- ይላል ቁ. 18።
ትልቁ ችግራችን ጉድለት ነው።
ጉድለት ምንድን ነው? ሙላት ምንድን ነው? በምን ይለካል?


ዓለም በጉድለቶች የተሞላች ናት። ፱ ናት ይባላል። ለምንድን እንዲህ ሆነ?
ዕንባቆም ፫፣፲፯-፲፰፡ እንደተጻፈው
ምንም እንኳ በለስም ባታፈራ፥ በወይንም ሐረግ ፍሬ ባይገኝ፥ የወይራ ሥራ ቢጐድል፥ እርሾችም መብልን ባይሰጡ፥ በጎች ከበረቱ ቢጠፉ፥ ላሞችም በጋጡ ውስጥ ባይገኙ፥…እኔ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል በመድኃኒቴ አምላክ ሐሤት አደርጋለሁ።
በጉድለት ውስጥ በእግዚአብሔር እንዴት መደሰት ይቻላል?
በ፫ ሃሳቦች እናየዋለን።
፩. የጎደለብን በትክክል ምንድን ነው?
-       ለመጀመሪያው ሰው ለአዳም - መልካምና ክፉ የምታስታውቀው ዛፍ- አትብላ ተብሏል።
እግዚአብሔር መብልን ሳይሆን ከመብሎች አንዱን ከለከለው።
የሕልውና ጉዳይ አይደለም፣ ሌሎችን እየበላ መኖር ይችላል።
ከእርሱ በኋላ ብዙ አባቶች በመጽሐፍ ቅዱስ የተለያዩ ጉድቶች ነበሩአቸው።
-      እኛስ አሁን የጎደለን ምንድን ነው?- ገንዘብ፣ ሥራ፣ ትዳር፣ ጤና፣ ሰላም፣ ቤት፣ ልብስ….
እነዚህ የኑሮ ጉዳዮች እንጂ የሕይወት ጉዳዮች አይደሉም። ያለእነዚህ /አንዱ/ መኖር ይቻላል።
ከሕይወት ጋር የተያያዙ.. አየር፣ ጊዜ /ዕድሜ/፣ ፀሐይ፣ …. አሉ። ያለእነዚህ /አንዱ/ መኖር አይቻልም።
-      በትክክል ካስተዋልነው፡ ከጎደለን እና ካለን የትኛው ይበልጣል። ያለን ይበልጣል።
የሚበላው ሞልቶ የሚሞት፣ የሚበላው አጥቶ የሚኖር ብዙ ሰው አለ። … እንደተባለ።
-      የብዙ ነገሮች መሟላት ለኑሮ እንጂ ለሕይወት ዋስትና አይሆንም።
ሕይወት በአንድ አምላክ እጅ ናትና።
-      ብዙ ነገሮች ስለጎደሉብን አንሞትም። ሞት ጥሪ ነውና።
-      አለን የምንለው ነገር ሁሉ ሞትን አያስቀርልንም፣ ጎደለን የምንለውም ሁሉ መኖርን /ሕይወትን አያስቆማትም።
ሕይወትና ሞት ከቁጥጥራችን ውጭ ናቸውና። ሙሉ በሙሉ በአምላክ እጅ ናቸው።
ይሄም ሆኖ የሆነ ነገር ጎድሎናል እንበል። ነገር ግን፡-
. የጎደለብን የሚጎላብን ለምንድን ነው?
ሰይጣን በዚች ዓለም ጊዜያዊ ስልጣን ስላለው ከተሰጠን ይልቅ የጎደለብንን አጉልቶ ስለሚያሳየን ነው።
አዳምና ሔዋንን የጠየቃቸው የተሰጣቸውን ሳይሆን የጎደላቸውን ነው።
ዘፍ ፫፣፩- «በውኑ እግዚአብሔር ከገነት ዛፍ ሁሉ እንዳትበሉ አዞአልን?»
-      ምን ሰጣችሁ? .. ቢላቸው.. ሲዘረዝሩ ይመሻል፡
-      ምን ጎደላችሁ? … አላቸው። /ጥበበኛ ነው። ክብሩ እንጂ ጥበቡ አልተነፈገውም።
ከተሰጣቸው ብዙ የተከለከሉትን አንድ ጠየቃቸው።… አስታወሳቸው… አጎላባቸው። ሌላውን እንዳያዩ ሸፈነባቸው።…ስለዚህ ለምን? እያሉ መጠየቅ ጀመሩ…. ለምን?
/እግዚአብሔር ለምን ጉድለትን በሕይወታችን አስቀመጠ?... በኋላ እናየዋለን።/
-      ክርስቶስ የተፈተነው በረሃቡ ጊዜ /እርቦት ሳለ/ ነው። በጉድለት /በችግር/
ማቴ ፬፣፪፡ አርባ ቀንና አርባ ሌሊትም ከጦመ በኋላ ተራበ።
ፈታኝም ቀርቦ። የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህ፥ እነዚህ ድንጋዮች እንጀራ እንዲሆኑ በል አለው።
ሰይጣን ጉድለታችን ያጠናል፤ ያገኛል። በዚያን ጊዜ ይቀርባል።
ክርስቶስን ከፈተነ የክርስቶስ የሆኑትን /ክርስቲያኖችን -- እኛን/ በደንብ ይፈትነናል።
ሰይጣን የእርሱ የሆኑትን አይነካም። የክርስቶስ የሆኑትን ግን ያለሟቀረጥ ይታገላል።
፩ጴጥ ፭፣፰ «በመጠን ኑሩ ንቁም፥ ባላጋራችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሣ አንበሳ ይዞራልና፤»
-      ሰይጣን በኛ ላይ ሥልጣን የለውም። ሲፈትነንም ከእግዚአብሔር እውቅና ውጭ አይደለም። በኢዮብ ታሪክ ይህን እናውቃለን።
ሰይጣን ጉድለታችን እንዴት ያውቃል? … የልባችን አያውቅም። ነገር ግን
ከአንደበታችንና ከእንቅስቃሴያችን ይረዳል።
በጉድለታችን ስናማርር ችግሮች እየተባባሱ ይሄዳሉ። እርሱ ስለሚሰማ፡ እና በውጊያው ስለሚገፋበት…..

ሰይጣን በጉድለታችን ይፈትነናል። እግዚአብሔር ይህን እያወቀ ለምን ዝም ይላል? 
ይቀጥላል..... 
DAT27

No comments:

Post a Comment

አስተያየትዎን ይስጡ / Give Comment