የእግዚአብሔር ሥራ
ለሚጠፋ መብል አትሥሩ፤ ነገር ግን ለዘላለም ሕይወት ለሚኖር መብል የሰው ልጅ ለሚሰጣችሁ ሥሩ፤ እርሱን እግዚአብሔር አብ አትሞታልና። እንግዲህ። የእግዚአብሔርን ሥራ እንድንሠራ ምን እናድርግ? አሉት። ኢየሱስ መልሶ፦ ይህ የእግዚአብሔር ሥራ እርሱ በላከው እንድታምኑ ነው አላቸው። ዮሐ 6፣ 27 – 29
-
ጌታችን ኢየሱስ
ክርስቶስ ለሕዝቡ እንጀራና አሳ አበርክቶ ስለሰጣቸው - ለዚያ ሲሉ ነበር የተከተሉት። ለዚህ መልስ ሲሰጣቸው - ለሚጠፋ መብል አትሥሩ፡፡
የምትከተሉኝ ለምን ዓላማ ነው?
እንደ ክርስቲያን /የክርስቶስ ተከታዮች/ በዚች ምድር የመኖራችን ዓላማ ምንድን ነው? ብንል መልሱ የእግዚአብሔርን ሥራ
እንድንሠራ ነው።
-
እርሱን እግዚአብሔር አብ አትሞታል፡- ወልድ የአብ ልጅ ነው። አብን መስሎ፣ አብን አክሎ የተገኘ፣ - ማኅተም፡-
ሲደረግ ቅርጹ በወረቀቱ ላይ በትክክል ያርፋል። የአብን ማንነት በሥጋ /በሰው/ ታትሞ ያየነው በክርስቶስ ነው። - ወልድ ሰው ሲሆን
አብ አትሞታል። የምወደው ልጄ ይህ ነው ብሎ ማረጋገጫ /ማኅተም/ አድርጎበታል።
-
ስለዚህ በክርስቶስ
የሆነውን ማንኛውም መንፈሳዊ ሥራ እግዚአብሔር ከእኔ ነው ብሎ እውቅና /ማረጋገጫ / ይሰጠዋል- ማለት ነው።