. እግዚአብሔርን ፍለጋ - ቀጣይ፡-
ምኑን
ነው የምንፈልገው?፡-
ባለፈው ክፍል - እግዚአብሔርን ፍለጋ በሚል - ስለእግዚአብሔር መኖር በተፈጥሮ፣ በሕሊና፣
በመሳሰሉት ማረጋገጥ እንደሚቻል አይተናል።
በአሁኑ
ጊዜ የፈጣሪን /የእግዚአብሔርን መኖር የሚጠራጠር ብዙም ላይኖር ይችላል፤ ወይም በአሁኑ ጊዜ ለኛ ይህ ብዙም አሳሳቢ ጥያቄ አይደለም።
ከላይ ከተጠቀሱት በአንዱ ወይም በሌላ በሆነ መንገድ - የእግዚአብሐየርን
መኖር አረጋገጥን - እግዚአብሔርን አገኘነው። ካገኘነው በኋላ ምኑን
ነው ማየት የምንፈልገው? ስንል ዳዊት እንዲህ ይለናል፡-
ሁልጊዜ ፊቱን ፈልጉ። መዝ ፻፬/፻፭፣ ፬
-
የእግዚአብሔር ሕልውና /መኖሩ/ የሚረጋገጠው አንድ ጊዜ ነው።
ከተገኘ - አለ። አይጠፋም።
ከዚያ በኋላ ግን ሁልጊዜ መፈለግ ያለብን - ፊቱን -
ነው።
-
በምናያቸው ፍጥረታት የእግዚአብሔርን አስደቂ ኃያል እጅ እናያለን። ቀጥሎ ግን ሁልጊዜ ፊቱን ማየት አለብን።
ፊት ምንድን ነው? -የማንነት መለያ ነው። ሁላችንም የምንለየው በፊታችን ነው። መታወቂያ ላይ የሚደረገው ፎቶ - ጉርድ
ፎቶ - የሚያሳየው ፊታችንን ነው።
-
አንድን ሰው አየሁት ለማለት - ፊቱን - ማየት ግድ ነው።
-
ሙሴ ከእግዚአብሔር ጋር ሕዝቡን ነጻ አውጥቶ ሲመራ፣ በተአምራት
ብዙ ዘመን ከኖረ በኋላ፡- እግዚአብሔርን እንዲህ ሲል ጠየቀው፡-
o እርሱም፦ እባክህ ክብርህን አሳየኝ አለ።….
-
እግዚአብሔርም -
o …ሰው አይቶኝ አይድንምና ፊቴን ማየት አይቻልህም......ፊቴ
ግን አይታይም» አለ። ዘጸ ፴፫፡ ፲፯ - ፳፫።
-
ፊቱን ማየት የማይቻል ከሆነ -ፊቱ የማይታይ ከሆነ
- ለምን ፊቱን ፈልጉ ተባለ? - ማየት የማይቻለው በዚህ በሥጋ ዓይን ነው። እግዚአብሔር
መንፈስ ነውና።
-
በመንፈስ ግን ከእኛ ጋራ ሲሆን፣ ሲሠራ፣ ሕይወታችን ሲጠብቅ… እናየዋለን።
ከእያንዳንዳችን የራቀ አይደለም።
(የሐዋ ፲፯፣ ፳፮)
-
መምህራን እንደሚያስተምሩት በርግጥ የሙሴ ጥያቄ ተመልሷል፤
ነገር ግን የተመለሰው ከ1400 ዓመት በኋላ- በኢየሱስ ክርስቶስ - በደብረ ታቦር ነው።
o ሙሴ በጥየቄው መሰረት በዓይነ-ሥጋ በአካል እግዚአብሔርን ያየው - በኢየሱስ ክርስቶስ - ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው
የሆነው አግዚአብሔር ነውና።
በፊታቸውም ተለወጠ፥ ፊቱም እንደ ፀሐይ በራ፥ ልብሱም እንደ ብርሃን ነጭ ሆነ። እነሆም፥ ሙሴና ኤልያስ ከእርሱ ጋር ሲነጋገሩ ታዩአቸው። ማቴ ፲፯፣ ፪ - ፫
ዛሬም እኛ እግዚአብሔርን በመንፈስ ዓይን የምናየው - በኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
ስለዚህ፡-