Wednesday, November 12, 2014

የሰናፍጭ ቅንጣት ክፍል ፩


ሌላ ምሳሌ አቀረበላቸው እንዲህም አለ፦ መንግሥተ ሰማያት ሰው ወስዶ በእርሻው የዘራትን የሰናፍጭ ቅንጣት ትመስላለች፤
እርስዋም ከዘር ሁሉ ታንሳለች፥ በአደገች ጊዜ ግን፥ ከአታክልቶች ትበልጣለች የሰማይም ወፎች መጥተው በቅርንጫፎችዋ እስኪሰፍሩ ድረስ ዛፍ ትሆናለች።   ----  ማቴ 13፣ 31-32/
-      ጌታችን ስለመንግሥቱ በምሳሌ አስተማረ - ለምን?
Ø  ራሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ለምን በምሳሌ እንደሚያስተምር ተጠይቆ የመለሰው ምክንያት፡-
²  ደቀ መዛሙርቱም ቀርበው። ስለ ምን በምሳሌ ትነግራቸዋለህ? አሉት።
እርሱም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ ለእናንተ የመንግሥተ ሰማያትን ምሥጢር ማወቅ ተሰጥቶአችኋል፥ ለእነርሱ ግን አልተሰጣቸውም።
ላለው ይሰጠዋልና ይበዛለትማል፤ ከሌለው ግን ያው ያለው እንኳ ይወሰድበታል።
ስለዚህ እያዩ ስለማያዩ እየሰሙም ስለማይሰሙ ስለማያስተውሉም በምሳሌ እነግራቸዋለሁ።
ማቴ 13፣ 10 – 13።
²  ሐዋርያት በክርስቶስ አምነው የእግዚአብሔር ልጆች ስለሚሆኑ - ምሥጢር ማወቅ ተሰጥቷችኋል አላቸው።
²  ለሌሎች ግን ገና በኃጢአት፣ በጨለማ ውስጥ ስላሉ የመንግሥቱን ነገር ማወቅ አይችሉም።
Ø  የዕውቀት ውስንነት - በኃጢአት/ በውድቀት ከነበሩን ሦስት የነፍስ መልኮች ፣ ዕውቀት፣ ቅድስና እና ጽድቅ -- እውቀታችን ጎደለ። - ይህን ክፍተት ለመሙላት - ምሳሌ አስፈለገ።
Ø  የስሜት ውስንነት- በውስን ተፈጥሯችን፣ በአምስቱ የስሜት ሕዋሳት የማንገነዘባቸው ብዙ ነገሮች አሉ። ስለዚህ በምናያቸው ነገሮች መግለጽ የግድ ነው።
Ø  ምሳሌው የእኛን ደካማነት ብቻ ሳይሆን - የእርሱን ጥበበኛነት ያሳያል። ጥበበኛ መምህር ነው።  
-      አባቶች ምሳሌ ዘየሐጽጽ ይላሉ።- ምሳሌ - ከሚመሰልለት ነገር ያንሳል፣ በማነሱ ግን ትልቅ ነገርን ያብራራል፧
-      ዓለምን/ ምድራችንን በሉል - መስለን እንማራለን፡፡
-      ጥበብሰ መድኃኒነ ውእቱ እንደተባለው በቅዳሴ ጥበብ የተባለው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወሰን የሌለውን እጅግ ታላቅ የሆነውን መንግሥተ-ሰማያት፣ -መጠን በሌላት -እጅግ ታናሽ በሆነች- በሰናፍጭ ቅንጣት -መስሎ አስተማረ። የሚገርም ምሳሌ ነው።
-      የእግዚአብሔር መንግሥት በሰናፍጭ ቅንጣት የተመሰለችው በዚህ ዓለም ሳለች ነው። ጅማሬዋ ነው። ፍጻሜዋ ግን በሰማይ ነው። ሩቅ አና ረቂቅ ነው።
-      የሰዎች መንግሥት በኃያልነት፣ በታላቅነት ሊገለጽ ይችላል።
Ø  የድሮ መንግሥታት / ነገሥታት ኃያልነት የሚታወቀው በግዛታቸው ስፋት… መሬት /ቅኝ ግዛት በማስፋፋት ነው።
²  የዓለም ጦርነቶች የተካሄዱት በአብዛኛው በድንበር ግጭት እና ከቅኝ ግዛት ነጻ ለመውጣት ነው።
Ø  የዚህ ዘመን መንግሥታት -- የአሜሪካ መንግሥት፣ የእንግሊዝ መንግሥት -- ኃያላን ሃገራት - የተባበሩት መንግሥታት… በጦር ኃይላቸው፣ በኢኮኖሚያቸው፣ ወዘተ.. ኃያልነታቸውን ይገልጻሉ።
