Tuesday, February 28, 2017

እኔስ የመረጥሁት ጾም ይህ አይደለምን? (ክፍል ፪)

Chosen Fasting by God p 2 , READ IN PDF
ባለፈው ጽሑፋችን በትንቢተ ኢሳይያስ ምዕራፍ ፶፰ ስለጾም በሚናገረው ክፍል ጾማችን ምን መምሰል እንዳለበትና ምን መምሰል እንደሌለበት በማየት ከጥልና ከክርክር በመራቅ፡ በመልካም ምግባር መታጀብ እንዳለበት የሚገልጸውን የመጀመሪያውን ክፍል አይተናል። በዚህ ክፍል በጾማችን የምናገኘውን በረከት እናያለን።
ትንቢተ ኢሳይያስ ምዕራፍ ፶፰፡-
ቁ. ፰. የዚያን ጊዜ ብርሃንህ እንደ ንጋት ይበራል፥ ፈውስህም ፈጥኖ ይበቅላል፥ ጽድቅህም በፊትህ ይሄዳል፥ የእግዚአብሔርም ክብር በኋላህ ሆኖ ይጠብቅሃል
የዚያን ጊዜ የሚለው ቃል ከላይ ከነበረው ጉዳይ ጋር አያያዥ ነው። በክፍል ፩ ካየነው ሃሳብ የሚቀጥል ነው። ጾማችን ምን መምሰል እንዳለበት ተረድተን በተግባር የፈጸምነው እንደሆነ፡ ለሌሎች የነፍስ መዳን ንስሐን በማሰብ ከጠብና ክርክር በመራቅ፡ ፣ በፍቅር፡ በመልካም ምግባር፡ የተራበን በማብላት፡ የተጠማን በማጠጣት የታረዘን በማብላት…. የታጀበ ከሆነ የዚያን ጊዜ  የምናገኛቸውን በረከቶች ይዘረዝራል። ብርሃን፡ ፈውስ፡ ጽድቅ፡ ጥበቃ።
-  ብርሃን፡- ጨለማን የሚያስወግድ ክስተት ነው፡፡ በዓለም ለተፈጥሮው ጨለማ የፀሐይ ብርሃን ይወጣል። የሕይወት ጨለማ ለሆነው ጭንቀት፡ ተስፋ መቁረጥ ብርሃን ያስፈልጋል። ይህም ብርሃን በጌታ በደስታ በእረፍት ያለጭንቀት መኖር፡ነው። ጨለማ አያሳይም፡ ምንም የሕይወት ተስፋ በሌለበት፡ ምን እበላለሁ? ምን እጠጣለሁ?... ብለን ከምንጨነቅበት ሁኔታ ያስወጣናል፡ ሕይወታችን ይመራል። ምድራዊ በረከትን ያመለክታል።
- ፈውስ፡-  የሥጋም የነፍስም ሊሆን ይችላል። ለሥጋ በሽታ ሃኪም መድኃትን ቢያዝም ፈውስ ግን ከእግዚአብሔር ነው። ጾም ለበሽታ ፈውስ አንዱ መሣሪያ እንደሆነ ጌታ ተናግሮአል።«ይህ ዓይነት ግን ከጸሎትና ከጦም በቀር አይወጣም አላቸው።» ማቴ ፲፯፡፳፩።  የነፍስ በሽታ ኃጢአት ነው። በክርስቶስ በማመን የምናገኘውን የነፍሳችን ድኅነት (መዳን) ጠብቀን የምናቆየው በጾምና ጸሎት (በአምልኮ) እና በቅድስና በመኖር ነው። ስለዚህ ጾም የነፍሳችንን መዳን (ፈውስ) ለማቆየት አንዱ መሣሪያ ነው። ፈውስ ወይም መዳናችን እስከመጨረሻው ከጸና ለፍሬ ይደርሳል። እስከዚያ መብቀል (ማደግ) አለበት። ለዚህም ጾም ያስፈልጋል ማለት ነው። ፈውስህ ፈጥኖ ይበቅላል።.. ለፍሬም ይደርሳል። ማለት ነው። ለመንፈስ ቅዱስ ፍሬ። (ገላ ፭፡፳፪)
 
