Tuesday, July 31, 2012

የእግዚአብሔር ቃል

ሰማያትን ያለምሰሶ ያጸና ነው፡
«በእግዚአብሔር ቃል ሰማዮች ጸኑ፥ ሠራዊታቸውም ሁሉ በአፉ እስትንፋስ» መዝ ፴፫፣፮

ዓለማትን የፈጠረ ነው፡
«ዓለሞች በእግዚአብሔር ቃል እንደ ተዘጋጁ፥ ስለዚህም የሚታየው ነገር ከሚታዩት እንዳልሆነ በእምነት እናስተውላለን።» ዕብ ፲፩፣፫

ሰማይና ምድር ሲያልፉም ይቀጥላል፡
«ሰማይና ምድር ያልፋሉ፥ ቃሌ ግን አያልፍም።» ማቴ ፳፬፣፴፭።

ለዘላለም ይኖራል
«የጌታ ቃል ግን ለዘላለም ይኖራል። በወንጌልም የተሰበከላችሁ ቃል ይህ ነው።» ፩ጴጥ ፩፣፳፭።

ብርቅ የሆነበት ዘመን ነበረ፡
«በዚያም ዘመን የእግዚአብሔር ቃል ብርቅ ነበረ ራእይም አይገለጥም ነበር።» ፩ሳሙ ፫፣፩።

የረሃብ ዘመን ይመጣል፡
«እነሆ፥ በምድር ላይ ራብን የምሰድድበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር እርሱም የእግዚአብሔርን ቃል ከመስማት እንጂ እንጀራን ከመራብና ውኃን ከመጠማት አይደለም።» አሞ ፰፣፲፩።

የበረከት ምንጭ ነው፡
«በኤልያስም እጅ እንደ ተናገረው እንደ እግዚአብሔር ቃል ዱቄቱ ከማድጋው አልተጨረሰም፥ ዘይቱም ከማሰሮው አልጎደለም። » ፩ነገ ፲፯፣፲፮።

የተፈተና ለሚታመኑት ጋሻ ነው፡
«የእግዚአብሔር ቃል ሁሉ ተፈትናለች እርሱ ለሚታመኑት ጋሻ ነው።» ምሳ ፴፣፭።

የሰው ሕልውና በቃሉም እንጂ በእንጀራ ብቻ አይደለም
«ኢየሱስም፦ ሰው በእግዚአብሔር ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም ተብሎ ተጽፎአል ብሎ መለሰለት።» ማቴ፬፣፬

አይሻርም፡
«ነገር ግን የእግዚአብሔር ቃል የተሻረ አይደለም።» ሮሜ ፱፣፮።

አይታሰርም
«ይህንም በመስበክ እንደ ክፉ አድራጊ እስክታሰር ድረስ መከራ እቀበላለሁ፥ የእግዚአብሔር ቃል ግን አይታሰርም።»
፪ ጢሞ ፪፣፱።



እምነት ቃሉን ከመስማት ነው
«እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው።» ሮሜ ፲፣፲፯።

የመንፈሳዊ ውጊያ መሣሪያ ነው
«የመዳንንም ራስ ቁር የመንፈስንም ሰይፍ ያዙ እርሱም የእግዚአብሔር ቃል ነው።» ኤፌ ፮፣፲፯።

ዳግመኛ የተወለድንበት የማይጠፋ ዘር
«ዳግመኛ የተወለዳችሁት ከሚጠፋ ዘር አይደለም፥ በሕያውና ለዘላለም በሚኖር በእግዚአብሔር ቃል ከማይጠፋ ዘር ነው እንጂ።» ፩ጴጥ ፩፣፳፫።

ለመዳን በእርሱ የምናድግበት
«…ለመዳን በእርሱ እንድታድጉ አሁን እንደ ተወለዱ ሕፃናት ተንኰል የሌለበትን የቃልን ወተት ተመኙ።» ፩ጴጥ ፪፣፫።

እንድንታዘዘው ታዘናል፡
«ለአምላክህም ለእግዚአብሔር ቃል ታዘዝ፥ ዛሬም የማዝዝህን ትእዛዙንና ሥርዓቱን አድርግ።» ዘዳ ፳፯፣፲

እንዲሞላብን ታዟል
«የእግዚአብሔር ቃል በሙላት ይኑርባችሁ።» ቆላ ፫፣፲፮።

እንዳንጨምርበት ታዟል፡
«እንዳይዘልፍህ፥ ሐሰተኛም እንዳትሆን በቃሉ አንዳች አትጨምር።» ምሳ ፴፣፮
«በዚህ መጽሐፍ የተጻፈውን የትንቢት ቃል ለሚሰማ ሁሉ እኔ እመሰክራለሁ፤ ማንም በዚህ ላይ አንዳች ቢጨምር እግዚአብሔር በዚህ መጽሐፍ የተጻፉትን መቅሠፍቶች ይጨምርበታል፤» ራእ ፳፪፣፲፰
እንዳናጎልም አስጠንቅቋል፡
«ማንምም በዚህ በትንቢት መጽሐፍ ከተጻፉት ቃሎች አንዳች ቢያጎድል፥ በዚህ መጽሐፍ ከተጻፉት ከሕይወት ዛፍና ከቅድስቲቱ ከተማ እግዚአብሔር ዕድሉን ያጎድልበታል።» ራእ ፳፪፣፲፱።

No comments:

Post a Comment

አስተያየትዎን ይስጡ / Give Comment