²  እነዚህ ሁሉ የፈለገ ኃያላን ቢሆኑ - ይወድቃሉ፣ ያልፋሉ። - ከዚህ ቀደም የነበሩ ኃያላን መንግሥታት አልፈዋል።
Ø  የእግዚአብሔር መንግሥት ግን በዚች ምድር - እዚህ ግባ በማትባል - በአንዲት ዛፍ - ፍሬ- ዘር - በሰናፍጭ ቅንጣት- ተመስላለች። -
²  ስትጀመር / ስትመሠረት መሬት ወድቃ የምትጠፋ / የጠፋች/ ትመስላለች። ግን ትወጣለች ታድጋለች። -- የሚገድባትም የለም።
²  በአንዱ በክርስቶስ ሞት የተመሠረተው የእግዚአብሔር መንግሥት ለዓለም እና ለዘላለም ስለሚቀጥል እስከዛሬ በመላው ዓለም ተስፋፍቷል፣ በሰማይም ለዘላለም ይቀጥላል።
Ø  የሰዎች / አገሮች መንግሥታት የሚመሰረቱት - በኃይል እና በጦርነት--- በመግደል ነው። ስለዚህ መስራቾቹ ይገድላሉ - በኋላ ግን እነርሱ ይሞታሉ። መንግሥታቸው በሌላ መንግሥት ይተካል።
በታሪክ እንደታየው ብዙ ጊዜ የመንግሥት ለውጥ የሚደረገው በኃይል እና በጦርነት ነው።
Ø  የእግዚአብሔር መንግሥት ግን የተመሠረተችው በመሞት ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ በመሞት ተከታዮቹም ይሞታሉ - በኋላ ግን ክርስቶስ እንደተነሳ ሕያው ይሆናሉ።
-      ዛፍ የመንግሥት ምሳሌ ሆኖ የቀረበው በዳንኤል ዘመን ለንጉሡ ለናቡከደነጾር መንግሥት ነው። /በሕልም/
Ø  …..ቅጠሉም አምሮ የነበረው፥ ፍሬውም የበዛው፥ ለሁሉም መብል የነበረበት በበታቹም የምድር አራዊት የተቀመጡ፥ በቅርንጫፎቹም የሰማይ ወፎች ያደሩበት ያየኸው ዛፍ - ንጉሥ ሆይ፥ እርሱ ታላቅና ብርቱ የሆንህ አንተ ነህ ታላቅነትህ በዝቶአል፥ እስከ ሰማይም ደርሶአል፥ ግዛትህም እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ነው።   ዳን 4፣ 10 – 12 ፡ 20 -22።
1.     የምሳሌው አስፈላጊነት
-      ሰይጣን የእግዚአብሔርን ቃል መሰራጨት እና የወንጌሉን መስፋፋት ይቃወማል። ከምሳሌዎች ዝርዝር ከላይ በእርሻው መካከል እንክርዳድ እየዘራ እንደሚቃወም። ማቴ 13፣24 - 28
ይህ ከሆነ የእግዚአብሔር መንግሥት እንዴት ይስፋፋል? የሚለውን ለማብራራት ነው።
2.    የዘሩ / የዛፉ ጠባይ / Biological Characters/
-      የሰናፍጭ - -ቅንጣት -- በምድር ካለ ዘር ሁሉ ታንሳለች። - በመጠንም ፣ በክብደትም።
Ø   በመጠኑ፡- (ስፋት..) - ሊለኩ ከሚችሉ ነገሮች ሁሉ እጅግ ያነሰ
²  ክብደቱ - ሊመዘኑ ከሚችሉ ነገሮች ሁሉ እጅግ የቀለለ
Ø  የጎመን ዘር ዓይነት ሆኖ ፍሬው በጣም ትንሽ ነው።፣  - በነፍሳት በቀላሉ የማይጠቃ።
Ø  በብዙ ዓይነት አፈር በቀላሉ ሊበቅል የሚችል፣ ከፍተኛ የአየር ንብረት ለውጥ የሚቋቋም።
Ø  ፍሬው ውስጥ ያለው ዘሩ በጣም ደቃቅ ሲሆን የዛፉ ቁመት ግን ረጅም ነው፡
እንደዘሩ ዓይነት፣ እንደአፈሩ እና አየሩ ሁኔታ በአንድ ዓመት ከ4 – 10 ሜትር ያድጋል።
Ø  አእዋፍ እስኪሰፍሩበት ድረስ -- ሌሎችን እስኪሸከም ድረስ ያድጋል። ይጠነክራል።
ከምሳሌው ምን እንማራለን?
 ---------ይቀጥላል
----ይቆየን፤

No comments:

Post a Comment

አስተያየትዎን ይስጡ / Give Comment