- ጽድቅህ ፡-እግዚአብሔር በልጁ እኛን ያዳነበት (ያጸደቀበት)፡ በቸርነቱ ወደእርሱ የምንቀርብበት ብቃት ነው። ይህም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። «አሁን ግን በሕግና በነቢያት የተመሰከረለት የእግዚአብሔር ጽድቅ ያለ ሕግ ተገልጦአል፥ እርሱም፥ ለሚያምኑ ሁሉ የሆነ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የሚገኘው የእግዚአብሔር ጽድቅ ነው፤ ልዩነት የለምና፤» ሮሜ ፫፡ ፳፩-፳፪፡፡ይህን ነገር ሁልጊዜ በፊታችን ልናዘክረው የሚገባ ጉዳይ ነውና በፊትህ ይሄዳል ተባለ።
ጥበቃ፡  ሰዎች ስለሆንን የፊታችንን እንጂ የኋላችን ማየት አንችልም። ከማናየው ከኋላችን የሚጠብቀን የሚከተለን የእግዚአብሔር ክብር ነው። የእግዚአብሔር ክብር ከኛ ጋር የሚቆየውም እኛ ከርሱ ጋር በጾም፡ በጸሎት ስንገናኝና ስንጸና ነው።
ቁ.፱  የዚያን ጊዜ ትጠራለህ እግዚአብሔርም ይሰማሃል ትጮኻለህ እርሱም፦ እነሆኝ ይላል። ከመካከልህ ቀንበርን ብታርቅ፥ ጣትህንም መጥቀስ ብትተው፥
ከላይ የተናገረውን በአጽንኦት በመድገም፡ ቀንበርን በሌሎች የምናደርሰውን ግፍ በማቆም፡ ጣት መጥቀስ ወደ ሌላው በጥፋተኝነት መክሰስን ብናቆም የዚያን ጊዜ ጸሎታችን ይሰማል። ወደ እግዚአብሔር የምንጣራውና የምንጮኸው በጸሎት ነው። ስለዚህ ከጾማችን ጋር የሚለንን ከታዘዝን እርሱም የምንለውን፣ የምንለምነውን ይሰማናል። ስንጠራው «እነሆኝ» - አለሁ- ይለናል። ይህ መልሱ ብቻ ጉልበት ነው። ክብር ለርሱ ይሁን።
ቁ ፲  ባታንጐራጕርም፥ ነፍስህንም ለተራበ ብታፈስስ፥ የተጨነቀውንም ነፍስ ብታጠግብ፥ ብርሃንህ በጨለማ ይወጣል ጨለማህም እንደ ቀትር ይሆናል።
ይህም ለአጽንኦት በድጋሜ የተነገረ ነው። ጨለማና ብርሃን መጠቀሳቸው እስራኤላውያን ከግብጽ ባርነት ነጻ ሲወጡ ጉዞአቸው በቀንና በሌሊት ስለነበረ ቀን በደመና፡ ሌሊት በዓምደ ብርሃን ይመራቸው ነበር። ስለዚህ አሁን ያሉት አይሁድ እንደአባቶቻቸው ሕይወታቸውን እንደሚመራ እያስታወሳቸው ነው።
ባታንጎራጉር- ባታማርር። ነፍስህን ሲል ራስን፡ ሁለመናን ያመለክታል። ለተራቡት ገንዘባችንን ብቻ ሰጥተን ዘወር ማለት ሳይሆን ጊዜያችንን፡ ጉልበታችንን፡ በመስጠት በፍቅር ቃል ማጽናናት… የተጨነቀውን ነፍስ በሁለመናው ችግር ያለበትን በረሃብ…. በብቸኝነት…ያሉትን ማጽናናት አለብን። ይህ ጌታ ከኛ የሚፈልገው ትልቅ ጉዳይ ስለሆነ ደገመው። ይህን ካደረግን ብርሃን በተባለው ምድራዊ በረከት ይሞላናል። ጨለማን በቀትር ማሰብ አይቻልም። የሚያስጨንቀን አንዳች ነገር ፈጽሞ አይኖርም ማለት ነው። እርሱ የሚሰጠን እረፍት ፍጹም ሙሉ ነውና።
ቁ ፲፩. እግዚአብሔርም ሁልጊዜ ይመራሃል፣ ነፍስህንም በመልካም ነገር ያጠግባል፤ አጥንትህንም ያጠናል፤ አንተም እንደሚጠጣ ገነት፥ ውኃውም እንደማያቋርጥ ምንጭ ትሆናለህ።
   ለአይሁድ አባቶቻቸውን ከግብጽ አውጥቶ የመራ ዛሬም ሕይወታቸውን ይመራል። በሲና በረሀ ውኃ ከዓለት ያፈለቀላቸው እና ያጠጣቸው ጌታ ዛሬ እነርሱ የሌሎችን ጥማት እንዲያረኩ ምንጭ ያደርጋቸዋል።
