Friday, February 17, 2012

የኖኅ ልጆች ምድርን መከፋፈል

Noah and his sons over the world, READ IN PDF
እግዚአብሔርም ኖኅንና ልጆቹን ባረካቸው እንዲህም አላቸው፦ ብዙ ተባዙ፥ ምድርንም ሙሉአት።
አስፈሪነታችሁና አስደንጋጭነታችሁ በምድር አራዊት፥ በሰማይም ወፎች፥ በምድር ላይ በሚንቀሳቀሱትም፥ በባሕር ዓሦችም ሁሉ ላይ ይሁን እነርሱም በእጃችሁ ተሰጥተዋል።
ሕይወት ያለው ተንቀሳቃሽ ሁሉ መብል ይሁናችሁ ሁሉን እንደ ለመለመ ቡቃያ ሰጠኋችሁ።
ነገር ግን ነፍሱ ደሙ ያለችበትን ሥጋ አትብሉ
ነፍሳችሁ ያለችበትን ደማችሁን በእርግጥ እሻዋለሁ ከአራዊት ሁሉ እጅ እሻዋለሁ ከሰውም እጅ፥ ከሰው ወንድም እጅ፥ የሰውን ነፍስ እሻለሁ።
የሰውን ደም የሚያፈስስ ሁሉ ደሙ ይፈስሳል ሰውን በእግዚአብሔር መልክ ፈጥሮታልና።
እናንተም ብዙ፥ ተባዙ በምድር ላይ ተዋለዱ፥ እርቡባትም።



ከመርከብ የወጡት የኖኅ ልጆችም እነዚህ ናቸው፥ ሴም፥ ካም፥ ያፌት ካምም የከነዓን አባት ነው።
የኖኅ ልጆች እነዚህ ሦስቱ ናቸው ከእነርሱም ምድር ሁሉ ተሞላች።
ዘፍ ፱፡ -፲፰።
ከእነዚህም የአሕዛብ ደሴቶች ሁሉ በየምድራቸው በየቋንቋቸው በየነገዳቸው በየሕዝባቸው ተከፋፈሉ።……የኖኅ የልጆቹ ነገዶች እንደ ትውልዳቸው በየሕዝባቸው እነዚህ ናቸው። አሕዛብም ከጥፋት ውኃ በኋላ በምድር ላይ ከእነዚህ ተከፋፈሉ።  ዘፍ , ,፡፴፪
የእግዚአብሔርም ቃል ተፈጸመ።
-  የኖኅ ልጆች ምድርን ሞሉአት
ー አሕዛብ, ሌሎች ሕዝቦች በሙሉ ከእነዚህ እንደተገኙ በታሪክ ትምህርት ይታወቃል። 

No comments:

Post a Comment

አስተያየትዎን ይስጡ / Give Comment