Wednesday, January 25, 2012

ፍቅር በመጽሐፍ ቅዱስ

Love in the Bible, READ IN PDF
ኃጢአትን  የምትከድን
ጥል ክርክርን ታስነሣለች ፍቅር ግን ኃጢአትን ሁሉ ትከድናለች።  ምሳ ፲፡፲፪።
ሰዎች የጌታ መሆናችን የሚያውቁበት
እርስ በርሳችሁ ፍቅር ቢኖራችሁ፥ ደቀ መዛሙርቴ እንደ ሆናችሁ ሰዎች ሁሉ በዚህ ያውቃሉ። ዮሐ ፲፫፡፴፭
ከእርሱ ማንም ወይም ምንም የማይለየን
ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ፥ ወይስ ጭንቀት፥ ወይስ ስደት፥ ወይስ ራብ፥ ወይስ ራቁትነት፥ ወይስ ፍርሃት፥ ወይስ ሰይፍ ነውን?  ሮሜ ፰፡፴፭።
ከፍታም ቢሆን፥ ዝቅታም ቢሆን፥ ልዩ
ፍጥረትም ቢሆን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን ካለ ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን እንዳይችል ተረድቼአለሁ። ሮሜ ፰፡፴፱፤
የመንፈስ ፍሬ

የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፥ የውሃት፥ ራስን መግዛት ነው።  ገላ ፭፡፳፪

ክፉ የማያደርግ የሕግ ፍጻሜ
ፍቅር ለባልንጀራው ክፉ አያደርግም፤ ስለዚህ ፍቅር የሕግ ፍጻሜ ነው። ሮሜ ፲፫፡፲
ከቋንቋ በላይ
በሰዎችና በመላእክት ልሳን ብናገር ፍቅር ግን ከሌለኝ እንደሚጮኽ ናስ ወይም እንደሚንሽዋሽዋ ጸናጽል ሆኜአለሁ። ፩ቆሮ ፲፫፡፩
ከእውቀትና ከእምነት በላይ
ትንቢትም ቢኖረኝ ምሥጢርንም ሁሉና እውቀትን ሁሉ ባውቅ፥ ተራሮችንም እስካፈልስ ድረስ እምነት ሁሉ ቢኖረኝ ፍቅር ግን ከሌለኝ ከንቱ ነኝ። ፩ቆሮ ፲፫፡፪
ከምጽዋትና ከመስዋዕትነት በላይ
ድሆችንም ልመግብ ያለኝን ሁሉ ባካፍል፥ ሥጋዬንም ለእሳት መቃጠል አሳልፌ ብሰጥ ፍቅር ግን ከሌለኝ ምንም አይጠቅመኝም። ፩ቆሮ ፲፫፡፫
ከእምነትና ከተስፋ በላይ
እንዲህም ከሆነ፥ እምነት ተስፋ ፍቅር እነዚህ ሦስቱ ጸንተው ይኖራሉ፤ ከእነዚህም የሚበልጠው ፍቅር ነው። ፩ቆሮ ፲፫፡፲፫።
ስለዚህ፡-
በእናንተ ዘንድ ሁሉ በፍቅር ይሁን።  ፩ቆሮ ፲፮፡፲፬።

No comments:

Post a Comment

አስተያየትዎን ይስጡ / Give Comment