Wednesday, January 11, 2012

ክርስቶስ በመጽሐፍ ቅዱስ-ሁሉ በሁሉ። ክፍል ፪

Christ in the Bible all in all part-2, READ IN PDF
ሁሉን ወራሽ የሆነ፡-
- ከጥንት ጀምሮ እግዚአብሔር በብዙ ዓይነትና በብዙ ጎዳና ለአባቶቻችን በነቢያት ተናግሮ፥
ሁሉን ወራሽ ባደረገው ደግሞም ዓለማትን በፈጠረበት በልጁ በዚህ ዘመን መጨረሻ ለእኛ ተናገረን፤ ዕብ ፩፡ ፩-፫።
    
ሁሉን ያስገዛለት፡-
ሁሉን ከእግሮቹ በታች አስገዛህለት ብሎ መሰከረ። ሁሉን ከእርሱ በታች ባስገዛ ጊዜ ያልተገዛለት ምንም አልተወምና። አሁን ግን ሁሉ እንደ ተገዛለት ገና አናይም፤ ዕብ ፪፡፰።

 ስለሰው ሁሉ ሞትን የቀመሰ፡-
ነገር ግን በእግዚአብሔር ጸጋ ስለ ሰው ሁሉ ሞትን ይቀምስ ዘንድ፥ ከመላእክት ይልቅ በጥቂት አንሶ የነበረውን ኢየሱስን ከሞት መከራ የተነሣ የክብርና የምስጋናን ዘውድ ተጭኖ እናየዋለን። ዕብ ፪፡፱።

 በእርሱ ሁሉ የሆነ፡-
ብዙ ልጆችን ወደ ክብር ሲያመጣ የመዳናቸውን ራስ በመከራ ይፈጽም ዘንድ፥ ከእርሱ የተነሣ ሁሉ በእርሱም ሁሉ ለሆነ፥ ለእርሱ ተገብቶታልና። ዕብ ፪፡፲።


በሆነው ነገር ሁሉ የሚምር፡ በነገር ሁሉ ወንድሞችን ሊመስል የተገባው፡-
ስለዚህ የሕዝብን ኃጢአት ለማስተስረይ፥ ለእግዚአብሔር በሆነው ነገር ሁሉ የሚምርና የታመነ ሊቀ ካህናት እንዲሆን፥ በነገር ሁሉ ወንድሞቹን ሊመስል ተገባው።
እርሱ ራሱ ተፈትኖ መከራን ስለ ተቀበለ የሚፈተኑትን ሊረዳቸው ይችላልና።  ዕብ ፪፡፲፯-፲፰።


ሁሉ በእርሱ የሆነ፡-
በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ።
ይህ በመጀመሪያው በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ።
ሁሉ በእርሱ ሆነ፥ ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም። ዮሐ ፩፡ ፩-፫።

ሁሉ በእርሱ እንዲያምኑ፡-
ሁሉ በእርሱ በኩል እንዲያምኑ ይህ ስለ ብርሃን ይመሰክር ዘንድ ለምስክር መጣ። ዮሐ ፩፡ ፯።

ስለርሱ በመጻሕፍት ሁሉ የተጻፈ፡-
ከሙሴና ከነቢያት ሁሉ ጀምሮ ስለ እርሱ በመጻሕፍት ሁሉ የተጻፈውን ተረጐመላቸው። ሉዋ ፳፬፡፳፯።

ሁሉ ከአባቱ ዘንድ የተሰጠው፡-
ሁሉ ከአባቴ ዘንድ ተሰጥቶኛል፤ ማቴ ፲፩፡፳፯።

በፈጣሪነቱ - ሁሉ በእርሱ፡ የተፈጠረ፡-
የሚታዩትና የማይታዩትም፥ ዙፋናት ቢሆኑ ወይም ጌትነት ወይም አለቅነት ወይም ሥልጣናት፥ በሰማይና በምድር ያሉት ሁሉ በእርሱ ተፈጥረዋልና ከፍጥረት ሁሉ በፊት በኵር ነው። ሁሉ በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሮአል።

በአዳኝነቱ -  ሁሉ ለእርሱ የተፈጠረ፡-
የሚታዩትና የማይታዩትም፥ ዙፋናት ቢሆኑ ወይም ጌትነት ወይም አለቅነት ወይም ሥልጣናት፥ በሰማይና በምድር ያሉት ሁሉ በእርሱ ተፈጥረዋልና ከፍጥረት ሁሉ በፊት በኵር ነው። ሁሉ በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሮአል። ቆላ ፩፡፲፮፡፡

ከሁሉ በፊት የነበረ፡ ሁሉ በእርሱ የተጋጠመ፡-
እርሱም ከሁሉ በፊት ነው ሁሉም በእርሱ ተጋጥሞአል።
እርሱም የአካሉ ማለት የቤተ ክርስቲያን ራስ ነው። እርሱም በሁሉ ፊተኛ ይሆን ዘንድ፥ መጀመሪያ ከሙታንም በኵር ነው። ቆላ ፩፡፲፰።

1 comment:

  1. ....ይህን በሐዋርያት የተገለጠውን እውነት ስለመሰከርህ ደስ ብሎኛል። ቃሉም የሚለው «የሉቃስ ወንጌል 12፥8 እላችሁማለሁ፥ በሰው ፊት የሚመሰክርልኝ ሁሉ፥ የሰው ልጅ ደግሞ በእግዚአብሔር መላእክት ፊት ይመሰክርለታል» ያለውን ዋጋ ያለጥርጥር ትቀበላለህና።

    ReplyDelete

አስተያየትዎን ይስጡ / Give Comment