የሕይወት መሪ ሁልጊዜ እግዚአብሔር ከሆነ የሚያሰጋን የለም። ነፍስህን ሲል ሁለንተናን ያመለክታል። ከላይ ቁ. ፲ ነፍስህን … ብታፈስስ.. ብታጠግብ … ሁለንተናችን ለተቸገሩት ስንሰጥ አሁን ጌታ ሁለንተናችን እርሱ ደግሞ ይሞላል ማለት ነው። ሌሎችን የምንረዳው አንድ ቀን ውለታ ይመልሳሉ ብለን በብድር መንፈስ ሳይሆን እግዚአብሔር ይሰጠኛል ብለን በእምነት ሊሆን ይገባል። አጥንትህንም ያጠናል፡- እግዚአብሔር እንደሚያበረታን ያሳያል። አሁን በእግዚአብሔር ስንበረታ ለሌሎች እንተርፋለን.. እንደሚጠጣ ገነት፡ አንደማያቋርጥ ምንጭ…. በጾምና ጸሎት ከእግዚአብሔር ጋር ሆነን የምንቀበለው በረከት ከኛ አልፎ ለሌሎች ይደርሳል።
ቁ.  ፲፪  ከዱሮ ዘመን የፈረሱት ስፍራዎች ይሠራሉ፥ የብዙ ትውልድም መሠረት ይታነጻል አንተም። ሰባራውን ጠጋኝ፥ የመኖሪያ መንገድን አዳሽ ትባላለህ።
ከምርኮ መልስ እስራኤላውያን የፈራረሱ ከተሞቻቸውን እንደሚሠሩ በልጆቻቸው የፈራረሰው ተስፋ እንደሚታነጽ ይነግራቸዋል።
ለዘመናት የፈረሱ - ከእግዚአብሔር ርቀው የሚባዝኑ ብዙዎች ናቸው። ትውልዱም መሠረት የለውም፣ እንደዘመኑ ተለዋዋጭ ነው። በአንድ ጌታ እና በእምነቱ ስላልጸና ወዲያ ወዲህ ስለሚል ለውድቀት ይዳረጋል፡፡ ስለዚህ ለትውልድ መታነጽ የሚተርፍ በረከት ከጾም ሊገኝ ይችላል ማለት ነው። እርሱ በሚወደው መልኩ በምንጾመው ጾም የምናገኘው በረከት ከእኛ አልፎ ለሌላው ሲተርፍ እስከብዙ ዘመንና ብዙ ትውልድ ድረስ የሚዘልቅ ይሆናል።
ቁ. ፲፫ና ፲፬  
ፈቃድህን በተቀደሰው ቀኔ ከማድረግ እግርህን ከሰንበት ብትመልስ፥ ሰንበትንም ደስታ፥ እግዚአብሔርም የቀደሰውን ክቡር ብትለው፥ የገዛ መንገድህንም ከማድረግ ፈቃድህንም ከማግኘት ከንቱ ነገርንም ከመናገር ተከልክለህ ብታከብረው፥
በዚያን ጊዜ በእግዚአብሔር ደስ ይልሃል፥ በምድርም ከፍታዎች ላይ አወጣሃለሁ፥ የአባትህንም የያዕቆብን ርስት አበላሃለሁ የእግዚአብሔር አፍ ተናግሮአልና።
ይህ የመጨረሻው ክፍል የሰንበትን አከባበር እና የሚገኘውን በረከት ይናገራል። አይሁድ በምርኮ ጊዜ ሰንበትን ከማያከብሩ ሕዝቦች ጋር ስለቆዩ አሁን ወደ ሃገራቸው ሲመለሱ ሰንበትን እንዲያስቡ እያስታወሳቸው ነው። ከ፲ቱ ትዕዛዛትም ሰንበትን አክብር አንዱ ነው። ዘጸ ፳፡ ፰፤
በሰንበት ቀን (በብሉይ ኪዳን ቅዳሜ፡ በሐዲስ ኪዳን እሑድ- ሰንበተ ክርስቲያን) ለጌታ የተለየ ቀን ስለሆነ ከማንኛውም ሌሎች ተግባራት በመለየት በልዩ ሁኔታ ማክበር ተገቢ እንደሆነ ያስተምረናል። የገዛ መንገድህ ከማድረግ .. ተከልክለህ… ብታከብረው ሲል በሰንበት የራሳችን ዕለታዊ ጉዳዮች ማቆም እንዳለብን ይነግረናል።
እንግዲህ በአጠቃላይ ይህ ክፍል ጾማችን ዓላማ ያለው፡ እግዚአብሔር የሚደሰትበት፡ እኛም በረከትን የምናገኝበትና ለሌላው የምንተርፍበት ታላቅ የአምልኮ ተግባር መሆኑን ተገንዝበን እንድንጾም እግዚአብሔር በቃሉ ያስተምረናል። እኔስ የመረጥሁት ጾም ይህ አይደለምን?..… የእግዚአብሔር አፍ ተናግሮአልና።

