Tuesday, November 18, 2014

የሰናፍጭ ቅንጣት - ክፍል ፪

1.     ከምሳሌው ምን እንማራለን?
1.     የሰናፍጭ ዘር --- ወደ ዛፍነት ያድጋል
Ø  ከሁሉ ያነሰና ከግምት የማይገባ ጥቂት ጅማሬ -- ወደ ታላቅ ግብ ይደርሳል።
Ø  ከቅንጣት - የጎላ ዕድገት ይወጣል
² በሥጋዊ አካል ስናየው የወንድ ዘር በዓይን የማይታይ ረቂቅ ነው፤ የሴትም እንቁላል በጣም ትንሽ ናት። ከእነዚህ ውህደት ጽንሱ ሲፈጠር በእጅ ጭብጥ አይሞላም።
² ከዚህ ውስጥ ግን የተለያየ አካል ይወጣል። ያድጋል። -- በመንፈሳዊውም እንዲሁ ነው።
Ø  የእግዚአብሔር መንግሥትም እንዲሁ ነው።
ክርስቶስ መንግሥቱን ለመመስረት በዚች ምድር ሲወለድ - የተናቀ፣ የተሰደደ፣ ብቻውን ነበረ።
በኋላ 12 ሐዋርያትን -ቀጥሎ- 120 ቤተሰብ -ከዚያ- 3ሺ-- 5ሺ --እያለ ዛሬ ክርስትና በመላው ዓለም ተስፋፋ። ወደፊትም ይቀጥላል።
²  የቤተክርስቲያን /የክርስቲያኖች/ እድገት እንዲሁ ነው።
2.    የሚያድገው መጀመሪያ በመሞት ነው።
Ø  ዘሩ ወደ መሬት ወደቆ - ይሞታል - በኋላ ይነሳል። -- እንደ ክርስቶስ ትንሣኤ
አንተ ሞኝ፥ አንተ የምትዘራው ካልሞተ ሕያው አይሆንም፤
የምትዘራውም፥ ስንዴ ቢሆን ከሌላም ዓይነት የአንዱ ቢሆን፥ ቅንጣት ብቻ ነው እንጂ የምትዘራው የሚሆነውን አካል አይደለም፤
እግዚአብሔር ግን እንደ ወደደ አካልን ይሰጠዋል ከዘሮችም ለእያንዳንዱ የገዛ አካሉን ይሰጠዋል።
፩ ቆሮ ፲፭፣ ፴፮ - ፴፰።
Ø  የእግዚአብሔር ሰማያዊ መንግሥት - በምድር - በክርስቶስ ሞት እና ትንሣኤ ተመሠረተ። ሰዎች የዘላለም ሕይወት /መንግሥተ ሰማያት የሚወርሱት ሞቱንና ትንሣኤውን ሲያምኑ ነው።
Ø  ይህንን የሕይወት የእግዚአብሔር መንግሥት ጥሪ ከአገልጋዮች እንደተቀበልነው እኛም ለሌላውም ማስተላለፍ አለብን።
Ø  ለማደግ- መውረድ፣ ከፍ ለማለት -ዝቅ ማለት የክርስትናው መሠረታዊ መመሪያ ነው።
Ø  ለሌሎች ለመትረፍ፣ ሌሎችን ለማዳን በቅድሚያ ለእኔነት መሞት ያስፈልጋል።
ክርስቶስ በኖረበት ዘመን ሁሉ የእኔ የሚለው አልነበረውም። ለእኔም አላለም።
አንድ መምህር እንዳለው፣ -« ክርስቶስ መለኮታዊ ኃይሉን ሌሎችን ለመርዳት እንጂ ራሱን ለማዳን አንድ ጊዜም አልተጠቀመም።»
Ø  ስለዚህ - ለእኔ - ከሚለው በፊት ለወገኔ - የሚለው ከቀደመ- ወንጌሉ / መንግሥቱ ይስፋፋል፤ - ትርፉ እንኳን በመንፈሳዊ - በሥጋዊም ጭምር ነው። መልካምነትም ይበዛል፤ ችግረኞችን አናይም፤
3.   በአደገች ጊዜ -- ራሷን ትችላለች


