Wednesday, February 22, 2012

ጾም በመጽሐፍ ቅዱስ

Fasting in the Bible, READ IN PDF
እግዚአብሔር የመረጠው ጾም
እኔስ የመረጥሁት ጾም ይህ አይደለምን? የበደልን እስራት ትፈቱ ዘንድየቀንበርንስ ጠፍር ትለቅቁ ዘንድየተገፉትንስ አርነት ትሰድዱ ዘንድቀንበሩንስ ሁሉ ትሰብሩ ዘንድ አይደለምን?
እንጀራህንስ ለተራበ ትቈርስ ዘንድስደተኞቹን ድሆች ወደ ቤትህ ታገባ ዘንድየተራቈተውንስ ብታይ ታለብሰው ዘንድ፥ ከሥጋ ዘመድህ እንዳትሸሽግ አይደለምን? ኢሳ ፶፰፡ ፮-፯።

እግዚአብሔር የሚለመንበት መንገድ
በአምላካችን ፊት ራሳችንን እናዋርድ ዘንድ፥ ከእርሱም የቀናውን መንገድ ለእኛና ለልጆቻችን ለንብረታችንም ሁሉ እንለምን ዘንድ  በዚያ በአኅዋ ወንዝ አጠገብ ጾም  አወጅሁ።
ስለዚህም ነገር ጾምን፥ ወደ እግዚአብሔርም ለመንን እርሱም ተለመነን። ዕዝ ፰፡፳፩-፳፫

ወደ እግዚአብሔር የምንመለስበት መንገድ
አሁንስ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ በፍጹም ልባችሁ፥ በጾምም፥ በልቅሶና በዋይታ ወደ እኔ ተመለሱ።
ኢዩ ፪፡፲፪

ከልመና  (ከጸሎት) ጋር የሆነ ጾም
ዳዊትም ስለ ሕፃኑ እግዚአብሔርን ለመነ ዳዊትም ጾመ ገብቶም በመሬት ላይ ተኛ። ፪ሳሙ ፲፪፣፲፮

በመዋረድ የሆነ ጾም
አክዓብም ይህን ቃል በሰማ ጊዜ ልብሱን ቀድዶ ገላውን ማቅ አለበሰ፥ ጾመም፥ በማቅ ላይም ተኛ፥ ቅስስ ብሎም ሄደ።  ፩ነገ ፳፡፳፯።


የኅብረት ጾም

በዚህም ወር በሀያ አራተኛው ቀን የእስራኤል ልጆች ጾመው፥ ማቅም ለብሰው፥ በላያቸውም ትቢያ ነስንሰው ተከማቹ።  ነህ ፱፣፩

የአዋጅ ጾም
በደብዳቤውም። ስለ ጾም  አዋጅ ንገሩ፥ ናቡቴንም በሕዝቡ ፊት አስቀምጡት
የጾም አዋጅ  ነገሩ፥  ናቡቴንም  በሕዝቡ ፊት አስቀመጡት። ፩ነገ ፳፣፱ ና ፲፪

ለመከራና ለስደት መፍትሔ
…..እርሱም፦ በዚያ ስፍራ ያሉት ከምርኮ የተረፉት ቅሬታዎች በታላቅ መከራና ስድብ አሉ የኢየሩሳሌምም ቅጥር ፈርሶአል፥ በሮችዋም በእሳት ተቃጥለዋል አሉኝ።
ይህንም ቃል በሰማሁ ጊዜ ተቀምጬ አለቀስሁ፥ አያሌ ቀንም አዝን ነበር በሰማይም አምላክ ፊት  እጾምና  እጸልይ ነበር፥  ነህ ፩፡፫-፬።

ለጥፋት አዋጅ መልስ
የንጉሡም ትእዛዝና አዋጅ በደረሰበት አገር ሁሉ በአይሁድ ላይ ታላቅ ኀዘንና ጾም  ልቅሶና ዋይታም ሆነ ብዙዎችም ማቅና አመድ አነጠፉ።  አስ ፬፡፫

በጾም ራስን ማድከም
እኔስ እነርሱ በታመሙ ጊዜ ማቅ ለበስሁ፥ ነፍሴንም በጾም አደከምኋት  ጸሎቴም ወደ ብብቴ ተመለሰ። መዝ ፴፬፡(፴፭) ፲፫
ጕልበቶቼ በጾም ደከሙ  ሥጋዬም ቅቤ በማጣት ከሳ። መዝ ፩፻፰ (፩፻፱) ፣፳፬

የተቀደሰ ጾም
ጾምን ቀድሱ፥ ጉባኤውንም አውጁ ሽምግሌዎችንና በምድር የሚኖሩትን ሁሉ ወደ አምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር ቤት ሰብስቡ፥ ወደ እግዚአብሔርም ጩኹ። ኢዩ ፩፡፲፬።
በጽዮን መለከትን ንፉ፥ ጾምንም ቀድሱ፥ ጉባኤውንም አውጁ፥  ኢዩ ፪፡፲፭

የአገልግሎት አንዱ መሳሪያ
እርስዋም ሰማኒያ አራት ዓመት ያህል መበለት ሆና በጣም አርጅታ ነበር፤ በጾምና  በጸሎትም ሌሊትና ቀን እያገለገለች ከመቅደስ አትለይም ነበር።  ሉቃ ፪፡፴፯።

ለዲያብሎስ ፈተና ድል ማድረጊያ
ከዚያ ወዲያ ኢየሱስ ከዲያብሎስ ይፈተን ዘንድ መንፈስ ወደ ምድረ በዳ ወሰደው፥
አርባ ቀንና አርባ ሌሊትም ከጦመ  በኋላ ተራበ። …………ያን ጊዜ ዲያብሎስ ተወው፥ እነሆም፥ መላእክት ቀርበው ያገለግሉት ነበር።  ማቴ ፬፡፩ - ፲፩
 

No comments:

Post a Comment

አስተያየትዎን ይስጡ / Give Comment