Saturday, June 16, 2012

በድካማችን ይሠራልና እንበርታ


«አላወቅህምን? አልሰማህምን? እግዚአብሔር የዘላለም አምላክ፥ የምድርም ዳርቻ ፈጣሪ ነው አይደክምም፥ አይታክትም፥ ማስተዋሉም አይመረመርም።

ለደካማ ኃይልን ይሰጣል፥ ጕልበት ለሌለውም ብርታትን ይጨምራል።

ብላቴኖች ይደክማሉ ይታክቱማል፥ ጐበዛዝቱም ፈጽሞ ይወድቃሉ
እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ ይሮጣሉ፥ አይታክቱም ይሄዳሉ፥ አይደክሙም። »   ኢሳ ፵፣፳፰-፴፩።
F   እግዚአብሔር፡ደካማውን ያበረታል። የተገፉትን ያነሳል። የተረሱትን ያስታውሳል። እንደሰው አይደለም።
F   እግዚአብሔር ደካማነትን በኃይሉ የሚያድስ እንጂ ስንዝል ትቶን የሚሄድ አይደለም። ድካም የባሕርይው ስላልሆነ  የእርሱ የሆኑትም ሲደክሙ ማየት አይወድም፤  ድካማችንን እያየ ዝም የሚል አይደለም።
F   ስንደክም እንደተነዳደለ ፌርሜሎ ወድቀን እንድንቀር አይፈልግም። ጣፋጭነቱ ሲያልቅ እንደምንጥለው እንደ ሸንኮራ ምጣጭ ወይም ደግሞ ኃይሉ እንደደከመ ባትሪ ድንጋይ አይጥለንም። እንደገና ይሞላናል እንጂ አይወረውረንም።
F   ሰዎች፡ አለቆች፡ ባለጊዜዎች ቢገፉንም እርሱ ግን ተቀብሎ ኃይልን አስታጥቆ ያቆመናል፣ ያበረታናል፣ ለሌላ እስክንተርፍ ድረስ ዕውቀትን፡ በረከትን ይሞላናል።
ስለሆነም
በሁሉ እንገፋለን እንጂ አንጨነቅም፤   እናመነታለን እንጂ ተስፋ አንቆርጥም፤
እንሰደዳለን እንጂ አንጣልም፤         እንወድቃለን እንጂ አንጠፋም፤  ፪ ቆሮ ፬፣፱።
ከዚህም ጋር፡-
መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፥  ኤፌ ፮፣፲፪
የሰው ጠላት የለብንም። በዚህ ፋንታ ውጊያችን ጠላቶች ከተባሉት፡-
ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር ነው እንጂ። ኤፌ ፮፣ ፲፪
 ይህን አውቀን፡-
ጠላቴ ሆይ፥ ብወድቅ እነሣለሁና፥ በጨለማም ብቀመጥ እግዚአብሔር ብርሃን ይሆንልኛልና በእኔ ላይ ደስ አይበልሽ። ሚክ ፯፣፰።
እያልን
በሁሉም ላይ ጨምራችሁ የሚንበለበሉትን የክፉውን ፍላጻዎች ሁሉ ልታጠፉ የምትችሉበትን የእምነትን ጋሻ አንሡ፤
የመዳንንም ራስ ቁር የመንፈስንም ሰይፍ ያዙ እርሱም የእግዚአብሔር ቃል ነው።
በጸሎትና በልመናም ሁሉ ዘወትር በመንፈስ ጸልዩ፤ በዚህም አሳብ ስለ ቅዱሳን ሁሉ እየለመናችሁ በመጽናት ሁሉ ትጉ፤
እንደተባልን፡ በእርሱ ብቻ በመታመን እንጽና።
ወንድሞቼ፡-
ሁልጊዜ ደስ ይበላችሁ፤   ሳታቋርጡ ጸልዩ፤     በሁሉ አመስግኑ፤   ፩ተሰ ፭፣፲፯።

No comments:

Post a Comment

አስተያየትዎን ይስጡ / Give Comment