Ø  ዘር ተሸካሚ ትፈልጋለች -- ትንሽ ስለሆነች -- በእጅ ትያዛለች ፤
Ø  ስትዘራ መሬት ላይ ትወድቃለች፣ መጀመሪያ ወደ ታች ታድጋለች። - ለውጭው ዓለም አትታይም።
² ሥር - መሠረት ትይዛለች -- ለመቆም- ለማደግ።
² ያለመሠረት መቆም/ ማደግ አይቻልም።
Ø  በቃሉ ዕውቀት፣ በእምነት ጽኑ መሠረት መያዝ አለብን።
² ነፋስ ሲነፍስ ፣ ጎርፍ ሲመጣ በአለት ላይ እንደተመሠረተው ቤት ለመጽናት።
²  የአንዱ ክርስቲያን መንፈሳዊ እድገት /በእምነት ማደግ/ እንዲሁ ነው። - በብርታት።
4.   የሰማይ ወፎች በቅርንጫፍዋ እስኪሰፍሩ ድረስ
Ø  ስታድግ፣ ራሷን ችላ ስትቆም - ፍሬ ታፈራለች።
² ሀ. መሰሏን ታስገኛለች፡ -- ፍሬዋ ውስጥ ዘር አለ።
ትበዛለች - ብዙ ፍሬና ብዙ ዘር ትሰጣለች።
² ለ. ለሌሎች ማረፊያ ትሆናለች። -- ሌሎችን ትሸከማለች።
በቅርንጫፎቿ አእዋፍ ጎጆ ይሠሩባታል።
² ሐ. ጥላዋ ያሳርፋል።-- ትልቅ ስለሆነች በበታቿ ጥላ አለ።
ከፀሐይ ግለት ማረፊያ ትሆናለች።
Ø  ወፎች እስኪመጡና እስኪሰፍሩባት ደረስ--- ለምን ሲሉ ነው የሚሰፍሩባት?
² ለሁለት ነገር፡- በጥላዋ ለማረፍ እና ከፍሬዋ ለመመገብ፤
² ወፎች - ይመጣሉ - ፍሬውንና ጥላውን አይተው።
Ø  ቤተክርስቲያን የመንግሥቱ አስፈጸሚ - በምድር ያለች የሰማይ መንግስት ኤምባሲ ናት።
ዛሬ የቤተክርስቲያን እድገት የሚለካው በምንድን ነው? -
² በሕንጻው ቁመትና ስፋት? በምእመናን ብዛት?- -አይደለም። እንደ ሰናፍጭ ዛፍ በሁለት ነገር፡-
l  1. በፍረያማነቱ፣ በቃሉ ሕይወትን የሚለውጥ በመሆኑ -  
l  2. በመጠለያነቱ፡ የሕዝቡን ሸክም የሚያሳርፍ በመሆኑ-
²  ሌሎችን - እንዲመጡ -  የሚያደርግ የሚጠራ ፍሬ እና ጥላ /መጠለያ/ አለን?
ወይስ እንኳን ሌሎችን የሚጠራ - ያሉትን የሚያባርር - ማንነት ነው ያላት?
²  /ባለፈው የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ (ጥቅምት / 2007) ከተያዙት አጀንዳዎች መካከል አንዱ - የምእመናን ቁጥር መቀነስ - ይላል። እንዴት ቀነሰ? ለምን? --- ብለን እንኳ አንጠይቅም።
l  የሕዝብ ብዛት እየጨመረ፣ ወንጌልም በተለያየ የመገናኛ ዘዴ እና የቴክኖሎጂ ውጤት እየተሰበከ እየተስፋፋ ባለበለበት ዘመን- የምዕመናን ቁጥር መጨመር አልነበረበትምን?
እኛ ግን - ባለበት እንኳ ማቆየት አልቻልንም። ለምን?
² የእኛ ቤተክርስቲያን ከዕድሜዋ ጋር አሁን በአገልግሎት ማደግና መስፋፋት ሲገባት - ቁልቁል እየሄደች ነው። እግዚአብሔር ግን በሥራ ላይ ነው። በተለያዩ መንገዶች መንግሥቱ እየሰፋ ነው።
Ø  በተናጠልም ስናየው የክርስቲያንነት እድገታችን የሚለካው በምንድን ነው? - በቁመት፣ በውፍረት? በብልጸግና?... አይደለም። አንደዛፉ በሁለት ነገር ነው።
² በፍሬያችን - በኑሯችን ፍሬ
² ለሌላው በመትረፋችን - ለሌሎች በመድረሳችን፣
-      በአጠቃላይ የእግዚአብሔር መንግሥት በአንድ ሰው በክርስቶስ ተመሥርታ፣ በሐዋርያት ተጀምራ ዛሬም ድረስ እየሰፋች እያደገች በመሄድ ላይ ነች። -ለዕድገቷ- የየራሳችንን ድርሻ እንወጣ።
-      የሰናፍጭ ቅንጣት፡- ሌላ ቦታ የተመሰለችው ስለ እምነት ነው።
Ø  ኢየሱስም፦ ስለ እምነታችሁ ማነስ ነው፤ እውነት እላችኋለሁ፥ የሰናፍጭ ቅንጣት የሚያህል እምነት ቢኖራችሁ፥ ይህን ተራራ። ከዚህ ወደዚያ እለፍ ብትሉት ያልፋል፤ የሚሳናችሁም ነገር የለም።
ማቴ 17፣ 20
²  - ሦስት ዓይነት እምነት አለ። የምንድንበት፣ የምንኖርበት፣ እና የተሰጥኦ/የተአምራት እምነት።
²  - ስለምንኖርበት እምነት ነው፡- እንደተራራ የገዘፈው ትልቁ ችግር በትንሽ እምነት ሊወገድ ይችላል የሚል ሃሳብ ያለው ነው።

/የዚህን ዝርዝር በሌላ ጊዜ እናየዋለን።/

No comments:

Post a Comment

አስተያየትዎን ይስጡ / Give Comment