5 comments:

  1. how do say about Quran?the faithfulls believe it is from God

    ReplyDelete
  2. Dear brother our subject is not about Quran. Here we are talking about the Bible and Christians and this title is about fasting {tsom}.

    ReplyDelete
  3. I found your piece about bible. you wrote some reasons that shows bible is from God. But honestly,the reasons you mentioned couldn't confirm it is from heaven unless otherwise we see it with our christian eyes.
    Okay dear, could you please answer my questions again though irrelevant to the topic?

    ReplyDelete
  4. Thank you Brother for your comment.
    But the question and the reasons mentioned are not meant for christians. The reasons explained for the proof {that the Bible is the word of God} are for non-believers. We as christians didn't need any proof. We have faith and we completely accept that the Bible is the Word of God. We prove that with our spirit and soul when we sense , taste the change we get by His word.
    As for your irrelevant question to the topic I think I have answered it. It doesn't concern us to talk about Quran. You can ask this question to those who concern them.Sorry for that.
    10Q.

    ReplyDelete
  5. I am sure no one can justify/prove that the Bible is from God.If you ask someone from other denomination, I am dead sure,he/she will answer that their holy book is from God.the quran,the book of mormon,etc."we prove that with our spirit and soul when we sense,taste the change we get by His word" is a general truth for all denominations.I would rather say the reason you provide about Bible is not for non-believers but for believers.Thank you for trying to answering my question

    ReplyDelete

አስተያየትዎን ይስጡ / Give Comment