ባለፈው መመለስ የጀመርነው ጥያቄ፡- እግዚአብሔር ፍጥረታትን በ፮ ቀን እንደጨረሰ በዘፍጥረት ፩ ተጠቅሶአል። አንድ ቀን የምንለው ፀሐይ ፡ወጥታ፡ ገብታ መልሳ እስክትወጣ ያለውን ፳፬ ሰዓት ነው። ፀሐይ ግን የተፈጠረች በአራተኛው ቀን ረቡዕ ነው። ቁ ፲፬። ታዲያ ከዚያ በፊት የነበሩት ፫ ቀናት (ከእሑድ- ማክሰኞ) በምን ተቆጠሩ?
መጽሐፍቅዱስ ከሰዎች የኑሮ ልማድ ጋር በየጊዜው መሻሻል የማያስፈልገው አንድ ጊዜ የተጻፈና ሁልጊዜ እየተነበበ ሕይወትን የሚመራ ልዩ መጽሐፍ መሆኑን፡፡ ባለፈው በጥያቄ ያነሳነው የመጀመርያው ክፍለ-ንባብ እንደየአካባቢዎቹ የዕውቀትና የመረዳት ደረጃ ሊስማማ ይችላል ብለን ብዙም ላልተማረ የኔብጤ መሃይም ሆነ በጥልቀት ለሚመራመር ሳይንቲስት ለሁለቱም በየራሳቸው በሚረዳ መልኩ መጻፉን አይተናል፡፡ ሁለቱም ሰዎች ናቸው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስም ለሰዎች ነው፡፡